ዶ/ር አባ ኀይለ ማርያም መለሰ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ምክትል ዋና ዲን) |
- መምህራኑም ከፍተኛ የአስተዳደር በደል እንደሚደርስባቸው ተናገሩ
- ፓትርያሪኩ÷ ተጠያቂዎች በጥናት ተለይተው ርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ ሰጥተዋል
- የመብት ማስከበር እንቅስቃሴው የመናፍቃን መጠቀሚያ እንዳይኾን ጥንቃቄ ያስፈልጋል
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህራን÷ ደቀ መዛሙርቱ ትምህርት በማቋረጥና ከምግብ በመከልከል የጀመሩትን አካዳሚያዊ መብትን የማስከበር የተቃውሞ እንቀስቃሴ አቁመው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የማግባባት ጥረት መጀመራቸው ተገለጸ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ተቃውሞ ያነሡባቸው የኮሌጁ ሁለት ሓላፊዎችና የጠየቋቸው አካዳሚያዊ መብቶች ጉዳይ በቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ መታየቱንና በጥልቀት እንዲጠና በፓትርያሪኩ መመሪያ የተሰጠበት መኾኑን ዋስትና በማድረግ ነው መምህራኑ ደቀ መዛሙርቱን የማግባባት ጥረት መጀመራቸው የተመለከተው፡፡