- ከ400 በላይ ምዕመናን በእንባ ወደ እስር ቤት ሸኝተዋቸዋል፡፡
- የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የበላይ አካል ተጽህኖ አለበት ፤
(አንድ አድርገን ሰኔ 22 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በፍርድ ቤቱ ውሳኔ በጣም አዝነናል ፤ ሲጀመር አንስቶ በባቦጋያ መድሃኒዓለም ቦታ እና በኩሪፍቱ ሪዞርት መካከል ያለው የቦታ ውዝግብ በየጊዜው ማቅረባችን ይታወቃል፤ አቅማችን በፈቀደው መጠን ጉዳዩን ሰዎች ዘንድ እንዲደርስ የመፍትሄ አካላት እንዲሆኑ ያላሰለሰ ጥረት አድርገናል ፤ ከወራት በፊት የቤተክርስትያኑን ቦታ በአካባቢው ምዕመናን ጉዳዩን ዳር እዲያደርሱ የተወከሉ ሰዎች በፍርድ ቤት “እናንተ መጠየቅ አትችሉም ቤተክርስትያኒቱ የወከለቻችሁ አካላት አይደላችሁም” በማለት ለኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት እንደተወሰነለት ገልጸን ፅፈን ነበር ፤
ከዚህ በኋላ ምዕመኑን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተስፋ ለማስቆረጥ ወደፊት ምንም ጥያቄ እንዳይጠይቁ ለማሸማቀቅ አቶ ጌታቸው ዶኒ ፤ የሪዞርቱ ባለቤትና የፍርድ ቤት ጠበቃቸው ከባቦጋያ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያ አስተዳዳሪ ጋር በመሆን የሀሰት ክስ ማቅረባቸውን ይታወሳል ፤ ይህ በእንዲህ እያለ አቶ ጌታቸው ዶኒ የሀሰት ምስክሮችን አስመጥቶ ፍርድ ቤት በማቆም ማስመስከሩ ይታወቃል ፤ በዚህ የፍርድ ቤት የምስክር ሂደት የቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ ፍርድ ቤት ውስጥ የሚሰሙትን ምስክርነት ለሶስተኛው ምስክር አሳልፈው ሲናገሩ በመያዛቸው ለ24 ሰዓት ታስረው በ2000 ብር ዋስ መፈታታቸው ይታወቃል ፤ ፍርድ ቤቱ እኝህን አስተዳዳሪ አቃቢ ህግ ክስ እንዲመሰርት ቢያዝም አቃቢ ህግ ልብ አግኝቶ ይህን ሲያደርግ መመልት አልተቻለም ፤ ፍርድ ቤቱ የተቀመጠው ህግ ከባለስልጣናት ትዕዛዝ ሲበልጥበት መመልከት አልቻልንም ፤ አስተዳዳሪው ምስክሮቹ ቃላቸው አንድ አንዲሆን በማሰብ የውስጡን ለውጩ ምስክር አሳልፈው ምስክርነቱን ሲናገሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በዝምታ መታለፋቸው ሁሉን አስደምሟል ፤ በመሰረቱ ምስክርነት እየተሰማ ሳለ አይደለም መስካሪ የችት ታዳሚው ችሎቱን አቋርጦ መውጣት እንደሌለበት ያስቀምጣል ፤ ዳኛው “ችሎትን በማወክ” በሚል አንቀጽ እዚያው ሌላ ፋይል ሳይከፍት የቅጣተኝነት ፍርድ ማስተላለፍ ይችል ነበር ፤