ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንል ወላዲተ አምላክ ዘይትነብብ በዕለተ ሠሉስ
ለምስጋና ሁለተኛ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን ነው በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣች የብርሃ ምንጻፍ ይነጸፋል የብርሃን ድባብ ይዘረጋል ከዚያ ላይ ሁና ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም ትለዋች እርሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል ወድሰኒ ትለዋች በዕለተ
ሰኑይ ድርክር አልቋልና ባርክኒ ይላታ በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በሳዕሌከ ትለዋች ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል፡፡ ውዳሴ ዘሠሉስ ውዳሴ በሠሉስ ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ ይላል ቃለ ጸሐፊ ነው፡፡ እርሱ ግን አክሊለ ምክሕነ ብ ይጀምራል አክሊለ ምክሕኒ፡፡ አክሊል የወዲህኛው ምክሕ የሰዲያኛው፡፡ ወቀዳሚተ መድኃኒትነ፡፡ ቀዳሚት የወዲህኛው መድኃኒት የወዲያኛው፡፡ መወሠረተ ንጽሕነ፡፡ መሠረት የወዲህኛው ንጽሕ የወዲያኛው፡፡ ኮነ በማርያም፡፡ በማርያም ድንግል ሆነልን አለ በዚህ ቀን ከነገሥታት ዳዊትን ከመሳፍንት ኢያሱን ከደናግል ኤልያስን አስከትላ መጥታለች ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት በህትባ የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለህም፡፡ ኢያሱም መድኃኒት ብትባል የደኅንነታችን መጀመሪያ መሆን አልተቻለህም፡፡ ኤልያስም ንጹሕ ድንግል ብትባል የንጽሕናችን መሠረት ዘውድ የደኅንነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ምርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም አክሊሎሙ ለሰማዕት እንዲለው አክሊለ ሰማዕት የሚባል ጌታ ጥንተ ሕይወቶሙ እንዲለው ጥንተ ሕይወት የሚባል ጌታ አኃዜ ዓለም በእራኁ ኲሉ ኁዝ ውስተ እዴሁ መሠረተ ዓለም ይጾውር ድደ ወይነብር ጠፈረ እንዲል፡፡ መሠረተ ዓም የሚባል ጌታ በድንግል ማርያም ማለት ፍጽምት ማለት ነው፤ ለጊዜው መልክ ከደም ግጋት ስተባብራ ተገኝታለች ፍጻሜው ግን ንጽሐ ሥጋ ከንጽሐ ነፍስ ድንጋሌ ሥጋ ከድንጋ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችና አንድም ጸጋ ወሀብት ማለት ነው፤ ለጊዜው ለናት ላታቷ ጸጋ ሁና ተሰጥታለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁሉ ጸጋ ሁና ተሰጥታለችና አንድም መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማት ነው፡፡ ምዕመናንን መርታ ገነት መንግሥተ ሰማያት አግብታለችና አንድም ልዕልት ማለት ነው ሮም አአርያ ማለት ልዑል ማት እንደሆነ፡፡ እርስዋንም መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን ይላታልና፡፡ አንድም ማኅበረ መሃይምናን ወሕዝብ ተለአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ተፈሥሒ ቤተ እስራኤል ወተሐሠዪቤተ ይሁ ማለት ነው፡፡ አንድም ማርያም ማት እግዝእተ ብዙኃን እንዲ አይለውም ብሎ ማርያም ማለት ቅሉ እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ አብሃም ማለት አበ ብዙኃን ማለት እንደሆነ፡፡ እንተ ወለደት ለነ ዘአእግዚአብሔር ቃለ፡፡ መመኪያነቷን በቅጽል አመጣው አካላዊ ቀልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኝልን፡፡ ዘኮነ ሰብአ በእንተ መድኃኒትነ፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ፡፡ እምድኅረ ኮነ ሰብአ ጥዩቀ አምላክ ፍጹም ውእቱ፡፡ ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው ፡፡ ሐራ ጥቃ ቃል ሥታ ኮነ ያውን ይዘው ወደታች ተለወጠ ይላሉና፡፡ ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው አለባቸው፡፡ ወበእንተዝ ወለደቶ እንዘ ድንግል ይእቲ፡፡ ስለዚህ ነገር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ወለደችው፡፡ መንክር ኀይለ ወሊዶታ ዘኢይ ትነገር፡፡ ድንቅ የሚሆን የመውለዷ ሥራ የማይመረመር ነው ፡፡ የማይመረመር የመውለዷ ሥራ ድንቅ ነው፡፡ በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለሚኚልን፡፡ ሐተታ እንደ ሰኞ፡፡ እስመ በፈቃዱ፡፡ በርሱ ፈቃድ፡፡ ወበሥምረተ አቡሁ፡፡ ባበቱ ፈቃድ ወመንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ፡፡ መጽአ ወአድኃነነ፡፡ ሰው ሆኖ አዳን፡፡ አንድም ሰው ሁኖ አድኖናልና፡፡ መንድር ብህ እስር፡፡ መጽአ በኲርሕ፡፡ በግድ ሰው ሆነ የሚሉ መናፍቃን አሉና እሰመ በፈቃዱ አበባቸው፡፡ በዕለተ ፍጥረት አብ መንፈስ ቅዱስ፡፡ አዳም ስሑት ፍጥረት ነው፡፡ አይፈጠር ቢሉ ወልድ እኔ ያዛለሁ ይፈጠር ብሎ ነበርና በግድ ሰው ሆነ የሚሉ መናፍቃን አሉና እስመ በፈቃዱ አለባቸው፡፡ እሊህንም እመቦ ዘይቤ ተሐብዩ ለብእሲ እምቅድመ ይፍጥሮ ውጉዘ ለይኩን ብሎ ሊቁ በዐሥራ አንደኛው ግዝት አንሥቷቸዋል፡፡ ኒህስ ምን ያለውን ይዘው ተነሥተዋል ቢሉ በዕርገተ ኢሳይያስ ሰማዕኩ እዘ ይአኤዝዞ እግዚእ ለእግዚእየ ወይቤሎ ኅልፍ እንተ ሰብዐቱ አናቅጸ ሰማያት ወረደ ላዕሌሁ ለመልአከ ሞት ካው ተሐብዩ የሚል ጥሬ አገኘን ብለው ይኸንን ይዘው ተነሥተዋል፡፡ ዐቢይ ውእቴ ስብሐተ ድንግልናኪ አማርያ ድንግል ፍጽምት፡፡ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት የምትሆኚ እመቤታችን በድንግልና ጸንተሸ ብትገኚ ላንቺ የተሰጠሸ ጸጋ ፍጹም ነው፡፡ ርከብኪ ሞገስ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡፡ እግዚ አብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሸልና፡፡ አንድም በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ላንች የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ አንቲ ውእቱ ሰዋሰው ዘርእየ ያዕቆብ እምድር ዘይበጽሕ እስከ ሰማይ ወመላእክተ እግዚአብሔር የዐርጉ ወይወርዱ ወስቴታ፡፡ መጽሐፍ ምሥጢር እንጂ ዘይቤ አይጠነቅቅምና ዘይበጸሕ ብሎ ውሰቴታ አለ ከምድር እስከ ሰማይ ተተክላ መላእክት ስወጡባት ሲወር ዱባት ያዕቆብ በፍኖት ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ ታሪክ ያዕቆብ ወደ ሶርያ ሲሄድ ሎዛ ሲደርስ ጊዜ መሸበት ከመንገዱ እልፍ ብሎ ድንጊያ ተንተርሶ ተኛ ሌሊት በራእይ የወርቅ መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ተተክላ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ዙፋን ባላዋ ላይ ተዘርግቶ ንጉሥ በላዋ ላይ ተቀምጦባት ሲወርዱባት ዙፋን ባላዋ ላይ ተዘርግቶ ንጉሥ በላዋ ላይ ተቀምጦባት ያያል ሲነጋ ተነሥቶ ደንጊያ ተክሎ ዘይት አፍስሶባት ዛቲ ይአቲ ኆኅታ ለሰማይ ዝየ ይትሐነጽ ቤተ እግዚአብሔር ብሎ ይሔዳል፡፡ ይኸም ምላሴ ነው የወርቅ መሰላ የመቤታችና ደንጊያው የትንቢተ ነቢያት እመቤታችን በትንቢተ ነቢያት ጸንታ ለመገኘቷ ምሳሌ፡፡ አ ድንግል አምሳ ወትንቢት ዘነቢያት እንዲል፤ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት አለ ቤታችን ከመቤታችን ሰው ከነሆኑ አስቀድሞ ለተልእኮ አይወጡም አይወርዱም ነበር ጌታችን ከመቤታችን ሰው ከሆነ በኋላ ግን ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ሆነዋልና አንድም የዐርጉ ሰው አምላክ ሆነ ይወርዱ አምላክ ሰው ሆነ እያ፤ ዙፋ የማኅፀኑዋ ንጉሥ የጌታ ምሳሌ፡፡ ንድም ደንጊያው የታቦት ዘይት የሜሮን ምሳሌ፡፡ አንድም ያዕቆብ የቀሳውስት ደንጊያው የአሕዛብ ዘይት የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግ፤ማ እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡: ይቆየን...........