ሰሞኑን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ስለ ዋልድባ ገዳማችን ይዞታ እና ከፊታችን የተደቀነውን አደጋ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያን ዜና ጨምሮ ስንሰማው ቆይተናል፥ የሚገርመው ግን የኢትዮጵያ ዜና ዘገባ እና በሌላው ዓለም የሚዘገበው ዘገባ በጣም የተለያየ መሆኑ ብዙዎችን ዜጎች ይልቁንም ኦርቶዶክሳዊያኑን ግራ ሳያጋባ የቀረ አይመስለንም። ለዚህም ነው አንድ የዝግጅታችን የዘወትር ታዳሚ አንድ ዜና ከአሜሪካዋ መዲና ከሆነችው ዋሽንግተን የላኩልን፥
ነገሩ እንዲህ ነው ባለፈው ጥቂት ሳምንት በፊት የቤተክርስቲያኑ ልጆች በአንድነት ተሰባስበው መልስ ቢሰጥም ባይሰጥም ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይረዳል ብለው እንደማንኛውም የሀገሪቱ ዜግነታቸው፣ እንደ ሃይማኖተኛነታቸው ድምጻቸውን ለማሰማት ከ1200 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በዚሁ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊትለፊት ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ አድርገው እንደነበረ ለሁላችንም የተሰወረ አይደለም፥ በዚህ ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ከመላው ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚከገኙ ቤተክርስቲያናት ወጣቶች፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ አረጋዊያን አባቶች እና እናቶች እንዲሁም ሕጻናት በዚሁ ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ተሳትፎ አድርገው እንደነበረ በተለያዩ የዜና መሰራጫዎች ተገንዝበናል፥ ከዚህ በተጨማሪ በጣም ጥቂት ከሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ካሕናት ተገኝተው ነበር እና ነገሩን ለማጣራት የዚህ ዝግጅት ክፍል በተለያየ መልኩ ሙከራ ስናደርግ ቆይተናል በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለው ቤተክህነት ምንም ተስፋ የምጣልበት እንዳልሆነ በዘገባቸው ተረድተናል፤ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ካህናት አባቶች በተለይ ህይወታቸውን በምንኵስና የሚኖሩ የዋልድባን ጉዳይ ከማናቸውም የህብረተሰቡ ክፍል በተለየ ይቆረቆሩለታል የሚል በተለያዩ የህብረተቡ ክፍሎች ታስቦ ነበር፥ ነገር ግን ያ ሊሆን ያልቻለበት ምክንያት ለሁላችንም እንቆቅልሽ ሆኖ ሰንብቷል። ለሁሉ በላይ ግን ትልቅ የህዝብ ተቃውሞ ያስነሳል ብለን የገመትነውን ለማጣራት በተለያዩ መንገዶች ሞክረን፣ ሁሉም መንገዶች ተመሳሳይ ናቸው፥ ነገሩ እንዲህ ነው።
|
አቡነ ፋኑኤል |
በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመው የተመደቡት አቡነ ፋኑኤል በተለያየ ጊዜ ትልቅ ተቃውሞ ሲደርስባቸው ቆይቷል ተቃውሞውም እንደቀጠለ ነው፥ አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ብፁዕነታቸው በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ በተደረገበት ወቅት፣ የብዙዎች ክርስቲያኖች፣ ሀገር ወዳድ ማኅበረሰብ፣ የሀገር ሀብት እና ቅርስ መውደም እና መጥፋት የሚጨንቃቸው በሙሉ የብጹዕነታቸውን መምጣት እና የሰላማዊ ሰልፉ ተካፋይ እንደሚሆኑ ጠብቆ ነበር። ነገር ግን ብጹዕነታቸው ለሃገር፣ ለሃይማኖት፣ ለወገን እና ለቅርሶቻችን መጥፋት ተጨንቀው ድምጻቸውን ሊያሰሙ ከመጡት ኢትዮጵያውያን ጋር መሰለፍ ቀርቶ፣ በዚያው ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ ጽፈው
"ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተሳተፉት በሙሉ፥ ቤተክርስቲያንን የማይወክሉ ፖለቲከኞች ናቸው" ብለው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ ጽፈው ማስገባታቸውን ስንሰማ "ጆሮ የማይሰማው ጉድ የለም!" ብለን ብዙ ሙከራዎችን ለማድረግ ችለናል፣ ይልቁንም ደብዳቤውን ለማግኘት የዝግጅት ክፍላችን ሙከራዎችን እያደረገ ይገኛል፤ እንደደረሰን እናቀርበዋለን።