Friday, March 30, 2012
በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ምጥን ዘገባ (ክፍል አንድ)
ስ
በስሰባው የጎንደርን ካህናትና ምእመናን እንደማይወክል ተገለጸ፤
በስሰባው የጎንደርን ካህናትና ምእመናን እንደማይወክል ተገለጸ፤
“ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ”
(አቶ አያሌው ጎበዜ፤ የክልሉ ፕሬዚደንት)።
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 20/2004 ዓ.ም፤ ማርች 29/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ “የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት” በዋልድባ ገዳም ህልውና እና ክብር ላይ የጋረጠውን አደጋ በተመለከተ “የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ካህናትና ምእመናን የሚያነሡትን ሐሳብ ለመስማት” የሚል ስብሰባ ትናንት መጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ዐምባ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
Thursday, March 29, 2012
why Waldba is a target?
zwethiopia@gmail.com
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
በዋልድባ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዓለም አቀፍ ውይይቶች ቀጥለዋል
- ሰላማዊ ሰልፎች ማድረጉ ይቀጥላል።
- “ሥር ነቀል የምእመናን እንቅስቃሴ ነው የሚያስፈልገው” ከተሳታፊ ምእመን
- ምእመናን ለቤተ ክርስቲያናቸው መቆም ያለባቸው ጊዜ ላይ መደረሱ ተወስቷል፡፡
- “ሁላችሁንም በእግዚአብሔር ስም አንድ ነገር እለምናችኋለሁ። ከዘረኝነት ራሳችንን እናጽዳ። ዘር ለዱባና ለድንች እንጂ ሁላችን ከአንድ ከክርስቶስ ከማይጠፋው ዘር የተወለድን ነን”
በዋልድባ
እና በጠቅላላው የቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ የተቀሰቀሰው ቁጣ በሕዝባዊ ውይይቶች ታጅቦ እየቀጠለ መሆኑን የሰሜን አሜሪካ
ምንጮቻችን ገልጸዋል። በመላው የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በስልክ ኮንፈረንስ ሐሳባቸውን እንዲሰጡ እያደረገ ባለው
በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ የምእመናን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ስለ ዋልድባ ይዞታ መደፈር ወይም ስለ
ዝቋላ እና አሰቦት ገዳማት የእሳት አደጋ ብቻ ሳይሆን “በጠቅላላው ስለ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ነው መነጋገር ያለብን” ወደሚለው
ገዢ ሐሳብ በመምጣት ላይ ናቸው ተብሏል።
Wednesday, March 28, 2012
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዛሬ 6 ዓመት አካባቢ የተናገሩት
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ቀርበው የሰጡት ቃል፣ ዋሽንግተን አካባቢ ስላሉት ቤተክርስቲያናት የተናገሩት እና እውነት ይህ በእውነት ነው? ልብ ያለው ልብ ይበል።
" የዋሸንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በመንፈሳዊ አስተዳደር ከእናት ቤተክርስቲያን ጋራ አንድነት መስርቷዋል" ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
Tuesday, March 27, 2012
የዋልድባ ገዳም መብት ለማስከበረ በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
“የአባቶቻችን ርስት እና ቅርስ ተጠብቆ ለትውልድ ይተላለፍ” የሚል መሪ ቃል ያለው የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ የአሜሪካን መንግስት መቀመጫ በሆነችው
በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ መጋቢት17፣2004 ዓ/ም በአካባቢው የሰዓት አቆጣጠር 9am ላይ ተካሄዶዋል:: በአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፉ ላይበቦታው የተገኙ አባቶች በጸሎት አስጀምረዋል:: በሰልፉም ከአንድ ሺህ በላይ ክርስቲያኖች እንደተገኙ በአካባቢው የነበሩ ዘጋቢዎቻችን ገልጸውልናል:: በአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፉም በአስተዳደር ምክንያት የተለያዩ ወገኖች በአንድነት የቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚፈታተኑን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል:: ለአራት ሰዓታት ያህል የቆየው የአቤቶታው ሰልፍ በተለያዩ መዝሙራት የታጀበ ነበረ:: ተሳታፊዎቹም ጥያቄዎቻቸውን በእንባ እና በጩኸት ለኤምባሲው አሰምተዋል::
በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ መጋቢት17፣2004 ዓ/ም በአካባቢው የሰዓት አቆጣጠር 9am ላይ ተካሄዶዋል:: በአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፉ ላይበቦታው የተገኙ አባቶች በጸሎት አስጀምረዋል:: በሰልፉም ከአንድ ሺህ በላይ ክርስቲያኖች እንደተገኙ በአካባቢው የነበሩ ዘጋቢዎቻችን ገልጸውልናል:: በአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፉም በአስተዳደር ምክንያት የተለያዩ ወገኖች በአንድነት የቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚፈታተኑን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል:: ለአራት ሰዓታት ያህል የቆየው የአቤቶታው ሰልፍ በተለያዩ መዝሙራት የታጀበ ነበረ:: ተሳታፊዎቹም ጥያቄዎቻቸውን በእንባ እና በጩኸት ለኤምባሲው አሰምተዋል::
Sunday, March 25, 2012
መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ነገ march 26, 2012 ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊትለፊት
የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ! |
ዋልድባ ገዳም በሰሜን ኢትዮጵያ በቀድሞው የጎንደር ክፍለ ሀገር ወይም በአሁኑ በአማራና በትግራይ ክልሎች አዋሳኝ የሚገኝ በመጀመሪያ በኢየሱስ ክርስቶስ የስደት ዘመን በእርሱ በራሱ የተባረከና በኋላም በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በእርሱ በጌታ መሥራችነት የድንጋይ ቆብ ቀርጾ ባመነኮሳቸው መነኮሳት አፅናነት የተመሰረተ ታላቅና ታሪካዌ ገዳም ነው፡፡እመቤታችን ከልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመዋዕለ ስደት ወቅት በኪደተ እግር ከረገጧቸው መካናት አንዱ ሲሆን፣ የእመቤታችን ስም የሚያመሰግኑ ቅዱሳን እንደ አሸን የሚፈሉበት ቦታ መሆኑንም ለእመቤታችን ትንቢት የተናገረው እዚሁ ገዳም ነው፡፡
ይህ ገዳም በስፋቱ፣በመነኰሳት ብዛቱ፣በፍጹማን ባሕታውያን መሸሸጊያነቱ፣ ለስዉራን ቅዱሳን መናኸርያነቱ፣ በበረሃነቱና በመሳሰሉት ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ካሉት ገዳማት ታላቁ ገዳም ሲሆን፣ በዓለም ደረጃም ሲታይ ከግብጹ አስቄጥስ ገዳም ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ የቅዱሳን በአት ነው፡፡በአሁኑ ሰአት የተሰወሩ ቅዱሳንን ሳይጨምር ከ3000 በላይ መነኰሳት በቋሚነት ለመላው ዓለምና ለአገራቸው ቀን ከሌሊት ስብሐት ወአኮቴት ወደ አምላካቸው የሚያቀርቡበት ቦታ ነው፡፡
በዚህ ገዳም እልፍ አእላፍ የተሰወሩ መናንያን እንዳሉ በአንድ ወቅት የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ስለተሰወሩ መነኮሳት ተጠይቀው የሰጡትን መልስ ማንሳቱ በቂ ነው፡፡እንዲህ ነበር ያሉት፤ "ግብፅ ውስጥ የማይታወቅ (የተሰወረ) መነኩሴ በአሁኑ ጊዜ የለም፤ ኢትዮጵያ ብትሄዱ ግን ብዙ የተሰወሩ መናንያንን ታገኛላችሁ" ነበር ያሉት፡፡እነዚህ የዋልድባ መነኰሳት የሚመገቡት ጌታ የባረከላቸውን በቀን አንድ ጭብጥ ቋርፍ ሲሆን፣ የዓመት ልብሳቸውንም የሚሸፍኑት ከበጎ አድራጊ ምእመናን ከሚያገኙት ስጦታ ነው፡፡ ታዲያ በዓይን የማይታይ ምግብ ይሁን እንጂ ሰማያዊውን ምስጋና እየተመገቡ ፀባ አጋንንቱን፣ ግርማ አራዊቱን በተለይም አንድ ቀን ለመዋል እንኳ የሚከብደውን ያን ከባድ የበረሃ ዋዕይ ታግሰው ለራሳቸውና ለዓለም ድህነትን (ህ ይዋጣል) ሲለምኑ ኖረዋል ፣እየኖሩም ነው፣ይኖራሉም፡፡
የዋልድባ ገዳም እንዲህ በቀላሉ ዘርዝረን የማንጨርሰው ብዙ ታሪክና ቃልኪዳን ያለው ቦታ ነው፡፡ጌታም ዋልድባን "እህልና ኃጢያት አይሻገርብሽ"ብሎ ለመናንያን መጠጊያና የምስጋና ማቅረቢያ ቦታ እንድትሆን ምግባቸውም መራራው ጣፋጭ እንዲሆን በቦታው ተገኝቶ ባርኮላቸዋል፡፡በዚህም ምክንያት ላለፉት እስራ ምእት (2000 ዓመታት) ለገዳሙ መነኰሳት ምግብነት ከተፈቀደው የሙዝ ተክል ውጭ ምንም አይነት እህል መሬቱን ሳይደፍር ቃልኪዳኑ ተጠብቆ እስካሁን ቆይቷል፡፡
ይድረስ ለአቡነ ጳውሎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ይድረስ ለአባ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት
አባታችን ይህቺን ትንሽዬ ጦማር እከትብሎ ዘንድ ያነሳሳኝ “ሰሞኑን” በተከሰቱ ሁለት ዓበይት ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎች ስላሉኝ ጥያቄ ለመጠየቅና በጉዳዮቹ ዙሪያ የተሰማኝንና የታዘብኩትን ነገር ልነግሮት በመፈለጌ ነው:: ይህቺን ጦማር ስከትብሎ እርሶ ጋር ላይደርስ ይችላል የሚል ጥርጣሬና ሀሳብ አላደረብኝም:: እናም በአንድም ሆነ በሌላ እንደሚድርስዎት እርግጠኛ ስለሆንኩ የተሰማኝን ነገር ሳላስቀር እንዲህ ከትቤዋለሁ::ጉዳዮቹም ሰሞኑን ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተብሎ ስለሚነገረው ስለሶስቱ ታላላቅ ገዳማት: ማለትም ስለአሰቦት: ዝቋላ እና ዋልድባ ገዳማት በረከታቸው ይደርብንና ስለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሺኖዳ 3ኛ ዜና እረፍት ናቸው::
Subscribe to:
Posts (Atom)