Friday, January 27, 2012

አባ ፋኑኤል በዳላስ ቴክሳስ


ሥርዓት አልበኛው ጳጳስ አባ ፋኑኤል

በትላንትናው እለት አባ ፋኑኤል ወደ ዳላስ ቴክሳስ ጉዞ አድርገው ከካሊፎርኒያ እና የምዕራቡ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ እና  ለስብሰባው ከተገኙት የደብር ተወካዮች ጋር ንግግር ለማድረግ ትላንት አመሻሹ ላይ ዳላስ ቴክሳስ ገብተው አድረዋል። በደብረ ምሥራቅ አቡነ ተክለሃይማኖት ወአረጋዊ ቤተክርስቲያን የሚደረገው ይህ ከአቡኑ ጋር የሚደረገው ስብሰባ ምንም አይነት ውጤት እንደማያመጣ እና በደጋሚ የአቋም ለውጥ ካመጡ በሚል ቀቢጸ ተስፋ እንጂ ምንም የተለየ ነገር እንደማይጠብዙ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከቦታው ገልጸውልናል፥ በተለይ በቦታው የተገኙት የደብር ሃላፊዎች እና የሰበካ ጉባኤ አባላት አቡኑ ሀሳባቸው እንደ ሁልጊዜው ከሆነ በምንም መልኩ አብረዋቸው እንደማይሠሩ ከወዲሁ ሲነጋገሩበት የቆየ ቢሆንም አንድ ቁርጥ ውሳኔ ከአቡነ ፋኑኤል እንደሚጠብቁና ውጤት ሊያመጣ የሚችል ንግግር ካልሆነ ግን ስብሰባውን ጥለው ወደየመጡበት ሀገር እንደሚወጡ አስቀድመው አሳውቀዋል። ለዚህ ስብሰባ መጠራት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉት የዴንቨር ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ እንደሆኑ እና በባለፈው በ፴ኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወቅትም በብጹዕ አቡነ ኤውስጣቲዎስ እና በብጹዕ አቡነ አብርሃም ላይ ከሊቀ መምሕራን ቀሲስ አማረ ካሣዬ ጋር በመሆን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ አቤቱታ አቅርበው ለአባ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መምጣት አይነተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይታወሳል።

 በስብሰባው ላይ ብዙ ያልተገኙ አድባራት ተወካዮች ያልተገኙ ቢሆንም፥ የተገኙት ግን አባ ፋኑኤል በተለያየ ጊዜ የሚያደርሱትን የሥርዓተ ቤተክርስቲያን መጣስ እና የቀኖና ማፍረስ ሥራዎችን በመቃወም ነበር ስብሰባው የተጀመረው፤ ተሰብሳቢዎቹም የተለያየ የምስል እና የድምጽ መቅረጫዎችን እንዳይጠቀሙ ሊቀ ካህናት አጥብቀው ሲያሰሙ ስለነበር በተከታዮቹ ቀናት በተሰብሳቢዎቹ ካህናት እና የሰበካ ጉባኤ ተጠሪዎች ችግር ሳይገጥማቸው እንደማይቀር ይገመታል።
የስብሰባው ሙሉ ሪፓርት እንደደረሰን እናቀርባለን ተጠባበቁን። 
ቸር ወሬ ያሰማን

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

Thursday, January 26, 2012

ተሀድሶያውያን እንደ እባብ የሞተ በመምሰል አፈር ልሰው ለመነሳት እየሞከሩ ነው

 

ትዝታው እና አቶ በጋሻው

(አንድ አድርገን ጥር 16 ፤ 2004ዓ.ም)፡- እነዚህ ሰዎች በጥምቅቱ የሲኖዶስ ጉባኤ የታገዱ እና ህገወጥ የተባሉ ሰባኪያን እና ዘማሪያን መሰል የተኩላው ለምድ የለበሱ ሰዎች (አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፤ አሸናፊ ገ/ማሪያም ፤ አሰግድ ሳህሉ ፤ ትዝታው ሳሙኤል ፤ ምርትነሽ ጥላሁን ፤ ሀብታሙ ሽብሩ ፤ እና መሰሎቻቸው) በየትኛው በር ገብተው ነው የቤተክርስትያናችን አዳራሽ የተፈቀደላቸው ? እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከቅዱስ ሲኖዶስ የትኛውም አውደ ምህረት ላይም ሆነ የትኛውም ቤተክርስትያን ላይ የመስበክ ፍቃድ እንዳይሰጣቸው እና ቤተክርስትያንን የማይወክሉ መሆኑን ገልፆ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመላው አዲስ አበባ ውስጥም ላሉ ፤  ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ አብያተክርስያናት በሀገረስብከታቸው አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጎ ነበር ፤ ታዲያ ይህን ጉባዬ ለዛውም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ማን ፈቀደላቸው?

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም ድምጽ: አባ ፋኑኤል እና የሐሰት ስርጭታቸው

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም ድምጽ: አባ ፋኑኤል እና የሐሰት ስርጭታቸው: ባለፈው ቅዳሜ ጥር ፲፪ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. አባ ፋኑኤል በቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት በአቶ አዲሱ አበበ አማካኝነትክፍል አጭር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፣ በቃለ ምልልሱም በርካታ የሆኑ ውሸት አዘል መልዕክቶችን በአ...

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

Wednesday, January 25, 2012

ጸብአቴ የማነ ብርሃን ማናቸው?

በዚህ ሰሞን በአትላንታ ጆርጂያ እራሱን ገለልተኛ ብሎ የሚጠራው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቦርድ አባላትና የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የነበሩት ጸብአቴ የማነ ብርሃን ከረር ያለ ውዝግብ ምዕመናኑን ለሁለት ከመክፈሉ ባሻገር፥ የምዕመናንን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ነገር መፈጸሙን ስንሰማ፣ ከአካባቢው የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ሞክረን በጉዳዩ ተሳታፊ ከሆኑት ምዕማን ጋር ግንኙነት በማድረግ ስለተፈጠረው ሁኔታ እንዲያብራሩልን ጠይቀናቸው ሙሉ መረጃውን ሰጥተውናል። የእኛ አላማ አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓቷ፣ ቀኖናዋ፣ ትውፊቷ ተጠብቆ አገልግሎቱን መፈጸም ሲሆን አንዳንድ ጥቅም ዓይናቸውን ያሳወራቸውን አባት ተብዬዎች ግን፣ ዝም ብለን አናልፍም ሕዝበ ክርስቲያኑን ስለማንነታቸው በማሳወቅ መለየት። የበግ ለምድ ለብሰው በውስጣችን የገቡትን ነጣቂ ተኩላዎች ማውጣት የኛ አነሳስ ነው።

ከቦታው ሆነው የዘገቡልን ባልደረባችን እንደገለጹልን ጸብአቴ የማነ ብርሃን ወደ አሜሪካ ከመጡ ጀምሮ ቤተክርስቲያንን ከእናት ቤተክርስቲያን ለይተው ገለልተኛ በሚል ከአሁኑ አባ ፋኑኤል ከቀድሞው አባ መላኩ ጋር መክረው እና ቀምረው ሕዝበ ክርስቲያኑን እኛ ገለልተኞች ነን በሚል ከእናት ቤተክርስቲያኑ ለይተው ለራሳቸው እንዲመች ብቻ አድርገው የሕዝቡን ጥሪት ሲመዘብሩ እና ቤተክርስቲያኒቱን ተረካቢ ትውልድ ለማሳጣት ያደረጉት በደል እና ግፍ አልበቃ ብሎአቸው ዛሬ ደግሞ በተለየ መልኩ ሕዝቡን ሊከፋፍሉት እና ሊያምሱት ቆርጠው ተነስተዋል፤ በዚህም መሠረት ላለፉት አስርተ ዓመታት ሲያደርጉ የቆዩትን በጥቂቱ ለመዘርዘር እንሞክራለን፦

Monday, January 23, 2012

አባ ፋኑኤል እና የሐሰት ስርጭታቸው

ባለፈው ቅዳሜ ጥር ፲፪ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. አባ ፋኑኤል በቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት በአቶ አዲሱ አበበ  አማካኝነትክፍል አጭር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፣ በቃለ ምልልሱም በርካታ የሆኑ ውሸት አዘል መልዕክቶችን በአባው ተላልፈዋል ከነዚህም ቀንጠብ ቀንጠብ አድርገን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ በመቀጠል ጥያቄዎችን በተከታታይ እንመልከታቸው
ጥያቄ: አባታችን አሁን የመጡበት ሹመቶ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው?
መልስ፡ አዎ፣ ከዚህ በፊት መጥቼ ቅዱስ ፓትሪያሪኩንም ነግሬያቸው ነበር እኔ የመጣሁት ሀገሬን ለማገልገል ነው እና በተቻለ መጠን እዚሁ ቢያረጉኝ ብዬ ነበር ነገር ግን በቅዱ ሲኖዶስ ስለታዘዝኩኝ ትዕዛዙን አክብሬ መጥቻለሁ፣ በመቀጠም እራሴው ደብዳቤ ጽፌ ወዳገሬ እንዲመልሱኝ ያለምንም ችግር በመጣሁ በሦስት ወሬ ወዳገሬ ተመልሻለሁ ነበር ያሉት።
እርምት: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከዚህ በፊት በመጡበት ወቅት ትልቅ ችግር ተነስቶ እንደውም በቅዱስ ሚካኤል ደብር መቀመጥ እንደማይችሉ ተነግሯቸው፣ እንደዛ ከሆነ የቤቱ ባለቤት እራሴው ነኝ እስቲ የምታደርጉትን እናያለን ብለው ከጥቂት የቤተክርስቲያኑ አባላት ጋር አምባጓሮ ጀምረው በዛው ጊዜ የተጀመረው የፍርድ ቤት ክስ እስከ አሁን ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለሁለት ከፍሎት ይገኛል፣ ቤተክርስቲያኑንም ላላስፈላጊ የ$200000 ብር ወጪ ተዳርጓል ለምን ይሄን ሸሸጉ?
ሌላው በዚሁ በመጡበት ጊዜ በተለምዶ እራሳቸውን ገልልተኛ ብለው የሚጠሩ አብያተ ክርስቲያናት ስብስብ ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለንም ብለው በዛው ጊዜ ከገለልተኞች አንድነት የወጡበት እና ባይተዋር የተደረጉበት ጊዜ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

Thursday, January 19, 2012

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሳችህ አደረሰን

"በፍሰሐ ወበሰላም ወረደ ወልድ ውስተ ምጥማቃት"

እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን አሜን
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሰዎት
የዛሬ ፲፻፱፸፬ ዓ.ም. ዓመት አካባቢ የእግዚአብሔር አብ የባሕሪይ ልጅ የሆነው ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ወልደ እግዚአብሔር) በእደ ምጥምቁ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ ምስጢር በዮርዳኖስ ወንዝ  ተፈፀመ። ጥንት ነቢያት በትንቢት የተናገሩለት፣ ሱባኤ የተቆጠረለት እነኛ ደገግ ነብያት ሊያዩት ቢወዱም ነገር ግን እድሜ እረፍታቸው ገድቧቸው ሊያዩት አልታደሉም፥ ጥንት ነቢያት የተነበዩለት ጊዜው ደረሰና በይሁዳ፣ በራማ፣ አካባቢ ድምጽ ተሰማ ይህ ድምጽ  በገሊላ አውራጃና አካባቢው ኮረብታማ ሥፍራ ተራርቀው በሚኖሩ ከተሞች ሁሉ ደረሰ።
ይህን ድምጽ ሰምተው ምላሽ ለመስጠት ከቤታቸው የወጡ በግብርና የሚኖሩ፣ በባሕር የነበሩ አሳ አጥማጆች እንዲሁም በገዥው መደብ ስር በተለያየ ማዕረግ እና ስም የሚጠሩና የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ ነበሩ፤ በጥሪው ምክንያት ሁሉም በአንድ ሥፍራ ተሰብስበዋል ጥሪውም እንዲህ የሚል ነበር "የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፥ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ ተብሎ እንደ ተጻፈ ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለችው አገር ሁሉ መጣ። " ሉቃስ ፫ ፥ ፫ - ፮ ለዚህ ድምጽ ምንነትና ማንነት ለማየት እና ለመስማት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የወረደው ሕዝብ ስፍር ቁጥር አልነበረውም፥ ተናጋሪው ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ነገር ግን በበረሃ ሲኖር ከኅብረተሰቡ ተለየቶ የበረሃ ማር እና አንበጣ እየበላ በጸጋ ያደገው የካህኑ ዘካሪያስ ልጅ መጥምቁ ዮሐንስ ነበር።

Wednesday, January 11, 2012

የተዋሕዶ ቤተሰቦች ለምን?

በተደጋጋሚ ከተለያዩ የዝግጅታችን ተከታታዮች
  • የተዋሕዶ ቤተሰቦች ማናቸው?
  • የናንተ የጡመራ መድረክ ለምን አስፈለገ?
  • ለቤተክርስቲያን መቆማችሁን በምን እናውቃለን?
  • ዓላማችሁ ምንድነው? እና የመሳሰሉት ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ከአንባቢያን ስለመጡ ሙሉም ባይሆን በመጠኑ የመልሳሉ ያልናቸውን ነጥቦች ከዚህ በመቀጠል አስቀምጠናቸዋል እና ጥያቄያችሁን ወይም አስተያየታችሁን በተለመደው መልኩ በኢሜል ወይም በፊስ ቡክ ልታደርሱልን ትችላላችሁ፤ የቻልነውን መልሰን ያልቻልነውን ሊቃውንቱን ጠይቀን መልሶቻችሁን ለመስጠት ከወዲሁ ተዘጋጅተናል።
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለዘመናት ከውስጥም፣ ከውጪም በሚመጡ ወራሪዎች እና ሃይማኖት እና ትውፊት ለዋጮች ስትታመስ ኖራለች፤ ምንም እንኳ ቤተክርስቲያኒቱ በጠላቶቿም ሳይቀር "ስንዱ እመቤት" እየተባለች እስከመጠራት ብትደርስም ፈተናው በየደረጃው መስራቿ ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ በቅናት ተነሳስተው ከሰቀሉበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ በዘመናችን እስከተነሱት ሃይማኖት ለዋጮች፣ ትውፊት ከላሾች ድረስ በብዙ ተፈትናለች፥ ዲያብሎስም ፆሩን መወርወሩን አያቆምም በተክርስቲያንም በክርስቶስ ደም ጸንታ ትቆማለች፡፡ ለዘመናት የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ፤ቀኖናና ትውፊት ሲያስተላልፉ የነበሩ ሁለት አይና ሊቃውንትን በአብነት ት/ቤቶች ስታፈራ ኖራለች፡፡ ከዚህም በላይ ቤተክርስቲያኒቱ ራሷን የምታስተዳድርበት የራሷ የሆነ ሥርዓት ለሺህ ዓመታት የነበራት ሲሆን ይህም አንድነቷን በመጠበቅ ከፍተኛ ሚና ሲጫወት ኖሯል፡፡ በተጨማሪም ቤተክርስቲያኒቱ ለሀገሪቱ ዘመናዊ አስተዳደር፤ ቋንቋ፤ ባህል፣ ስነ-ጽሁፍ፣ ስነ-ስዕል እና ስነ-ህንፃ ወዘተ ከፍተኛ የልማት አስተዋጽኦ አድርጋለች፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ዘመናት ብዙ ፈተናዎችን ስትጋፈጥና በእግዚአብሄር እርዳታም ስትወጣ ኖራለች ከነዚህም ዋነኞቹ የዮዲት ጉዲት ጭፍጨፋ፣ የግራኝ መሃመድ ህንፃ ቤተክርስቲያንና ቅርስን የማውደም ዘመቻ እንዲሁም የነገስታት እና የመሪዎች የሀይማኖት ጥላች  አፄ ሱስዮስ በመካከለኛው ዘመን ያደረሱት በደል፣ የደርግ መንግስት የቤተክርስቲያኒቱን አንጡራ ሀብት መውረስ የመሳሰሉት በአብነት የሚጠቀሱ ፈተናዎች ናቸው፡፡

Thursday, January 5, 2012

ቤተ ክርስቲያናችን በሀገረ አሜሪካን በይበልጥ ውስብስብ የሆነ ችግር ውስጥ እየገባች ነው

ይህ ጽሁፍ አሐቲ ተዋሕዶ ከሚባል ፌስ ቡክ የተገኘ ነው፤ ይጠቅማል ብለን ስላሰብን እንደሚከተለው አቅርበነዋል መልካም ንባብ ይሁንልዎ።

ባለን መረጃ በሰሜን አሜሪካ በ26 ግዛቶች(እስቴቶች) ውስጥ 106 አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ:: በሁሉም  እስቴቶች ቢቆጠር የአጥቢያዎቹ ብዛት ከ106 በላይ ይሆናል ማለት ነው:: እነዚህ አጥቢያዎች ሁሉ በውጫዊ እና  በውስጣዊ ተጽኖዎች ምክንያት በፖለቲካ፣ በዘር እና በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች የተከፋፈሉ ናቸው:: በአስተዳደር መዋቅር  ደግሞ ስደተኛ ሲኖዶስ፣ ገለልተኛ፣ በግለሶዎች፣ እና በኢትዮጵያ ሲኖዶስ በማለት የተለያዩ ናቸው:: በአስተዳደር  ብቻ ሳይሆን በሃይማኖታዊ ሥርዓት ጭምር የተላያየ አቋም ያላቸው አጥቢያዎች አሉ:: ለምሳሌ እመቤታችን ቅድስት  ድንግል ማርያም የአዳም ኀጢአት ወርሳለች በማለት በግል የመሠረቱት አጥቢያቸው ውስጥ የሚያስተምሩ እነ አባ መዓዛ  በየነ እና ቀሲስ አስተራየ ጽጌ የሚጠቀሱ ናቸው:: እንዲሁም ደግሞ አንዳንድ አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት በይፋ  በኦርጋን መዘመር ተፈቅዶዋል በማለት ወደ መቅደሱ ኦርጋን አስገብተው የሚዘምሩ አሉ::

ይህ በአስተዳደር፣ በፖለቲካ፣ በዘር፣ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅም እና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተለያዩት አጥቢያዎች  እንዴት አንድነት ማምጣት ይቻላል? የተወጋገዙት የጳጳሳት መታረቅስ ይህንን ችግር ይፈታው ይሆን? ጊዜ ይፍታው  ተብሎስ የሚተው ጉዳይ ነውን? አሐቲ ተዋሕዶ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር ከተጠበቀ ለዚህም መዋቅር  መጠበቅ በጋራ ከሰራን አንድነት ይመጣል ብላ ታምናለች:: የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅሯ ከግንዱ ተለይቶ  እዚህ ሀገረ ቅርጫፎች ብቻቸውን ከተስፋፉ ወደፊት ከፕሮስቴንታንቶቹ የሚለየን ነገር አይኖርም የሚል ስጋት አለን::  የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው ብለንም እናምናለን::

Wednesday, January 4, 2012

የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሥራ አስፈጻሚ የብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን እንቅስቃሴ እየተቃወመ ነው


(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 24/2004 ዓ.ም፤ January 3/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ለዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ተመድበው ቢላኩም ሀ/ስብከቱን ማስተዳደር ያልጀመሩት አቡነ ፋኑኤልን በተመለከተ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ቀጥሎ ሀ/ስብከቱን እንዲያስተዳድር የተመረጠው ሥራ አስፈጻሚ “ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን” 1ኛ ቆሮ 14፡40 በሚል ርእስ ኅዳር 29 ቀን 2004 ዓ. ም ባወጣው መግለጫ በሀ/ስብከቱ ያለው ዋነኛ ችግር “የውስጥ የቤተ ክርስቲያን ፈተናና እና ችግር  የሆነው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በማክበርና ባለማክበር፤ እውነታን በመናገርና ባለመናገር፤ የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም በማስጠበቅና የግል ጥቅምን ከቤተ ክርስቲያን በማስቀደም፤ መዋቅርን በመጠበቅና ባለመጠበቅ፤ ጽኑ መንፈሳዊ አቋም በመያዝና ባለመያዝ መካከል” መሆኑን ጠቅሷል።


መግለጫው አክሎም “በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የምንገኝ አብያተ ክርስቲያናት እያሳሰበን የመጣው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ጠብቆና አስጠብቆ የመጓዝ ሁኔታ በመሆኑ በሀገረ ስብከታችን ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከዚህ ቀደም ያሳሰብን ቢሆንም፤ እውነት ሊደበቅ ስለማይገባ ያለውን እና ተጨባጭ የሆነውን ጉዳይ ለቅዱስ ሲኖዶስና ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በድጋሚ ማሳሰብ እንዳለብን በመረዳት ይህንን የአቋም መግለጫ አዘጋጅተናል” ብሏል።  

Tuesday, January 3, 2012

አክራሪ ሙስሊሞች የወራቤ ደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያንን ሊያቃጥሉ ሲሉ ተያዙ


‹‹ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያን ጸልዩ››

(አንድ አድርገን ታህሳስ 17 2004 ዓ.ም) ፡-የቤተክርስትያናችን ፈተና መልኩን እየቀየረ መጥቷል ፤ ፈተናችንም ከብዷል ፤ የዛሬ አንድ ወር ገደማ አክራሪ ሙስሊሞች የቅድስት አርሴማን ቤተክርስትያን ሲያቃጥሉብን ፤ ሀዘናችን ከልባችን ሳይወጣ ፤ መንግስትም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዞ ሄዶ ፍትህ ሳናገኝ ፤ ሌላ ትንኮሳ ተካሂዶብናል ፤ ፤ የሙስሊም ማህበረሰቦች ያሉበት አንዳንድ ቦታ ላይ ቤተክርስትያን መስራትም ሆነ በተሰሩት ላይ አምልኮተ እግዚአብሔር መፈፀም እየከበደ ነው፡፡

ሰበር ዜና - ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ


  • READ THIS ARTICLE IN PDF.
  • በየአህጉረ ስብከቱ ለሚፈጠሩት ችግሮች የአቡነ ጳውሎስ ግፊት እንዳለበት ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ
  • አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ፓትርያርኩ ያቀረቧቸው አጀንዳዎች “ለአስቸኳይ ስብሰባ የማይበቁ ናቸው” በሚል አጣጥሏቸዋል::
  • በፓትርያርኩ እልከኝነትና ተንኮል ላይ ያመረሩት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት “የቤቱ ችግር ተጣርቶ መወገዝ ያለበት ይወገዝ፤ ስለ ወንጌል አገልግሎት፣ መልካም አስተዳደር፣ ሰላም እና ልማት መነጋገር ሲገባን ቤተ ክርስቲያን በእርስዎ የተነሣ ስትበጠበጥ እና ስትናጥ መኖር የለባትም” በሚል አቡነ ጳውሎስን ሲገጹ እና ሲያስጠነቅቁ አርፍደዋል::
  • ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከሲዳማና ጌዲኦ ዞኖች አማሮና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት እንዲነሡ ‹በ15,000 ምእመናን ፊርማ› ቀርቧል የተባለው ‹አቤቱታ› ስድነት የተሞላበትና በአቡነ ጳውሎስ ግፊት የቀረበ የተሐድሶ መናፍቃን ሤራ መሆኑን ሲኖዶሱ ገልጧል፡፡ በሕገ ወጥ አድመኞች የቀረበውን ይህንኑ ስድ አቤቱታ በመቃወም 20,000 የሐዋሳ እና ዲላ ምእመና ያሰባሰቡት የተቃውሞ ፊርማ አቤቱታ ለሲኖዶሱ ጽ/ቤት ደርሷል::
  • አቡነ ጳውሎስ “ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም” የሚለውን ስመ ማዕርጋቸውን በመጠቀም በአኵስም ሀገረ ስብከት ላይ ሥልጣናቸውን የሚያጠናክር አጀንዳ አቅርበዋል፡፡ አጀንዳው አቡነ ጳውሎስ አስገነባዋለሁ ከሚሉት ሙዚዬም አገልግሎት ጋራ በተያያዘ አጠያያቂ ገጽታዎች እንዳሉበት ተነግሯል::

“ብትፈነዱ እንደ እኛ ካህን ጳጳስ አትሆኑም” አባ ፋኑኤል


  • “እኛን ከጠላችሁ ለምን ቤተ ክርስቲያን ትመጣላችሁ እዛው በየቤታችሁ መቅረት ትችላላችሁ”
  • “ብትፈነዱ እንደ እኛ ካህን ጳጳስ አትሆኑም”
  • “እኔ ተምሬ ዶክተር ፕሮፌሰር መሆን እችላለሁ እናንተ ግን ካህን ጳጳስ መሆን አትችሉም”
  • “ስትወለዱም ስትሞቱም ያለ እኛ አይሆንላችሁም የአህያ ሥጋ አደላችሁ አትጣሉም …”
  • “ማፈሪያ ማፈሪያዎች ናችሁ … ማፈሪያዎች”