(ሰበር ዜና) ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀን ከሥልጣናቸው አወረደ
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 18/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 29/2011, እዚህ ይጫኑ)፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወደል ሳሙኤል ዛሬ ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ ወሰነባቸው። ከሥልጣናቸው መነሣትችም ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በሚከሰሱበት ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ውጪ ነው የሚባለውን እምነታቸውን የሚመረምር አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴም ተሰይሟል። የኮሚቴው አባላትም ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣
ብፁዕ አቡነሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ናቸው።
አባ ሰረቀ ከሓላፊነታቸው እንዳይነሡ በጥብዓት ሲከራከሩላቸው የቆዩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይዘውት የነበረውን አቋም እንዲቀይሩ ወጣቱ በቅርቡ ያሳየውን ተቃውሞ የተረዳው መንግሥት ተጽዕኖ ሳያደርግ አልቀረም ተብሏል። መላው ኦርቶዶክሳዊ እና የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶው ቤተሰብ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እና ለቅ/ሲኖዶስ ያለውን አክብሮት በመግለጽ ላይ ይገኛል።