ዜናዎች




ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙ ቀደምት ዘገባዎችን ይመልከቱ











































-

-----------------------------------------------------------------------------------------------------------
  • በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ለማቋቋም ቅድመ ዝግጅት

     እየተደረገ ነው

  • የሚደራጀው የቱሪዝም መምሪያ አጎብኚውንና የጉዞ ወኪሉን ያስተባብራል
  • በግል አስጎብኚዎች የሚዘጋጀውን የኢየሩሳሌም ጉዞ በሓላፊነት ይመራል
  • በቱሪዝም ዘርፍ የቤተ ክርስቲያንን ፋይናንሳዊ አቅም ለማጠናከር ታቅዷል
  • ጥናቱ በኢየሩሳሌም ጉብኝት ባደረገው የልኡካን ቡድን እየተካሄደ ነው
  • የቡድኑ የኢየሩሳሌም ጉብኝት አቡነ ማቲያስን ለፕትርክና ለማግባባት እንደ ኾነ ተደርጎ መዘገቡን የልኡካኑ አባላት አስተባብለዋል
የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሀገር ውስጥና በውጭ አህጉረ ስብከት በተለይም በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ያሉ ገዳማትንና የቤተ
 ክርስቲያኒቱን የቱሪስት መስሕቦች የሚያስተዋውቅ የቱሪዝም መምሪያ ለመመሥረት በዝግጅት ላይ መኾኑን አስታወቀ፡፡ በመምሪያው ሥር መምሪያው
የሚያስተባብረው አስጎብኚ ድርጅት እና የጉዞ ወኪል ለማቋቋም የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ጥናት ለቅዱስ ሲኖዶስ መቅረቡ ተመልክቷል፡፡
ቤተ ክርስቲያን አስጎብኚ ድርጅትና የጉዞ ወኪል በማእከል ማደራጀቷ÷ ወደተለያዩ ቅዱሳት መካናት የሚደረጉ የምእመናን ጉዞዎችን በባለቤትነት ይዛ
ትምህርተ ሃይማኖቷን፣ ሥርዐተ እምነቷንና ክርስቲያናዊ ትውፊቷን በሚያስጠብቅ አኳኋን በሓላፊነት ለመምራት፣ በተሳላሚነት ስም የሚፈጸመውን ሕገ ወጥ
የሰዎች ዝውውር በመቆጣጠር ተመጣጣኝ ዋጋ እና በቂ ዋስትና ያለው አገልግሎት ለመስጠት፣ በአገልግሎቱ ከሚሰበሰበው ከፍተኛ ገቢ ሐዋርያዊ አገልግሎቷን
 ለማጠናከርና ለማስፋፋት የሚያስችል ፋይናንሳዊ አቅም ለማዳበር እንደሚያስችላት ተገልጧል፡፡
በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ለሚዲያ አካላት ባሰራጨው መግለጫው÷ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የምትሰጥባቸው
 ጥንታዊና ታሪካዊ ሀብቶቿ ከሚያስገኙት የቱሪዝም ገቢ የበይ ተመልካች ኾና በመቆየቷ በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ተቋማዊ አቅሟን ለማጠናከር መሥራት
የምትችልበት ጊዜው አሁን እንደኾነ አስታውቋል፡፡ በዋናው መሥሪያ ቤት ለማቋቋም በታቀደው የቱሪዝም መምሪያ የአስጎብኚ እና የጉዞ ወኪል ቢሮዎችን
ለመክፈት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ጥናት የተደረገ ሲኾን ጥናቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ መኾኑን መምሪያው በመግለጫው ላይ
አመልክቷል፡፡
የቅድመ ዝግጅት ጥናቱ በዋናነት የተደረገው ቤተ ክርስቲያናችን የቅዱሳት መካናት ይዞታ ካላቸው አገሮች ቀደምት ባለርስት በኾነችበት በእስራኤል – ቅድስት
ሀገር ኢየሩሳሌም ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የቅድስት ሀገር ይዞታዋን እንደ አንድ ሀ/ስብከት አደራጅታና አንድ ሊቀ ጳጳስ መድባ ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዙትን
 ምእመናን አቅሟ በፈቀደ መጠን ስታስተናግድና ተልእኮዋን ስትፈጽም መኖሯን ዘገባዎች ያስረዳሉ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ አንጋፋው የኢየሩሳሌም 
መታሰቢያ ድርጅት ተመሥርቶ በድርጅቱ አማካይነት ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዙ ምእመናን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲጨምር ተደርጓል፡፡ ቤተ
ክርስቲያናችንም ድርጅቱ ለሚያጓጉዛቸው ምእመናን በድርጅቱ ፈቃድና ወጭ አንድ አንድ ቡራኬ ሰጪ አባት በመላክና ተጓዦች ምእመናን በጸሎት በመሸኘት
ተወስና ቆይታለች፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ የግል አስጎብኚዎቹ ቁጥር (በሰሞኑ የዜና ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አንቀጽ አገላለጽ ‹‹በኢየሩሳሌም ታሪካውያን ስፍራዎች ቁጥር
ልክ››) እየበዛ መጥቷል፡፡ የዚያኑ ያህል በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ዐይነቱ ‹‹ቀራንዮ አስጎበኚና የጉዞ ወኪል›› በተሳላሚዎች ስም የሚጓዙ ግለሰቦች ሕገ ወጥ
 ዝውውር የሚያካሂዱበት መኾኑ መንፈሳዊ በረከትን ከማግኘት ጎን ለጎን ለቅዱሳት መካናት ይዞታችን የምእመኑ አለኝታነት የሚረጋገጥበት የእውነተኛ
ተሳላሚዎች ጉዞ እንዳይደናቀፍ ስጋት አሳድሯል፡፡ ለዚህም ሲባል የተሳላሚዎችን ዕድሜና የዋስትና ማስያዣዎችን መሠረት ያደረገ የጉዞ መስፈርት
የሚዘጋጅበት ኹኔታ ለዳሰሳ ጥናት ወደ ኢየሩሳሌም አምርቶ የነበረው ልኡክ ስለ ጥናቱ ለቅ/ሲኖዶስ ባቀረበው አጭር መግለጫ ላይ በመፍትሔ ሐሳብነት
ቀርቦ ተመልክቷል፡፡
በግል የተቋቋሙትን የቅድስት ሀገር አስጎብኚ ድርጅቶች በአንድ ማእከል ማስተባበር የቤተ ክርስቲያናችንን የገቢ ምንጭ ለማዳበር፣ ለተሳላሚ ምእመናን ክፍያ
 ለመቀነስና በጉዞ ላይ ለሚደርሰው ችግር ሁሉ በቂ ዋስትና ለመስጠት የተሻለ አማራጭ ኾኖ ተወስዷል፡፡ የቱሪዝም ማእከሉ ጠቀሜታ ለኢየሩሳሌም ብቻ
ሳይኾን የቱሪስት መናኸርያና ‹የወፍ አዕላፉ› ሁሉ መጠቀሚያ የኾኑትን በጣና ሐይቅ ዙሪያ የሚገኙትን ገዳማት፣ የአኵስምንና የላሊበላን ታሪካውያን ስፍራዎችና
 የመሳሰሉትን ‹‹በቁጥጥር ሥር ለማዋልና ለመዳኘት›› ያስችላል ተብሎ እንደሚታመን ተገልጧል፡፡
በቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የተመራው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከፍተኛ ሓላፊዎች የሚገኙበት የልኡካን ቡድን ከኅዳር 14 – 22 ቀን 2005
ዓ.ም የዳሰሳ ጥናቱ በተጀመረበት በኢየሩሳሌም ተገኝቶ ከገዳማቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቲያስና ከሚመለከታቸው አካላት ጋራ ተገናኝቶ ተወያይቷል፡፡
የልኡካኑን የሥራ ጉብኝት በማስተባበር የዳሰሳ ጥናቱን ካቀረቡት መካከል የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊው መምህር ሰሎሞን ቶልቻ እንደገለጹት÷ ከሊቀ
ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ጋራ በቱሪዝሙ ሀብቶቻችን ላይ ያተኰረና ለሁለት ሰዓት የዘለቀ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
ከዚህም ባሻገር ከገዳሙ ማኅበር ጋራ በገዳሙ ዋና መጋቢ አማካይነት ቤተ ክርስቲያናችን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስለምትከፍተው የቱሪዝም መምሪያ ምክክር
ተደርጓል፡፡ የልኡካኑ ውይይት በእስራኤል የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ የኾኑ አካላትንም ያካተተ እንደነበር መ/ር ሰሎሞን ቶልቻ ተናግረዋል፡፡
ከብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በተጨማሪ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንን በሚመለከት ሌላ የሥራ ጉብኝት በኢየሩሳሌም የነበሩት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ
 ሳሙኤል ከብፁዕ ዋና ጸሐፊው ጋራ አይሁዳውያን የሃይማኖት መሪዎችን ማነጋገራቸው ተዘግቧል፡፡ ንግግሩ ቤተ ክርስቲያናችን በስታተስኮው ምክንያት
የባለይዞታነት መብቷ ሳይከብር፣ ገዳማቷን ለማስፋፋትና ለማደስ ሳትችል ለዘመናት ተጨቁና በኖረችበት ኹኔታ ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጧል፡፡
አይሁዳውያኑ የሃይማኖት አባቶች በዚህ ረገድ ከቤተ ክርስቲያን ጋራ አብሮ ለመሥራት፣ ግንኙነቱን ለማጠናከርና ለማስፋፋትም የጋራ (የትብብር) ኮሚቴ
ለማቋቋምና የጉብኝት ልውውጥ ለማድረግ በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጧል፡፡
ቡድኑ ወደ ኢየሩሳሌም ከማምራቱ አስቀድሞ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅና ከልኡካኑ አንዱ በኾኑት አቶ ተስፋዬ ውብሸት መሪነት
በኢትዮጵያ የእስራኤል መንግሥት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ከኾኑት ወ/ሮ በላይነሽ ዛቫድያን ጋራ ውይይት መደረጉን ቀሲስ ሰሎሞን ቶልቻ አስታውቀዋል፤
 በውይይቱም አምባሳደሯ ቤተ ክርስቲያን በቱሪዝም ኢንዱስትሪው በምታከናውናቸው ተግባራት መንግሥታቸው አብሮ ለመሥራት ያለውን በጎ ፈቃድ
መግለጻቸው ተመልክቷል፡፡
በማእከል በሚቋቋመው የቱሪዝም መምሪያ አማካይነት በልደተ ክርስቶስ እና በትንሣኤ በዓላት ምእመናን ወደ ኢየሩሳሌም ለሚያደርጉት ጉዞ የኢትዮጵያ አየር
መንገድ አብሮ እንዲሠራ ቤተ ክርስቲያኒቱ መጠየቋን የመምሪያ ሓላፊው አስረድተዋል፤ በውጤቱም ቤተ ክርስቲያን ለምታደርገው የቱሪዝም እንቅስቃሴ አየር
 መንገዱ በሚበርባቸው ዓለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻዎች ሁሉ የቤተ ክርስቲያናችንን የቱሪስት መዳረሻዎች በማስተዋወቅ አብሮ እንደሚሠራ መግለጹ
 ታውቋል፡፡
የቱሪዝም መምሪያንና በሥሩም አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ማቋቋሙ በቀድሞው ፓትርያሪክ ዘመን የተወጠነ እንደነበር የገለጹት መ/ር ሰሎሞን÷ ውጥኑን
የሚያብራራ ባለ12 ገጽ የጥናት ምክረ ሐሳብ በጥቅምት ወር ለቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቀርቦ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ውብሸት፣ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊው
 አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ እንዲሁም የውጭ ግንኙነት መመሪያ ሓላፊው መ/ር ሰሎሞን ቶልቻ (የጥናቱ ምክረ ሐሳብ በቀረበበት ወቅት የገዳማት መምሪያ ሓላፊ ነበሩ) የተካተቱበትና በብፁዕ ዋና ጸሐፊው የተመራው የልኡካን ቡድን በኅዳር ወር አጋማሽ ወደ ኢየሩሳሌም ያመራውም በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ እና በብፁዕ ዋና ጸሐፊው ፈቃድ ለገዳማቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ እንዲሁም ለመንግሥት አካል በተጻፉት የድጋፍ ደብዳቤዎች እንደነበር ተረጋግጧል፡፡
እውነታው ይኸው ኾኖ ሳለ በአንዳንድ የጡመራ መድረኮችና ከጡመራ መድረኮቹ ገልብጠው በአገር ቤት ጽሑፎቻቸውን ባተሙ መጽሔቶች ላይ የልኡካን
ቡድኑ ወደ ኢየሩሳሌም ያደረገው ጉዞ ዓላማ÷ ብፁዕ አቡነ ማቲያስን ‹‹ለስድስተኛ ፓትርያሪክነት ሢመት ለማግባባት›› እንደነበር መዘገቡ ‹‹ከእውነት የራቀ፣
 የጉዞውን ዓላማም ይኹን ደረጃ እንደማይመጥን በሁሉም ዘንድ ሊታወቅ እንደሚገባው›› በመግለጽ የልኡካን ቡድኑ አባላት ዘገባውን አስተባብለዋል፡፡
በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ በተፈቀደው የልኡካን ቡድኑ የሥራ ጉብኝት መርሐ ግብር ውስጥ የተባለው ዘገባ እውነትነት እንደሌለው መገለጹ አንድ ነገር
ኾኖ÷ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ግን ስድስተኛው ፓትርያሪክ እንዲኾኑ የመንግሥትንና አንዳንድ የቅ/ሲኖዶሱን አባላት ድጋፍ ማግኘታቸው ሲገለጽ መቆየቱ
ይታወሳል፡፡



                   በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መሪነት ወደ እስራኤል የተጓዘው ልኡክ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረበ አጭር የጉዞ መግለጫ
ቤተ ክርስቲያን በዋናነት በያዘችው ሐዋርያዊ ተልእኮዋ የሰው ልጆችን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገቡና የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ለማድረግ
 ትተጋለች፡፡ ከዚህ የዕለት ከዕለት አገልግሎትዋ በተጨማሪ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ቀዳሚ በመሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት እየሠራች
ትገኛለች፡፡ ይኹን እንጂ በቱሪዝም ኢንዱስትሪ አልሠራችም፤ ተጠቃሚም አይደለችም፡፡ በአንጻሩ በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ መንግሥታዊ እና የግል ድርጅቶች
እንዲሁም ግለሰቦች በቤተ ክርስቲያኗ ስም በሚያገኙት የቱሪዝም ገቢ ከፍተኛ ተጠቃሚዎች ኾነዋል፡፡
ከአገራችን ተጠቃሽ የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል አብዛኛውን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች በአደራ እና በባለቤትነት ይዛና ጠብቃ የምታገለግለው የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ይኹን እንጂ ከዚህ አትራፊና ምንም ወጪ ከሌለበት ኢንዱስትሪ የበይ ተመልካች ከመኾን በቀር የሚፈለገውን ያህል
 ተጠቃሚ አልኾነችም፡፡ ይህ ዐይነቱ አሠራር እየቀጠለ ከሄደ በገንዘብ ደረጃ ከምታጣው ጥቅም በላይ ቀኖናዋን፣ ትውፊቷንና አስተምህሮዋን እየሸረሸረ መሄዱ
 ስለማይቀር ቅዱስ ሲኖዶስ የቱሪዝምን ጠቀሜታና አስፈላጊነት ተመልክቶ፣ ከዚህ ቀደም ለቱሪዝሙ ከተሰጠው ትኩረት በላይ አጽንዖት ሰጥቶ ውሳኔ
ሊያሳልፍበት፣ መመሪያ ሊሰጥበት ይገባል፡፡ ለዚህም መነሻ ይኾን ዘንድ የጥናት ዳሰሳ አስፈልጓል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን በጥንታዊነቷ፣ በረዥም ዘመን አገልግሎቷ፣ በውስጧ በያዘቻቸው በርካታ ቅርሶችና የቅድስና ሥፍራዎች ከማንኛውም አካል በፊት
 ከኢንዱስትሪው ተጠቃሚ ትኾን ዘንድ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ የቱሪዝም መምሪያ በቤተ ክርስቲያናችን በዋናው መ/ቤት በኩል ቢከፈት የቤተ
ክርስቲያናችን ትውፊትና ክብር ከማስጠበቁም በላይ ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለአገራችን ያለው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የላቀ ነው፡፡ ይህም፡-
  • ዘርፉ በሚያስገኘው ከፍተኛ ገቢ ቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎቷን ታጠናክራለች፡፡
  • ቤተ ክርስቲያናችን በራሷ የቱሪዝም ክፍል አገልግሎት እየሰጠች እምነቷን፣ ሥርዐቷንና የአበውን አስተምህሮ ትጠብቃለች፤ 
  • ታስጠብቃለች፡፡
  • ለበርካታ የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡
  • ሕጋዊና ዘመናዊ አሠራርን በማጠናከር አገራዊ የልማት ተሳትፎዋን ያጎላዋል፡፡
ከዚህ አኳያ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስፖንሰር አድራጊነት ከኅዳር 14 – 22 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ እስራኤል የተጓዘውና በቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ
አቡነ ሕዝቅኤል የተመራው ልኡክ፣ ቤተ ክርስቲያናችን በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ያላትን ተሳትፎ የሚያጠናክር ጥናታዊ ዳሰሳ አካሂዷል፤ ጥናታዊ ዳሰሳውን
 በተመለከተም ልኡኩ ለቅ/ሲኖዶስ መግለጫ አቅርቧል፡፡
ቅ/ሲኖዶስ ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለያዩ ሰብሰባዎች በቱሪዝም ጉዳይ ውሳኔዎች ቢያሳልፍም ውሳኔው ተግባራዊ አልኾነም፡፡ አሁን ግን በቱሪዝሙ ዘርፍ
ባለድርሻ ከኾኑት አካላት፡-
  • ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
  • ከኢትዮጵያ አየር መንገድ
  • ከእስራኤል ኤምባሲ
እንዲሁም ከሌሎች በዘርፉ ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር በተደረገ ምክክር የቤተ ክርስቲያናችንን ራእይ በመደገፍ በቱሪዝሙ አብሮ ለመሥራት ከፍተኛ በጎ
ፈቃድ ተገኝቷል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቤተ ክርስቲያን ለምታደርገው የቱሪዝም እንቅስቃሴ አየር መንገዱ በሚበርባቸው ዓለም አቀፍ
 የቱሪስት መዳረሻዎች ሁሉ የቤተ ክርስቲያናችንን የቱሪስት መዳረሻዎች በማስተዋወቅ አብሮ እንደሚሠራ ቃል ገብቶልናል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የቤተ ክርስቲያናችን የቱሪዝም አስጎብኚና የጉዞ ወኪልበቅዱስ ሲኖዶስ
 መልካም ፈቃድ ሲጸድቅና ሲከፈት በጠቅላይ ቤተ ክህነት በመምሪያ ደረጃ የቱሪዝም መምሪያ ተብሎ እንዲዋቀር ይደርጋል፡፡ መምሪያው በሀገሪቱ የቱሪዝም
ሕግና የንግድ ሥርዐት በአገልግሎት ሰጪነት እንዲከፈትና እንዲሠራ ይደረጋል፡፡ ይህም ሥራ ሲጀመር የቱሪዝም ክፍሉ ሁለት ክፍሎች ይኖሩታል፡፡ እሊህም፡-

  • አስጎብኚ (ቱሪስት አስጎብኚ)፣
  • የጉዞ ወኪል (የትኬት ቢሮ) ናቸው፡፡
ቱሪስት አስጎብኚው÷ የቱሪስት ማስጎብኘት ሥራ ይሠራል፡፡ የጉዞ ወኪሉ ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮች፣ አባቶች እና ምእመናን ወደ ውጭ ጉዞ
 ሲያደርጉ የአየር ትኬት ይቆርጣል፤ የትኬት ቢሮ ይኖራል፡፡ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን ለተለያየ ተልእኮ እስከ ዛሬ ከሌላ ትኬት ኤጀንሲ ይቆረጥ
 የነበረው ቀርቶ ከራሷ ቱሪዝም መምሪያ የትኬት ኤጀንት ቢሮ ትኬት በመቁረጥና ኮሚሽኑን ገቢ በማድረግ ከቱሪዝም ከሚገኘው ገንዘብ ባላነሰ ከአየር
መንገድ የትኬት ኮሚሽን ተጠቃሚ ትኾናለች፡፡
የቱሪዝም መምሪያው የሰው ኀይልና የቢሮ አደረጃጀት
የቱሪዝም መምሪያው በታቀደለት ዓላማ ሙሉ ሥራውን ለመጀመር የተሟላ የሰው ኀይል አደረጃጀት ሊኖረው ይገባል፡፡ በቅድሚያ መምሪያውን በመምሪያ
ደረጃ እንዲዋቀርና የመምሪያ ሓላፊ እንዲኖረው ማድረግ፣ በቀጣይ ባለሞያዎችን እንደ አስፈላጊነቱ መመደብ፡፡ የቱሪዝም መምሪያው ሁለት ክፍል ቢሮዎች
ከሙሉ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች ጋራ በማሟላት ሥራ እንዲጀምር ይደረጋል፡፡
ፈቃድ አደረጃጀት
የቱሪዝም መምሪያው በቅዱስ ሲኖዶስ ተፈቅዶ ሲጸድቅ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በመምሪያ ደረጃ ይዋቀርና በሀገሪቱ የንግድና የቱሪዝም ሕግና ደንብ መሠረት
 እንዲቀጥል አስፈላጊው ፎርማሊቲ እንዲያሟላ ይደረጋል፤ ሂደቱም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት በሚያደርገው የቅርብ ክትትልና በሚሰጠው መመሪያ
 ይከናወናል፡፡
ልኡኩ በእስራኤል ጉዞው ስለ ቱሪዝም የተመለከተው
እንደሚታወቀው ሁሉ ቱሪዝም የሰው ልጆችን በቋንቋ፣ ባህል፣ አኗኗር፣ በሃይማኖት፣ በታሪክ የሚያስተሳስር ምንም ወጪ የሌለበት ትርፋማ ኢንዱስትሪ ነው፡፡
 ማእከለ ምድር ተብላ የምትታወቀው ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከበርካታ ዘመናት ጀምሮ የንግድና የዓለም አቀፍ ቱሪዝም ማእከል ኾና ቆይታለች፡፡
በኢየሩሳሌምና አካባቢዎቹ ያሉትን የቅድስና ቦታዎች በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቱሪስት ይጐበኟቸዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ ቱሪዝም በእስራኤል በከፍተኛ ኹኔታ
 አድጓል፡፡ ሀገሪቱ በዚህ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ገቢዋ እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡
ከኢትዮጵያ በተለይም በዓመት ሁለት ጊዜ በልደተ ክርስቶስ እና በትንሣኤ በዓላት በርካታ አባቶችና ምእመናን ቅድስት አገርን ለመሳለምና ለመጐብኘት
 በተለያዩ የግል አስጐብኚዎችና በተለይም በኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት አማካይነት እንደሚጓዙ ይታወቃል፡፡ በሌላ መልኩ በየዓመቱ ከ50 ሺሕ ያላነሱ
 እስራኤላዊ አይሁዳውያንና በትውልድ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤሎች ጎብኚዎች ኢትዮጵያን ይጐበኛሉ፡፡ በመኾኑም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው
ጥንታዊና ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ ዳብሮ በቱሪዝም እየተሳሰሩ ይገኛል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን በዋናው መ/ቤት በኩል የቱሪዝም አገልግሎትን ብታስፋፋ በተለይም ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌምን በዓመት ሁለት ጊዜ በልደትና በትንሣኤ
በዓላት በማስጐብኘት ሐዋርያዊ አገልግሎቷን የሚያጠናክር በሚልዮን የሚቆጠር ገቢ እንደሚያስገኝላት ልኡኩ አረጋግጧል፡፡ በዚህም ፋይናንሳዊ አቅሟን
በማጎልበት መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶቿን ታስፋፋበታለች፤ ታጠናክርበታለች፡፡ ከዚህም ባሻገር፡-
  • ቤተ ክርስቲያናችን ከምታገኘው ከፍተኛ ገቢ በተጨማሪ ለተሳላሚዎችና ጎብኚዎች በሚሰጠው ያልተከለሰ የታሪክና የትውፊት
  •  ማብራሪያ ምእመኖቿን ታገለግላለች፡፡
  • በተሳላሚነት ስም የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን ነን እያሉ በፖለቲካ ስደተኝነት ስም የሚቀሩ ዜጐችን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡
  • በተለያዩ የግል አስጐብዎች በምእመናን ስም እየሄዱ በዚያው በመቅረት ካለ ፈቃድ በሚኖሩ ሕገ ወጥ ስደተኞች የተነሣ የእስራኤል
  •  መንግሥት በገዳማችን ላይ የሚያሳድረውን ጥላቻ ያስወግዳል፡፡
  • ቤተ ክርስቲያናችን በቱሪዝም ዘርፉ ላይ በመሥራት ሀገራዊ የልማት ተሳትፎዋን ትገልጽበታለች፡፡


  • ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች
እንደ ልኡኩ ምልከታ ቤተ ክርስቲያናችን ቱሪዝምን በዋናው መ/ቤት በመምሪያ ደረጃ በመክፈቷ በእጅጉ ትጠቀማለች እንጂ ምንም ተጐጂ አያደርጋትም፡፡
ይኹን እንጂ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በዓመት ሁለት ጊዜ በሚደረገው የመሳለም መንፈሳዊ ጉዞ አጋጣሚውን ተጠቅመው በዚያው የሚቀሩ ተሳላሚዎች
 እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በመኾኑም የጉዞውን ዓላማ ለመጠበቅና በዚህም ሳቢያ ከሚመጣው ዕንቅፋት ለመጠበቅ መፍትሔ ማበጀት ይገባል፡፡
የመፍትሔ ሐሳቦች
ከላይ የተገለጹትን ችግሮች ለመፍታት ልኡኩ አማራጭ የመፍትሔ ሐሳቦችን አስቀምጧል፡፡ ይህም በሚደረገው ጉዞ፡-
  • ለተጓዡ የዕድሜ መነሻ በመገደብ ከ50 ዓመት በላይ እንዲኾን ማድረግ፤
  • ከኀምሳ ዓመት በታች ለኾነ ተጓዥ በቂ የማስያዣ ገንዘብ እንዲሁም የማይንቀሳቀስ ንብረት በዋስትና እንዲያሲዝ ማድረግ ችግሩን
  •  ለመቅረፍ ያስችላሉ፡፡

  • የቱሪዝሙ ክፍል ሌሎች ጠቀሜታ
ይህ የቱሪዝም መምሪያ እያደገና እየተስፋፋ ሲሄድ በሀገር ውስጥ ያሉ ጎብኚዎችን እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ውጪ በመላው ዓለም የሚገኙ ዓለም አቀፍ
 ቱሪስቶች በአስጐብኚነት እያመጣ ሀገሪቱንና ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያብስጐበኝ ይኾናል፡፡ በቅድሚያ ግን የበይ ተመልካች ኾና ያሳለፈችው ዘመን በቅቶ
 በኢየሩሳሌም ጉብኝት ተጠቃሚ እንድትኾን ማስቻል ነው፡፡ ልኡኩ በእስራኤል ቆይታው ምእመናን በኢየሩሳሌም የአጭር ቀናት የመሳለምና የጉብኝት
 ቆይታቸው ከገበያ እና አልባሌ ጉዳዮች ይልቅ ሃይማኖታዊ የቅድስና መካናትን መጎብኘት ያስፈልጋቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲናችንን እምነት፣ ሥርዐት፣ ታሪክና
 ትውፊት ጠብቆ የሚያስጐበኝ ባለሞያ በመመደብ ካሉት አስጐብኚ ድርጅቶች በላቀና በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት ለመስጠት ስለሚቻልበት ኹኔታ ልኡኩ
አጽንዖት ሰጥቶበታል፡፡











































 “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን”
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤያወጣውን
 መግለጫ አስመልክቶ ከአዲስአበባ የመጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ልኡካንለሰጡት መግለጫ ከሰላምና አንድነትጉባኤው የተሰጠ ማብራሪያ
 ጥር 3 ቀን 2005 ዓ/ም (January 11/2013)
READ THIS FILE IN PDF
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንየሰላምና አንድነት ጉባኤ ታኅሣሥ 12 ቀን 2005ዓ.ም ወቅታዊውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይአስመልክቶ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫውንእንዲያወጣ ያስገደደው ዋነኘው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስሲኖዶስ ለዕርቀ ሰላሙ ድርድር የላካቸው የሰላም ልዑካን ሳይመለሱና በዳላስ፤ ቴክሳስ የተደረገውንየሦስተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት ሪፓርት ሳያቀርቡ በአዲስ አበባ በኩል ስድስተኛ ፓትርያርክለመምረጥ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙ በመሰማቱ እንደነበር ይታወቃል።


በመሠረቱ የሰላምና አንድነት ጉባኤ ይህ ዓይነቱ ሁኔታ እንዳይፈጠር ከወዲሁ በማሰብ በጥቅምት ወርበተካሔደው ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስለ ፓትርያርክ የምርጫ ሕግ ረቂቅ አስመልክቶ ውይይት ስለሚደረግበትና አስመራጭ ኮሚቴ ስለሚሰየምበት ሁኔታ ለኅዳር 30 ቀን 2005ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ  ስብሰባ እንደተጠራ በኢትዮጵያ ያሉት አባቶቻችን በሰጡት መግለጫ ላይ ባየ ጊዜ ጉዳዩ አሳስቦት ወዲያውኑ ሁኔታውን ደብዳቤ ጠይቆ ነበር። ይኸውም ጥቅምት 28 ቀን 2005ዓ.ም (Nov. 6/2012) በቁጥር 066///2012 በተጻፈ ደብዳቤያችን ላይ 3ኛው የዕርቀ ሰላም ንግግር የሚጠናቀቀው ገና ኅዳር 30 ቀን 2005 ዓ.ም በመሆኑ የሰላሙ ሒደት ቅድሚያ ተሰጥቶት ከአንድደረጃ ላይ ሳይደርስ በስድስተኛው ፓትርያርክ ሢመት ዙሪያ የሚደረጉ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ለሰላሙ እንቅፋት እንዳይሆኑ በማሳሰብ ጥያቄያችንን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርበን ነበር።

ይሁንና የፈራነው ነገር አልቀረም። ይኸውም ልዑካኑ ወደ አዲስ አበባ ሳይመለሱ አስመራጭ ኮሚቴበመሰየሙ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት በከፍተኛ ጉጉት የሚናፍቀውን ሕዝበክርስቲያንና ለዚህም ስኬታማነት በእጅጉ የሚደክሙትን የሰላምና አንድነት ጉባኤ አባላት በእጅጉአስደንግጧል። በመሠረቱ ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ያሳሰበው እኛን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባላት ብቻአልነበረም። ይልቁንም ከኢትዮጵያ የመጡት የሰላም ልዑካን በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ሊቀ ጳጳሳአማካይነት በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ይህ ዓይነቱ አድራጎት “ይሆናል ብለን አናምንም፤ ሆኖ ከተገኘ ግንበጣም እንቃወመዋለን” ማለታቸውን ስንሰማ ከዚህም ጋር ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በተመሳሳይ መልኩ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ላይ የተወሳው የፓትርያርክ የምርጫ ሕግ ታይቶ ስለሚጸድቅበት ሁኔታ እንጂ ስለ ስድስተኛ ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየም አስመልክቶ ውሳኔ አለመሰጠቱን አውስተው አሁንም ቅዱስ ሲኖዶስ ሁኔታውን እንደገና በማጤን ሊመለከተው እንደሚገባ ሲገልጹ የሰላሙ በር እንዳልተዘጋ ተገንዝበናል ስለሆነም ብዙ የተደከመበትንና በመልካም ሒደት ላይ የሚገኘውን ሰላም በርእንዳይዘጋበት በመስጋቱ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ኃዘኑንና ስጋቱን ለመግለጽ መግለጫ ለማውጣትተገዷል።

በመሠረቱ የሰላምና አንድነት ጉባኤ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት በአዲስ አባባ በኩል የተከሰተውንሁኔታ በተመለከተ ለማጣራት ከኢትዮጵያ የመጡትን የቅዱስ ሲኖዶስ ልዑካን ለማነጋገር ሞክሮ ነበር። ይልቁንም በልዑካኑ ጸሐፊ በንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ በኩል ጥያቄ አቅርቦ ለጥያቄው ተገቢውን መልስባለማግኘቱና የጉዳዩንም አሳሳቢነት በመገንዘብ ለሃያ አንድ ዓመታት የቆየው የቤተ ክርስቲያናችን ችግርበውይይት ከመፈታቱ በፊት ለሰላሙ እንቅፋት የሚሆኑ ማናቸውም ነገሮች እንዳይደረጉ ለመጠየቅና ለማሳሰብ ጉባኤው ተስማምቶ መግለጫ አውጥቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኢትዮጵያ የመጡትልዑካን ታኅሣስ 13 ቀን 2005 ዓ.ም በተጻፈ መግለጫ የሰላምና አንድነት ጉባኤ አባላትን ወቅሰውናተችተው አግባብነት የሌለው መግለጫ ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለተነሣበት የሰላም አጀንዳ ቅድሚያ በመስጠት በሦስተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ንግግር ወቅት ከልዑካኑ በቀረበለት ጥያቄና ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በተሰጠው መመሪያ መሠረት በዳላስ፤ ቴክሳስ የተካሔደውን የዕርቀ ሰላም ውይይት አጠቃላይ ገጽታ ለማስረዳትና በተያያዘ መልኩ ጉባኤው በቅርቡ ያወጣውን ወቅታዊ መግለጫና በአንጻሩ ደግሞ ከኢትዮጵያ ልዑካን የተሰጠውን የአጸፋ መግለጫ ለማብራራት፤ እንዲሁም ስለ ዓራተኛው የዕርቀ ሰላም ጉባኤ ቅድመ ዝግጅትም አስፈላጊ ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ተገቢውን የማግባባት ሥራዎች ለመሥራት ሁለት ልዑካንን ማለትም ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዓለማየሁንና መምህር አንዱዓለም ዳግማዊን በአንድ ድምፅ ሰይሞ ልኳል።

ይሁን እንጂ ልዑካኑ ዐቃቤ መንበሩም ሆኑ የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊና የመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ሳያውቁ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ግቢ እንዳይገቡ ከመደረጉም በላይ የጉባኤው ልዑክ የሆኑት ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ፍጹም ሰላማዊ ሰው መሆናቸው እየታወቀ፣ የሰላምና አንድነት ጉባኤ ልዑክ ሆነው በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለሱ መቆየታቸው ግልጽ ሆኖ ሳለ ባልታወቀ ምክንያት በቦሌ ኢሚግሬሽን ባለ ሥልጣን አስቸኳይ የስልክ ጥሪ አማካይነት ተልዕኳቸውን ሳይፈጽሙ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ተገደው ከአገር እንዲወጡ መደረጉና ሌላው ልዑክ መምህር አንዱዓለም ዳግማዊም በደረሰባቸው መጉላላት የሰላምና አንድነት ጉባኤው በእጅጉ አዝኗል። ይህ ጉዳይ በመላው ዓለም የሚገኙ ካህናትንና ምእመናንንም በእጅጉ አሳዝኗል። ይህ በዚህ እንዳለ መምህር አንዱዓለም ዳግማዊ ወደ አሜሪካ በተመለሱ ማግሥት በመንበረ ፓትርያርኩ ግቢ ወረቀት በትነዋል በሚል በሐሰት የተቀናበረ ጽሑፍ በማዘጋጀት መልካም ስማቸውን የሚያጎድፍና የሰላም ተልዕኳቸውን የሚያደናቅፍ ፍጹም አሳፋሪና ኢ-ክርስቲያናዊ ድርጊት መከናወኑንም የሰላምና አንድነት ጉባኤው በቅርቡ ለመረዳት ችሏል።  ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲህ ዓይነቱን ተግባር በቀላሉ ሊያልፈው የማይገባበመሆኑ ሁኔታውንም በቅርብ ተከታትሎ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር አስቸኳይ እልባት እንዲሰጠው  ይደረግ ዘንድ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰላምና አንድነት ጉባኤ ይጠይቃል

በዚህ አጋጣሚ የሰላምና አንድነት ጉባኤውን ድካምና ያላሰለሰ ጥረት ዋጋ በመስጠት መምህር አንዱዓለም ዳግማዊ ወደ አሜሪካ በሚመለሱበት ዕለት ወደ መንበረ ፓትርያርኩ መጥተው ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተላኩትን መልእክት እንዲያቀርቡና ለጉባኤው መልስ ይዘው እንዲመለሱ ከፍተኛ ትብብር ያደረጉትን ዐቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤልንና የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልን ከልብ ያመሰግናል። እንዲሁም በመልካም ሒደት ላይ ያለውን የዕርቀ ሰላም ጥረት ከፍጻሜ ለማድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉትንና በማድረግ ላይ የሚገኙትንና የሰላም ልዑካን የሆኑትን ብፁዓን አባቶችና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጉባኤው ልባዊ ምስጋና ያቀርባል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባዔ ዓላማው ቤተ ክርስቲያንንአንድ ማድረግ ነው። ስለሆነም ዋነኛ ግቡ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ማየት ነው። አቋሙምበኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገር የሚገኙትን አባቶች በአክብሮትና በእኩልነት በማየት ለቤተ ክርስቲያንሰላምና አንድነት ተግቶ መሥራት ነው። በአንጻሩ ደግሞ ለሰላሙ ሒደት እንቅፋት የሚሆኑ ማናቸውምነገሮች ሲፈጠሩ  ተገቢውን ማሳሰቢያ ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ያቀርባል። ስለዚህም በሰላምና አንድነት ጉባኤው በቅርቡ የተሰጠው ወቅታዊ መግለጫ ለድፍረት ሳይሆን በዕርቀ ሰላሙ ላይ የተፈጠረውን ስጋት በአግባቡ ለመግለጥና ከወዲሁም ለማሳሰብ መሆኑን ሁሉም እንዲገነዘብይፈልጋል።

ከላይ እንደገለጥነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ወደ ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሞ በላካቸው ሁለት ልዑካን አማካይነት የላከው መልእክት ሊደርስ ባለመቻሉ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ለመላው ካህናትና ምእመናን በያሉበት ስለ ጉባኤው ወቅታዊ መግለጫ ተገቢነትና ሚዛናዊነት ለማስረዳት እንዲሁም ከኢትዮጵያ የመጡት የሰላም ልዑካን አላግባብላስተላለፉት መግለጫ ከዚህ በታች የሚከተለውን ማብራሪያ  የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለመስጠትተገዷል።

1ኛየሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት የሚዳፈር ነውየሚለውን በተመለከተ

ከኢትዮጵያ የመጡ ልዑካን የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው በማለት ያለአግባብ ተችተዋል። በመሠረቱ የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ የወጣውየቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት ለመዳፈር አይደለም። ለአባቶቻችንና ለቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም ፍቅርና አክብሮት ባይኖረን እኮ የተለያዩትን አባቶች አንድ ለማድረግ ማንም ሳያስገድደን ላለፉት ሦስትዓመታት ባልደከምንም ነበር። ይልቁንም በቤተ ክርስቲያናችን ያለው ልዩነት ተወግዶ በአንድ መንበር፣ በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ የምትመራ አንዲት ቤተ ክርስቲያን እንድትኖር ያላሰለሰ ጥረት የምናደርገውም ለዚህ ነው። ይህንንም ከልዑካኑ የተሻለ የሚረዳ አካል ያለ አይመስለንም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ማንኛውንም የሰላምና አንድነት እንቅፋትለማስወገድና የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት ለማየት በመጓጓት ሁለቱንም አካላት በእኩልነትበማየት ለማገናኘትና ለማስማማት ዘወትር ተግቶ ከመሥራት በቀር ሌላ ዓላማና ተልእኮ የሌለው መሆኑን ለሚመለከተው ሁሉ በአጽንዖት ለመግለጽ እንወዳለን። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት የተዳፈረው የልዑካኑ ጸሐፊ በልዑካኑ ስም ያወጡት መግለጫ ነው። ምክንያቱም 1ኛ) የግል ሐሳባቸውን ብቻ የገለጡበትን መግለጫ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ . . . ያወጣው መግለጫ” በማለት ራሳቸውን በቅዱስ ሲኖዶስ ቦታ ተክተው ከቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ መግለጫ በማውጣታቸው፤ 2ኛ) ልዑካኑ ወደ ላካቸው አካል ሔደው ሪፓርት ሳያቀርቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሙሉ ፈቃድና ዕውቅና በሚሠራው የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ አማካኝነት ለመደራደር ፈቃደኛ እንደማይሆኑ አላግባብ መወሰናቸው፤ 3ኛ) በጋራ መግለጫቸው አክብረው ያመሰገኑትን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በማግሥቱ ቃላቸውን ለውጠው በመተቸታቸው የላካቸውን አካል ቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት የተዳፈሩት የልዑካኑ ጸሐፊና መግለጫቸው መሆናቸውን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።

2የሰላምና አንድነት ጉባኤውን ሚዛናዊ ሥራ በተመለከተ
ልዑካኑ ባወጡት መግለጫ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ሚዛናዊነት የጎደለው ነው በማለት ገልጸዋል፡፡የሰላምና አንድነት ጉባኤው ይህን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ሥራዬ ብሎ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶሚዛኑን ጠብቆ የሚሠራና በየጊዜው በሁለቱም አባቶች በኩል ለሚፈጠሩ ማናቸውም የሰላምእንቅፋቶች ተገቢውን መልስ ሲሰጥ የቆየ ነው። ለምሳሌ ያህል በሰሜን አሜሪካ ባሉት አባቶች በኩልለሰላሙ ሒደት እንቅፋት የሚሆኑ ማናቸውም ዓይነት ሁኔታዎች ሲከሰቱ በአፋጣኝ እያነጋገረ በተደጋጋሚ የማስተካከያ ደብዳቤዎች እንዲጻፉ ማድረጉ በአዲስ አበባ ከሚገኙት የቅዱስ ሲኖዶስአባላት የተሰወረ አይደለም። ይህንን በተመለከተ ደግሞ በመግለጫችንም ሳይቀር ጠቅስን የጻፍንበትጊዜ እንደነበረ ከዚህ በፊት ከወጡት መግለጫዎቻችንና ከፋይሎቻችንም ለመረዳት ይቻላል።በመሠረቱ በሁለቱም ተዳራዳሪዎች በኩል እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚል ሲያጋጥም የሰላምና አንድነት ጉባኤው ባለበት ከፍተኛ ኃላፊነት ለሰላሙ ሥምረት ይበጃል ብሎ ያመነበትን የመፍትሔ ሐሳብእንዲቀበሉ መጠየቅ ከአንድ አደራዳሪ አካል የሚጠበቅ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። ጉባኤው ሁልጊዜ ለሚያፈልቃቸው የመፍትሔ ሐሳቦች ደግሞ ማዕከል የሚያደርገው ቤተ ክርስቲያንን ብቻ ነው። ምናልባትም የሰላምና አንድነት ጉባኤው የሚሠራው የሽምግልና ሥራ በመሆኑ ሁሉንም  ላያስደስትይችላል። ስለሆነም ሁለቱም ወገኖች የማዳላት ሥራ ተሠራብን ብሎ ከመናገር ነጻ ይሆናሉ ለማለትምአስቸጋሪ ነው። ጉዳዩን በእውነት መነጽር ለሚያየው ግን የማዳላት ሥራ ሠርቶ ችግርን በጋራ በመፍታት እውነትን ሰላምንና ፍቅርን ለማምጣት የሚያስብ አካል ይኖራል ብሎ ማመን የዋሕነትነው። የሰላምና አንድነት ጉባኤው ዋነኛ ዓላማና አቋም ለሰላሙ ሥምረት ተገቢውን ጥረት በማድረግሚዛናዊነቱን ጠብቆ መሥራት በመሆኑ ከዚህ በፊት ባደረግናቸው ሦስት ጉባኤያት የሰላምና አንድነትጉባኤውን ጥረት ከማድነቅ ያለፈ ነገር በቃልም ይሁን በጽሑፍ ከሁለቱም አካላት የደረሰብን ትችትወይም አስተያይት እስካሁን ድረስ አለመኖሩን ለመግለጽ እንወዳለን።

3ኛ) የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ አሳሳች ትርጉም ይሰጣል የተባለውን በተመለከተ
ከአዲስ አበባ በመጡት ልዑካን ስም በወጣው መግለጫ ላይ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ያወጣውመግለጫ “አሳሳች ትርጉም ለመስጠት ነው” ተብሎ ተተችቷል። ይሁን እንጂ ይህ ዓይነቱ አባባልበፍጹም ከእውነት የራቀ ተራ ግምት ነው። በመሠረቱ ይህ ሐሳብ የተሰነዘረው በልኡካኑ የጋራ መግለጫተራ ቁጥር 4 ላይ የተወሳውን አቋም አብራርተን በመጻፋችን ይመስላል። ይኸውም በሁለቱም አካላትዘንድ ማለትም  በውጭ ባሉ አባቶች በኩል ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት፤ በኢትዮጵያ ባሉት አባቶች በኩልደግሞ የስድስተኛ ሢመተ ፓትርያርክ ከሰላሙ በፊት እንዳይደረግ በጋራ ተስማምተው ያንን የሚወክልቃል በጋራ ባወጡት መግለጫ ተራ ቁጥር 4 ላይ ያለውን መርጠው “ሰላሙ ለፍጻሜ እስከሚደርስድረስ በሁለታችንም በኩል ለሰላሙ መሰናክል የሚሆኑ ማናቸውንም ሥራዎች ከመሥራትተቆጥበን በትዕግሥት መጠበቅ ይኖርብናል” ሲሉ ተስማምተዋል። ይህንም በጉባኤው ላይ ምንማለታቸው እንደሆነ ሁለቱም የሰላም ልዑካን በሰፊው የተነጋገሩበት ሲሆን በመግለጫችን የተወሳው እውነት መሆኑን ለመረዳት ካለን የድምጽ  መረጃዎች  በቀላሉ ማረጋገጥ  ይቻላል። የሰላምና አንድነትጉባኤውም 3ኛው ጉባኤ አበው እንደተጠናቀቀ ኅዳር 30 ቀን 2005 . ባወጣው መግለጫ ላይይህንኑ መሠረተ ሐሳብ አብራርቶ ማውጣቱ ይታወሳል። ለተጨማሪ መረጃ የጉባኤውን ድረ ገጽ ይመልከቱ። http://eotc-peace-and-unity.blogspot.com

4ኛ) የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ ሰላሙን ለማደናቀፍ ነው የሚለውንበተመለከተ
ከአዲስ አበባ የመጡት ልዑካን መግለጫ ጸሐፊ የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫውን ያወጣውሰላሙን ለማደናቀፍ ነው ሲሉ ጉባኤውን ወቅሰዋል። ይሁን እንጂ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት ሲል ያለ አንዳች ዕረፍት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ባለው ዕውቀት፤ ጊዜናገንዘብ ተጠቅሞ ላለፉት ሦስት ዓመታት የደከመበትንና ዓላማዬ ብሎ የያዘውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይለማደናቀፍ ማናቸውንም ነገር እንደማያደርግ በሁሉም ዘንድ የታወቀ ሐቅ ነው፡፡ “ሰላሙን ለማደናቀፍነው” በማለት የሰላምና የአንድነት ጉባኤውን የወቀሱበት ምክንያት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነበአጽንኦት ልንገልጽ እንወዳለን። ምክንያቱም ልዑካኑ ለሦስተኛ ዙር በዳላስ፤ ቴክሳስ በተደረገው ጉባኤአበው መጨረሻ ላይ በጋራ ባወጡት መግለጫ በተራ ቁጥር 5 ላይ “ይህን መሠረታዊና ታላቅ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ለማሳካት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ከልብ እናመሰግናለን” ብለው በአንድ ቃልያመሰገኑትን ጉባኤ በአጭር ጊዜ  ውስጥ ቃላቸውን እንዲለውጡና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት በብዙ ድካም ላይ የሚገኘውን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የሌለውን ስም መስጠትና መንቀፍለምን እንዳስፈለገ ምሥጢሩ አልገባንም። በዚህም ምን አንድምታ ለመስጠት እንደታሰበም ግልጽአይደለም። በመሆኑም እውነታውን ለአንባብያን ኅሊና፣ ለታሪክና  ለጊዜ ከመሥጠት ያለፈ ለዚህ ሰፊማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ ባለመሆኑ በዚሁ እናልፈዋለን። ይሁን እንጂ በሦስተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት ላይ በተደረሰው ተስፋ ሰጭ የሰላም ሒደት ደስ ያልተሰኙትን አካላት ለማስደሰትናበምክንያት ቤተ ክርስቲያንን በልዩነት እንድትቀጥል ለማድረግ ምክንያት ተፈልጎ እንዳይሆን አሁንምጉባኤው ያለውን ከፍተኛ ሥጋት ለመግለጽ ይወዳል።

5ኛ) በሦስተኛው ዙር ጉባኤ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ያቀረበውን የመፍትሔ ሐሳብበተመለከተ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተለያዩ የመፍትሔ ሐሳቦችንእያፈለቀ ለሁለቱም አካላት ሲያቀርብ ቆይቷል። ለምሳሌ ያህል ቀደም ሲል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነጳውሎስ በሕይወት ሳሉ ለቤተ ክርስቲያን መለያየት ትልቁ ፈተና በአንድ ዘመን በተፈጠረው ጊዜያዊችግር ምክንያት ሁለት ፓትርያርኮች መኖራቸው ነበር። በዚህም ምክንያት ሁለቱም አባቶች በሕይወትባሉበት ዘመን ቤተ ክርስቲያን ምን ብታደርግ ሰላምን ልታገኝ እንደምትችል የተጠና ባለ ሰባት ነጥብየመፍትሔ ሐሳብ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለሁለቱም አካላት አቅርቦ ነበር። ቅዱስ ሲኖዶስ በቀረቡትየመፍትሔ ሐሳቦች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ ሳይሰጥበት ቅዱስነታቸው ስላረፉ ጉባኤው ከአሁኑየቤተ ክርስቲያናችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚገናዘብና ሁለቱንም ይበልጥ ሊያቀራርብና ሊያስማማየሚችል ወቅቱን ያገናዘበ አዲስ የመፍትሔ ሐሳብ በማጥናትና በማፍለቅ በዳላስ በተደረገው ስብሰባላይ  ባለ አራት ነጥብ የመፍትሔ ሐሳብ ማቅረቡ ይታወሳል። ይህ የመፍትሔ ሐሳብ በጥር ወር 2005 ዓ.ም በሎስ አንጀለስ፤ ካሊፎርኒያ ከሚካሔደው አራተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት በፊት በሁለቱምአካላት በኩል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአስቸኳይ ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያገኝተልኳል። እንደሚታወቀው የመፍትሔ ሐሳቡ ዝርዝር በዳላሱ ጉባኤ በልዑካኑ ፊት በንባብ መሰማቱንበመግለጫችን ላይ አትተን ጽፈናል።

ነገር ግን እኛ በአዲስ አበባው ልዑክ መግለጫ ጸሐፊ እንደተባለው በየትኛውም ምክንያት አባቶቻችንን ለማሳዘን የማይገባ ሥራ አልሠራንም፤ አንሠራምም። ምክንያቱም የምንደክመው የእግዚአብሔርመንግሥት ለሆነቸው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ነውና። በዚህ አይነት ከባድ ጊዜበሰላምና አንድነት ጉባኤው ላይ እንዲህ ዓይነቱ ፈታኝ ነገር መሰንዘሩ ካለብን የሥራ ክብደት አንጻርእውነተኛውን ዓላማችንን ከመግለጽና በአኰቴት ከመቀበል ያለፈ ነገር አይኖርም። አሁንም እኛየምንጮኸው በሁለቱም ወገኖች በኩል ከዕርቀ ሰላሙ የሚቀድም ምንም ነገር እንዳይኖር ነው። ያምሆነ ይህ የሰላምና አንድነት ጉባኤውን በእጅጉ ያሳሰበውን የሰላም እንቅፋት በማስወገድ ለሰላሙስኬታማነት ሁሉም ወገኖች ተገቢውን ሁሉ ካደረጉና ቤተ ክርስቲያንን አንድ ካደረጉ በየትኛውምመንገድ ሰላሙ ይምጣ እንጂ የእኛ መግለጫ ኃይለ ቃል እንቅፋት ሊሆን እንደማይችል እናምናለን።ስለዚህ ከአዲስ አበባ የመጡት ልዑካን በሰላምና አንድነት ጉባኤው ላይ ያለአግባብ ያስተላለፉትንየቅሬታ መግለጫ እንዲያነሡልን በትሕትና እንጠይቃለን። በተጨማሪም ቅዱስ ሲኖዶስ ሁኔታውንበስፋት ተመልክቶ የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ጥረት ለሠመረ ውጤት እንዲበቃ ያደርግ ዘንድበአክብሮት እየጠየቅን፦

1)      ሰላሙንም ለማሰናከል ለሚፈልጉ ክፍሎች ይህ ለሰላሙ ሒደት እንቅፋት እንደ ዋና ምክንያት ተደርጎ  እንዳይቆጠር፤

2)    የጉባኤው መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት እንቅፋት እንዳያጋጥመው የድርሻችንን ለመወጣት በመሆኑ አሁንም በልዑካኑ የጋራ መግለጫ ላይ “ሰላሙ ለፍጻሜ እስከሚደርስ ድረስበሁለታችንም በኩል ለሰላሙ መሰናክል የሚሆኑ ማናቸውንም ሥራዎች ከመሥራትተቆጥበን በትዕግሥት መጠበቅ ይኖርብናል” ብለው ልዑካኑ የገቡትን ቃል በማክበርና በማስከበርከምንም በላይ የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት ያስቀደመ ሥራ እንዲሠራ ለማድረግ በሁለቱምበኩል ጥረቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤

3)    የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ካለን ልባዊ ፍላጎትና ፍጹም ቅንነት አንጻር በመልካም ሒደት ላይ የሚገኘው ሰላም እንቅፋት እንዳያጋጥመው በማሰብየተሰጠ ማሳሰቢያ መሆኑ እንዲታወቅልን እየገለጥን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 ከተዘረዘሩትና ከአዲስ አበባየመጡት ልዑካን ባወጡት መግለጫቸው ካቀረቧቸው ወቀሳዎችና ትችቶች የሰላምና አንድነት ጉባኤውፍጹም ነጻ መሆኑን በአጽንዖት እንገልጻለን።

4)    በዳላስ፤ ቴክሳስ በተካሔደው ሦስተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ንግግር ላይ በልዑካኑ በተደረሰው የጋራ ስምምነት መሠረት ለዕርቀ ሰላሙ ሥምረት ይበጃሉ ተብለው በሰላምና አንድነት ጉባኤው የቀረቡትን ባለ አራት ነጥብ የመፍትሔ ሐሳቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በጥልቀት እንዲነጋገርባቸውና እንዲመክርባቸው እንዲደረግና እስካሁን ድረስ ቀደምነት ባላቸው ብፁዓን አባቶች ብቻ የተዋቀረው የሰላም ልዑክ ከልዩነት በኋላ ከተሾሙት አባቶች ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት ታክለውበት በአራተኛው የዕርቀ ሰላም ጉባኤ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እንዲገኙ እንዲደረግልን በትሕትና እንጠይቃለን።

5)     በመጨረሻም የሰላምና አንድነት ጉባኤ ወቅታዊውን ሁኔታ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ የዕርቀ ሰላሙን የሠመረ ውጤት ለማየት ካለው ቅን ፍላጎትና ጉጉት አንጻር እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት ለመዳፈር አለመሆኑን እየገለጽን ማንኛውንም እንቅስቃሴያችንን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠንን ተገቢውን መመሪያና ምክር ለመቀበል ዝግጁዎች መሆናችንን በትሕትና እንገልጻለን።

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ።”

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ።

---------------------------------------------------------------------------------------------------


  • ግርግሩ መልክ ይያዝ::
  • ሥርዐተ ቀብሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት ይተላለፋል::
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 16/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦  የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አስከሬን፣ ተጠብቆ ከቆየበት ሃያት ሆስፒታል ዛሬ፣ ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም፣ 5፡00 ላይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ደርሷል፡፡

በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ሓላፊዎችና መላው ሠራተኞች፣ የየድርጅትና የየኮሌጁ ሓላፊዎችና ሠራተኞች፣ አገልጋዮችና ምእመናን ታጅቦ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ከገባ በኋላ በቅድስቱ ውስጥ ዐርፎ ጸሎተ ቅዳሴው በብፁዕ አቡነ ማቲያስ የካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መሪነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ከንጋቱ 12፡00 ላይ በመላው ኢትዮጵያ ገዳማትና አድባራት የደወል ድምፅ ተሰምቷል፡፡
በወጣው መርሐ ግብር መሠረት የቅዳሴው ሥነ ሥርዐት እንዳበቃ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አስከሬን በልዩ ሠረገላ ኾኖ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በሚኒስትሮችና የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ በፖሊስ ሠራዊት ባንድ፣ በምእመናንና ምእመናት ታጅቦ ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጉዞ ያደርጋል፡፡ በዚህ ጉዞ የፖሊስ ሠራዊት ግራና ቀኝ በሰልፍ አስከሬኑን ያጅባል፡፡ የቅዱስነታቸው አስከሬን በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዳረፈ የዕለቱ መርሐ ግብር በጸሎት ይዘጋል፡፡ ረቡዕ ለኀሙስ አጥቢያ ከምሽቱ 2፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ሙሉ ጸሎተ ማሕሌቱ ሲከናወን ያድራል፡፡

በዛሬው የመርሐ ግብሩ ክንውን ሐዘንን ከመግለጽ ባሻገር በተለይም የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን አስከሬን ይዞ ለማስገባት ከተመደቡት አባቶች ውጭ በአንዳንድ መነኰሳት ዘንድ የታየው ከፍተኛ ግርግር ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ነው፤ በቀጣይ የሥርዐተ ቀብሩ ሂደት ቢያንስ ከሚገኙት እንግዶችና በቴሌቪዥን ከሚሰጠው የቀጥታ ሥርጭት አንጻር ፈር መያዝና መስተካከል እንደሚገባው አስተያየት እየተሰጠበት ይገኛል፡፡
እስከ አሁን በሥነ ሥርዐቱ ላይ የቅብጥ፣ የሶርያ፣ የአርመንና ሕንድ /ማላባር/ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ልኡካን እንዲሁም የግሪክ ኦርቶዶክስ ተወካዮችና የመሳሰሉት እንግዶች እንደሚገኙ ማረጋገጣቸው ተገልጧል፡፡
ቀሪውን የቀብር ሥነ ሥርዐት ክንውን ከመርሐ ግብሩ ይመልከቱ፡፡

የቅዱስነታቸውን ነፍስ በአብርሃም ዕቅፍ ያኑርልን
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡






በሕገወጦች በጨለማ የተዘጋጀው ደብዳቤ ተበተነ፡፡ 
አትም ኢሜይል
ግንቦት 7/2004 ዓ.ም.
ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ የተወሰደ: 

ከጥቂት ቀናት በፊት ማኅበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ማእከላዊ አስተዳደር ተገዥ ካለመሆን አልፎ የተቋሙን ሕልውና ወደ መፈታተን እንደ ደረሰ በማተት የሚከስ ደብዳቤ ለሕግ ተገዢ ባልሆኑ ግለሰቦች በጨለማ ተረቅቆ በመምሪያው ሓላፊ እንዲፈረም ተደርጎ ሊወጣ እንደ ነበር፤ ነገር ግን በመምሪያው ሓላፊው በቆሞስ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ መታገዱን ገልጸን ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ እስከ አሁን ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ “ፍጹም ሕገ ወጥ ድርጊት በሕጋዊዋና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መፈጸም የለበትም፤ ይቁም” ያሉትን የመመሪያ ሓላፊ አስተዳደሩ ከቦታቸው አንሥቷል፡፡ በምትካቸውም ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ደብዳቤውን በወቅቱ በተገለጠው ሁኔታ በማርቀቅ፣ እንዲፈረምና እንዲሠራጭ የሞት ሽረት ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት ግለሰቦች አንዱ የሆኑትን መምህር ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተን ሾሟል፡፡
ቆሞስ አባ ኅሩይ በመምሪያ ሓላፊነት ተመድበው ቦታውን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ በማኅበሩ መስተካከል አለባቸው በሚሏቸው ጉዳዮች ላይ ሁሉ የማኅበሩን አመራር አካላት እየሰበሰቡ መመሪያ ሲሰጡ፣ ማኅበሩም መመሪያዎችን እየተቀበለ ወደ ተግባር ሲለውጥ ቆይቷል፡፡ ቆሞስ አባ ኅሩይ ደብዳቤ በማርቀቅ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ልዩ ልዩ ክፍሎች አልፎ እስከ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በሚደርስ ሁኔታ በማብረር የማያምኑ ውይይት ተኮር ዘመናዊ የአመራር ዘዴን የሚከተሉ በመሆናቸው ማኅበሩ መመሪያቸውን ሁሉ እየተቀበለ በማገልገል ላይ ነበር፡፡ ማኅበሩ የሚፈልገው በመጠነ ሰፊ ችግሮች ውስጥ ባለች ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ የሚያሠራው ነውና፡፡

የመምሪያ ሓላፊው ቆሞስ አባ ኅሩይ ባላጠፉት ጥፋት ተከሰው ከቦታው መነሣታቸውን በመቃወም ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጥ ማኅበሩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ደብዳቤ ጽፏል፡፡ ጉዳዩም በቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳነት ተይዟል፡፡
maderaja memreya letter


ማኅበሩ ለጻፈው ደብዳቤ ምላሽ በሚጠብቅበት በአሁኑ ወቅት፤ በመምሪያ ሓላፊነት የተመደቡት መምህር ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተ ለረጅም ዓመታት የታገሉለትን ማኅበሩን የማደናቀፍ እኲይ ተግባር የሚያረጋግጡላቸውን ደብዳቤዎች ማብረር ጀምረዋል፡፡ በትላንትናው ዕለት ካበረሯቸው ደብዳቤዎች አንዱ ለቆሞስ አባ ኅሩይ መነሣት ምክንያት የሆነውንና ራሳቸው መምህር ዕንቊ ባሕርይ ከመሰል ግብረ አበሮቻቸው ጋር ሆነው አርቅቀው እንዲፈረምና እንዲበር የተሯሯጡለት ደብዳቤ ነው፡፡

የማኅበሩ አመራር በደብዳቤው ይዘትና በመምሪያችን እየተፈጠረ ስላለው የተጠናና ቤተ ክርስቲያኗን የማዳከም እንቅስቃሴ ላይ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረበውን አቤቱታ መልስ ይጠብቃል፡፡ በሒደቱ የሚፈጠሩትን ማናቸውንም ክስተቶች እየተከታተለ ለምእመናን ይፋ ያደርጋል፡፡
mk letter to synodos
የማኅበሩ አባላትም ሆኑ ምእመናን ዛሬ በማኅበራችን ላይ እየደረሰ ያለው ችግር በእናት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ካለው ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የማይባል በመሆኑ አገልግሎታችንን በተለመደው ሁኔታ አጠናክረን እንድንቀጥል እናሳስባለን፡፡

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

1 comment:

  1. የአትናቴዎስ ትምህርት ስለ መንፈስ ቅዱስ
    የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ
    አባ ጎርጎርዮስ የሸዋ ሊቀ ጳጳስ /M.A/


    አትናቴዎስ ስለ መንፈስ ቅዱስም በተናገረበት ባስተማረበት አንቀጽ መንፈስ ቅዱስ እንደ አብ እንደ ወልድ ከአብ ከወልድ ጋር ፍጹም አካል መኾኑን፣ በባሕርይ በህልውና አንድ መኾኑን ይናገራል፡፡ ከቅድስት ሥላሴ ሦስተኛው አካል መንፈስ ቅዱስ ሕጹጽ ፍጡር አይደለም፡፡ በብሉይ ኪዳን፣ በሐዲስ ኪዳን እንደ አብና እንደ ወልድ አምላካዊ ክብሩ ተነግሮለታልና፡፡ እነ አርዮስ እንደሚሉት መንፈስ ቅዱስ ፍጡር ቢኾን ኑሮ የፍጡራን ሕይወት ባልኾነም ነበር፤ እንዴትስ የእግዚአብሔርን ምሥጢር ለማወቅ ቻለ? /1ኛቆሮ.2÷10/ ወልድ ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ እንደሆነ መንፈስ ቅዱስም ከአብና ከወልድ ጋር አንድ ባሕርይ ነው፡፡ ሦስቱ አካላት /ገጻት/ ባንድ ባሕርይ ባንድ ህላዌ ይኖራሉ፤ አብ በወልድ ቃልነት ዓለምን ፈጠረ፡፡ ሦስቱ አካላት አንድ አምላክ ነው፡፡ በምሥጢረ ሥላሴ ወይም በሦስቱ መካከል ባዕድ ባሕርይ የለምና፡፡


    ወልድ ከአብ እንደ ተወለደ መንፈስ ቅዱስም ከአብ የሠረጸ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት ምሥጢር ገልጧል፤ ቋንቋ አናግሯል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ከበዓለ ጰንጠቆስጤ ጀምሮ የሚመራ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በአትናቴዎስ ትምህርት የባሕርይና የህላዌ እንዲሁም የአካላት ልዩነት፣ በምሥጢረ ሥላሴ የሚነገሩ ባሕርይ፣ ህላዌ፣ ከዊን በእስክንድርያ ትምህርት ቤት ከአትናቴዎስ በኋላ ትክክለኛ ፍቻቸው እንደሚከተለው ነው፡፡ /ኡሲያ/ ህላዌ የሚለው ቃል በእስክንድርያ ትምህርት ቤት በነበረው የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት አካል ከባሕርይ ሳይለይ አንዱ ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት ከዊን ማለት ነው፡፡ በአንጾኪያ ግን ይልቁንም ጳውሎስ ሳምሳጢና ተከታዮቹ «ህላዌ» የሚለውን ቃል በተሳሳተ አተረጓጐም በመተርጎም፤ ብዙዎቹን አሳስተዋል፡፡


    ለምሳሌ «ዋሕደ ህላዌ» ማለት ሦስቱ አካላት አንዱ በአንዱ አድሮ የሚኖር ማለት ነው፤ ብለው ያስተምራሉ፡፡ እዚህ ላይ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አካላዊና በከዊን የተለየ ህላዌ አልነበራቸውም ለማለት ጳውሎስ ሳምሳጢ ይመቸዋል፡፡ በሱ አስተሳሰብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በአብ ህልዋን ኹነው የሚያገለግሉ ዝርዋን እንጂ አካላውያን አይደሉምና፡፡ ስለዚህም በ260 ዓ.ም እሱን ለማውገዝ የተሰበሰቡ ሊቃውንት «ዋሕደ ህላዌ ምስለ አብ» ብሎ አትናቴዎስ ረትቶበታል፡፡ /አሞኡሲዮን ቶ፣ -ትረ/ ይህም የአትናቴዎስ አባባል ከጳውሎስ ሳምሳጢ ጋር ዝምድና የለውም፡፡ «ዋሕደ ባሕርይ» በማለት የባሕርዩን አንድነት «ምስለ አብ» አብ ማለት የአካልን ልዩነት ያሳያልና «ዋሕደ ህላዌ ምስለ አብ» በአንቀጸ ሃይማኖት «ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ» የምንለው ነው፡፡ እንግዲህ ህላዌ የሚለው ቃል፤ በምሥጢረ ሥላሴ አንዱ አካል በሌላው አድሮ ወይም ጥገኛ ኹኖ የማይኖር፣ ከሥላሴ አንዱም አንዱ፣ እያንዳንዱ አካል በአካሉ፣ በመልኩ፣ በገጹ ፍጹም መኾኑን ያሳያል፣ ያመለክታል፡፡ «ህቡረ ህላዌ ምስለ አበመለኮቱ፣ ኅቡረ ህላዌ ምስሌነ በትስብእቱ» /ተረፈ ቄርሎስ/
    በሌላም ቦታ «ህላዌ» ከግብርና ከአካል ስም ጋር ተጣምሮ ይገኛል፤ ለአብ የወላዲነት ለወልድ የተወላዲነት፣ ለመንፈስ ቅዱስ የሠራጺነት ስሙ ነው፡፡ «እስመ አበዊነ ስመይዎን በዝንቱ ገጸ መካን ለህላዌያት አካላተ፤ አትናቴዎስኒ ረሰየ ህላዌ አሐደ አካለ ዘእግዚአብሔር ቃል ዘተሠገወ» እንዲል፡፡
    ዳግመኛም ህላዌ አካልና ባሕርይ አንድ ኹነው የቆሙበት አስተጋባኢ ስም ስለሆነ ለአካልም ለባሕርይም ይነገራል፡፡ በአንቀጸ ተዋሕዶ ማለት የሦስቱን አንድነት በምንናገርበት ጊዜ አሐዱ ህላዌ እንላለን፡፡ መውለድና ማሥረጽ፣ መወለድና መሥረጽ በዚያው ባንድ ባሕርይ ውስጥ ነውና፡፡


    ስለዚህ በምሥጢረ ሥላሴ ባሕርይ አይከፈልም፡፡ አካል አይቀላቀልምና፡፡ ህላዌ ግን ለአካልም ለባሕርይም መነገሩን ገልጠናል፡፡ ባሕርይ ምንጊዜም ቢኾን ለአካል አይነገርም፤ አካልም ለባሕርይ ስም አይኾነውም፣ አለዚያ ግን ባሕርይን መክፈል ስምና ግብርን ማፋለስ ይኾናል፡፡ ወላዲ ባሕርይ፣ ተወላዲ ባሕርይ፣ ሠራጺ ባሕርይ የማይባለውም ስለዚህ ነው፡፡ ከተባለ ግን ሦስት መለኮት፣ ዘጠኝ አካላት ወደ ማለት ይሸነሸናል፤ የምሥጢረ ሥላሴው የግብር ስም ለምሥጢረ ተዋሕዶው የባሕርይ ስም አይሰጥም፡፡ የሦስቱም አካላት መለኮት ወይም ባሕርይ አንድ ነው፡፡ «ሠለስቱ ገጻተ አሐዱ አምላክ» ብሎ ለማመንና ለማሳመን ይህን ኹሉ ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በላይ እንዳየነው በእስክንድርያ የትርጓሜ ትምህርት ቤት እነ አትናቴዎስ «ህላዌን» /ኡሲያን/ ለአካልም ለባሕርይም ሰጥተው ይናገራል፡፡ /ኩነት/ ከዊን ግን ለአካል ብቻ ነው /ኢስታሲስ/ በአንጾኪያ ግን «ህላዌን» /አሲያን/ ለባሕርይ ብቻ /ኩነትን/ ከዊንን /ኢስታሲስን/ ለአካል ብቻ ሰጥተው ይናገራሉ፤ በዚህኛው ልዩነት የለም፡፡

    ReplyDelete