Tuesday, June 16, 2015

ሰበር ዜና - ከእዚህ በፊት በሰጣቸው ትምህርቶቹ በርካታ ጥያቄዎች የተነሱበት በጋሻው ደሳለኝ ሉንድ፣ስዊድን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌላ ትልቅ ውዝግብ ፈጠረ።።''በጋሻው ስዊድን የገባው በአውሮፓ የምትገኘውን፣በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ አባቶች የምትመራውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማወክ ያለመ ተልኮ ይዞ ነው'' አውሮፓ የሚኖሩ አባቶች እና ምዕመናን።(የደብዳቤ እና የፎቶ ቅጅዎች ተያይዘዋል)



           አቶ በጋሻው ዛሬም የውዝግብ ማዕከል ሆኗል
 


  • ወደ ሉንድ፣ስዊድን የገባበት ሰነድ በራሱ አወዛጋቢ ሆኗል፣
  • ሉንድ፣ስዊድን የሚገኘው ቴዎሎጂ ዩንቨርስቲ የግለሰቡን ወደ ስዊድን መምጣት እንደሚያውቅ ተደርጎ የተገለፀውን ደብዳቤ ሐሰት መሆኑ እየተነገረ ነው፣
  • ዩንቨርስቲው ስለጉዳዩ እንደማያውቅ ለማወቅ ተችሏል፣
  • በአውሮፓ የሚኖሩ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ አባቶች ስር የሚገኙ አጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የበጋሻውን አወዛጋቢ የሀገር ቤት ታሪክ የሚያውቁ አባቶች እና ምዕመናን በብርቱ እያስጠነቀቁ ነው፣
  •  ''ከሀገር ቤት አቡነ ማትያስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እና ቋሚ ሲኖዶስ እንዳስተምራችሁ ፍቃድ ሰጥተውኛል'' በጋሻው ለሉንድ፣ስዊድን ምዕመናን የነገራቸው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በበርካታ የቤተክርስቲያኒቱ ጉባኤያት ላይ ሁከት በመፍጠር፣በአደባባይ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶች በማጥላላት እና በአስተማራቸው ትምህርቶች አፅራረ ቤተ ክርስቲያን ይዘት ከሐዋሳ እስከ ጎንደር ከአዲስ አበባ እስከ ሐረር ባሉ አያሌ አጥብያ አብያተ ክርስቲያናት በሚገኙ  አባቶች ከመድረክ ላይ እንዳያስተምር በሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት፣የደብር አለቆች እና ምዕመናን የታገደው በጋሻው ደሳለኝ ስዊድን፣ሉንድ አንድ ሰንበት በተጭበረበረ መንገድ መድረክ በግድ ነጥቆ ማስተማሩ ምእመናንን በእጅጉ አስቆጥቷል።

በጋሻው መድረኩን በጉልበት ከነጠቀ በኃላ መድረክ ላይ ቆሞ 

ሉንድ፣ስዊድን ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሁለት ሳምንታት በፊት የግንቦት 21 የደብረ ምጥማቅ የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል ለማክበር ዝግጅት ይጀምራሉ።በእዚህ መሰረት ከስዊድን እና ኖርዌይ የሚገኙ አባቶች በአቡነ ኤልያስ ተመድበው ለአገልግሎት ይሄዳሉ።ጉባኤው ሲካሄድ ቀደም ብሎ በጋሻው በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ በማገልገል ላይ በሚገኘው ዲ/ን ያሬድ አማካይነት የግብዣ ደብዳቤ ተልኮለት ስዊድን ገብቶ ነበር።ሆኖም ግን ምእመኑን በመፍራት በዕለቱ በቦታው ዝር ሳይል ይቆያል።

በሳምንቱ ግን በቦታው የዶክትሬት ዲግሪውን በመስራት ላይ በሚገኘው እና ያለውን ትርፍ ጊዜ በሙሉ በቤተ ክርስቲያኒቱን በነፃ በቅዳሴ፣በማስተማር እና ምዕመናንን በመምከር የሚያገለግለው ቀሲስ መንግሥቱ በቦታው የዕለቱን ትምህርት ለመስጠት ሲዘጋጅ ከበጋሻው በኩል ትዕቢት በተሞላበት እና የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት ፈፅሞ በተፃረረ መልክ ካህኑን እላፊ ንግግሮችን ከመናገሩም በላይ መርሃ ግብሩን የሚመራው እና ቀደም ብሎ በጋሻውን ለማስመጣት ደብዳቤዎችን መላኩ የተነገረለት ዲ/ን ያሬድ የድምፅ መናገርያውን ከካህኑ ነጥቆ ለበጋሻው ሲሰጥ እና ቀሲስ መንግስቱ እና ምዕመናን ቤተ ክርስቲያኑን ጥለው እያለቀሱ ሲወጡ ተስተውሏል።ይህ ጉዳይ የበርካታ ምእመናንን ልብ ያሳዘነ ከመሆኑም በላይ ጉዳዩ በእዚህ ሳይቆም  ለቅዳሜ ሰኔ 6/2007 ዓም አሁንም በድጋሚ ምእመናንን የሚጠራ ፖስተር ተዘጋጅቶ እንዲሰራጭ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

Sunday, June 14, 2015

“ሃይማኖታዊ ግጭት ለማስነሣት ተንቀሳቅሳችኋል” የተባሉ የሰበካ ጉባኤ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ





  •   ፖሊስ10 ቀንየምርመራጊዜጠይቆባቸዋል

    
በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ፣ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤና የደብሩ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት “ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት ተንቀሳቅሳችኋልበሚል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት በዋና ሥራ አስኪያጅ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጥያቄ እየታሰሩ ነው

  •   በጥያቄአቸው፣ በአስተዳደር ይኹን በልማት ሥራ ምንም ችግር የለም ብለዋል በሌለ ልማት!
  • ምእመናኑንም ‹‹ምንም ዓይነት ድርሻ የሌላቸውና ማንነታቸው የማይታወቅ›› ሲሉ ገልጸዋቸዋል
  • የታሰሩት ምእመናን በፖሊስ ጣቢያ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ መስቀላችኹን አውልቁ›› ተብለዋል
  • የቀድሞው የደብሩ አለቃ ዘካርያስ ሓዲስና ኃይሌ ኣብርሃ ከውዝግቡ ለማትረፍ እያሰሉ ነው
bole bulbula medየቤተ ክርስቲያን ይዞታ ከቤተ ክርስቲያን አቋም ጋር በሚስማማ እና ሀብቷን በሚያስጠብቅ አኳኋን እንዲለማ በመጠየቅ በቅንጅት የተንቀሳቀሱ የቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ደብር ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላትበሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥያቄ እየታሰሩ እና ለእንግልት እየተዳረጉ ነው፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በክፍለ ከተማው ለወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ በጻፉት ደብዳቤ፣ በምእመናኑ እና የሰንበት ት/ቤት አባላቱ ተበይዶ የታሸገው የደብሩ ቢሮዎች በፖሊስ ርምጃ እንዲከፈቱ ምእመናኑም በወንጀል ድርጊት እንዲጠየቁ አመልክተዋል፡፡
ጥያቄአቸውን ተከትሎ ባለፉት ኹለት ቀናት ከኻያ የማያንሱ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት መታሰራቸው ታውቋል፡፡ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ ታስረው ከተለቀቁት ውጭ እስከ አኹን በእስር የሚገኙ ስምንት ምእመናን (አራት ምእመናን እና አራት የሰንበት ት/ቤት አባላት) በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገልጧል፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል ደብሩን በስብከተ ወንጌል ሲያገልግሉ ቆይተው በጡረታ የተገለሉ የ70 ዓመት ሕመምተኛ አዛውንት ይገኙበታል፡፡ ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሲገቡ በአዛዡ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ፤ መስቀላችኹን አውልቁ›› መባላቸውን ከእስር የተፈቱት ምእመናን ተናግረዋል፡፡
በደብሩ የልማት እና የመካነ መቃብር ይዞታዎች የሚገኙ የንግድ ቦታዎች እና ሱቆች ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ግለሰቦችን በሚጠቅም አኳኋን በከፍተኛ ዋጋ እየተከራዩ ባለበት ኹኔታ የደብሩ ገቢ እና ልማት እየተዳከመ መምጣቱ በምእመናን እየተገለጸ እና ይኸውም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የአስተዳደር ጉባኤ በተሠየመ አጥኚ ቡድን ተረጋግጦ እርምት እንዲደረግ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቢሰጥም፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ በደብሩ የአስተዳደር ይኹን የልማት ሥራዎች ምንም ዐይነት ችግር እንደሌለ ነው በደብዳቤአቸው የጠቀሱት፡፡

በአ/አበባ ሀ/ስብከት: ከብር 113 ሚልዮን በላይ የፈሰስ ዕዳ እንዲሰረዝ መጠየቁ እርምት ያስፈልገዋል፤ ‹‹የአየር ባየር የዘረፋ ስልቱን ለመሸፈን የተቀመረ ነው›› /ሠራተኞች/

Lique Tebebit Elias Techane
የአጥቢያዎች ፈሰስ፣ የሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪዎች እና የአበል ክፍያዎች ቀበኛ የጥንቆላ እስረኛሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ: ከግሮሰሪ(አ.አ) እስከ ባለአምስት ፎቅ ሕንፃ(መቐለ) ባለቤት
  • የቁጥጥር እና የፋይናንስ ሓላፊዎች የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ዝቅተኛ ነው
  • በቆጠራዎች የሚዘረፈው የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቢሯቸው ድረስ ይመጣላቸዋል
  • የቤተሰብ ጉባኤ በሚመስለው የቁጥጥር ክፍሉ ስብሰባ የዘረፋ ስልቶች ይቀመራሉ
  • ትኩረቱን ወደ ከፍተኛ ግዥዎችና ፕሮጀክቶች ለማዞር እስከ መምከር ተደርሷል
  • እነኃይሌ ኣብርሃ እንዳሉት፣ ‹‹ንቡረ እድ ኤልያስን የተማመነ ምን ይኾናል!››
/ከሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች/
‹‹ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች›› እንዲሉ በአኹኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሒሳብ እና በጀት እንዲኹም በቁጥጥር አገልግሎት ዋና ክፍሎች በኩል ከሕግ፣ ከመርሕ እና ከሥነ አመክንዮ ውጭ ብዙ ሕገ ወጥ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በአድባራት የደመወዝ እና የአበል ክፍያ ጭማሪ፤ በክብረ በዓል እና በወርኃዊ የአብያተ ክርስቲያን የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እና የንብረት ሽያጭ ጨረታ ወቅት የሚሠሩ ሙስናዎች ልክ እንደ ሕጋዊ መብት በግልጽ እተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ ለዛሬው፣ ለቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ወሳኝ ስለኾነው የፈሰስ(ፐርሰንት) ጉዳይ እንመልከት፡፡