Tuesday, February 4, 2014

የሐመረኖህ ኪዳነ ምህረት በላስቬጋስ የተደበቀና የደረስኩበት የውስጥ ችግር

 አንድ የዘወትር አንባቢያችን ከላስቬጋስ አካባቢ በተለይ በሐመረ ኖሕ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በመሆን እያገለገሉ ስላሉት መነኮስ እና ሥራቸው መጠነኛ የሆነ መረጃዎችን ልኮልናል። ምዕመን የማወቅ መብት አለው ብለን ስለምናምን ይኛም የመጣልንን መረጃ እንደወረደ ለእናንተው አቅርበነዋልና ተከታተሉ። መልካም ምንባብ እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ እንመኛለን።
መላከ ሰላም አባ ገብረ ኪዳን ሽፈራው
በጥቂት ምዕመናንና በአንድ ቄስ የዛሬ ስምንት አመት የተቋቋመው የሐመረኖህ ቤተክርስቲያን በመናፈሻ ፣በላይብረሪ ‘በሰርቢያንቸርች ፍላሚንጎና ጆንስ፣ቶሮፓይንስና ትሮፒካና በሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፣በመጨረሻም አሁን ባለበት ቤተክርስቲያን በብዙ ድካምና ትጋት ሲገለገል ቆይቷል አራት ወራት ያህል በካህን እጦት ከዲሲ፣ከሎሳንጀለስና ከሳንዲያጎ ፣ከዳላስ ቴክሳስ ካህናት እየተመላለሱ ሲያገለግሉ ቆይተዋል እለዚህ ቤተክርስቲያኑን በየሳምንቱ እየተመላለሱ ሲያገለግሉ የነበሩት ባለውለታ ካህናት ቀሲስ ከፈለኝ፣ አባ ሀይለስላሴ፣አባ ገብረ ማርያም፣አባ ገብረ መድህን ፣ቀሲስ ብርሀኑ፣ቀሲስ ሰብስቤ በመሀል ስማቸውን የረሳኋቸው የመጡ ካህናት ይኖራሉ እነዚህ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በባእል ቀን ሲያገለግሉን ነበር ከአራት ወር በኋላ በአቡነ ማትያስ ሽዋሚነጽ ዲ/ሳሙኤል ደጀኔ ቅስና ተቀብለው ለአራት አመታት ያህል ብቻቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አንድምቀን አገልግሎቱ ሳይቋረጥ ከአራት አመት በኋላ ዲ/ዮሐንስን ቅስና ከአቡነ ማርቆስ ተሸሙ ቀሲስ ሳሙኤልን እያገዙ ብዙም ሳይቆይ አባ ገብረኪዳን መጡ አንድ ሆነው በፍቅር በሰላም ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ አዲስ የሰበካ ጉባኤ ከተመረጠ ወዲህ ሰለም እየደፈረሰ መጣ በጉባኤው ውሰት አባ ገብረ ኪዳንን ጨምሮ ሦስት የማህበረ ቅዱሳን አባላት አሉበት እንደምንሰማው ውሳኔዎች በግሩፕ መወሰን ጀመሩ በሞቀበት ፈላ የሆነው ዲ ምስክርም ወደሞቀበት ሲያጫፍር ቆየ ይህ በእንዲህ እንዳለ አባ ገብረ ኪዳን ለአራት ወር ወደሀገርቤት ሲሄዱ


1. የተከራዩትን አፓርትመንት ኮንትራቱ ሲያልቅ መሄድ ሲችሉ ሳያልቅ በመሄዳቸው በባዶቤት ቤተክርስቲያኒቱ 4000.00 ብር በከንቱ አወጣች

2. የአራት ወር ደሞዝና አልፎም ተርፎ የመጓጓዣቸውንም ቤተክርስቲያኑ ካልከፈለኝ በሚል ገንዘብ ወዳድነታቸውን አሳዩ በሰበካጉባኤ ያለው አለመግባባት ተባባሰ

3. ሰበካ ጉባኤው አባ ሃላፊነት የጎደለው ሥራ ሲሰሩ አስተዳደራዊ ውሳኔ በመስጠት ፈንታ ደሞዛቸውን እንክፈል ብሎ ወሠነ በተለይ በማህበረቅዱሳኑ አባላትና በሞቀበት ፈላው ዲቆን ግፊት ይህ አግባብነት የሌለው ውሳኔ ተወሰነ አባ ሆዬ ሰበካ ጉባኤው ደሞዝ ከለከለኝ በሚል ሰበብ ከህዝቡ በአፈቀላጤያቸው በዲ/ወንደሰን በቀለ እና በሞቀበት ፈላው ዲያቆን ቅስቀሳ የሰበሰቡት ገንዘብ ሳያንስ ከሰበካ ጊባኤው የአንድ ወር ደሞዛቸው ቀድሞውኑ ለቫኬሽን የተከፈላቸው ሲሆን አይበቃኝም ብለው ስለመለሱት እርሱን ጨምሮ የሁለት ወር ደሞዛቸውን ተከፍሏቸዋል በሞቀበት ፈላው ዲያቆን ቤታቸውን ስከራይላቸው አካውንታቸው ውስጥ መቶሺህ ዶላር አየሁ ብሎ አነድ ሰሞን ምስጢሩን ለመንዛት ቢሞክርም ሰሚጆሮ ስላጣ አፉን ዘግቷል አባ መቶሺህ አይደለም ሚሊየን ቢኖራቸውም በቃኝ አይሉም እሳቸውም ለዚህ ምስክር ናቸው እኔ አሜሪካ የመጣሁት ልመንን አይደለም ገንዘብ ፍለጋ ነው የዋልድባን እና ደብረሊባኖስን ገዳም ወደጉን እያየሁ የመጣሁት ብለዋል ዛሬስ አባ የሁለት ሺህ ሶስት መቶ ዶላር ደሞዝተኛ ናቸው አይበቃቸው ይሆን ላንድ ለራሳቸው በሳምንት አንድቀን እየሠሩ ይህን ያህል ደሞዝ በአሜሪካ እጅግ ብዙ ገንዘብ ነው
አባ ግን አሁንም አይበቃኝም የለኝም ነው የሚሉት ምክንያቱም ሕዝቡ ደግሞ ትንሽ ጣል እንዲደርግላቸው ነው

4. አባ ገብረኪዳን በእየእስቴቱ እየሄዱ ሲያገለግሉ በየሳምንቱ ቢያነስ ሁለት መቶብር ከየቤተክርስቲያኑ ይሰጣቸዋል አራት ጊዜ ሁለት 800 መቶ ዶላር ማለት ነው 800+2300 ይሆናል ሦስት ሺሀ አንድ መቶ ስለዚህ አባ ገለልተኛ ቤተክርስቲያን የለ የኢትዮጵያ ብሯ ካለች ቀጥ ብለው ያገለግላሉ የሚገርመው ነገር አቡነ ፋኑኤልን ገለልተኛ ለምን ይሄዳሉ እያሉ መክሰሳቸው ነው ለሳቸው ጊዜ ይቻላል ለጳጳሱግን ነውር ነው የሚያስጠላኝ እንዲህ ያለ ነገር ነው ሰው ራሱ ሲያደርገው መልካም ሌላውግን ለም ማለት አይቻልም አባ ለብር ሲሉ ሲያትል ሄደው የአቡነ ፋኑኤልን ስም ጠርተው እንደቀዱ አውቃለሁ ላስቬጋስ ላይደግሞ አይጠሩም ለምን ለብር 2300 ዶላር እንዳይቀር ያኮረፈ ህዝብ የሚጥላትን እጁን እንዳይሰበስብ ይገርማችኋላ በሪፖርት እንኳ ለአባ ደሞዝ ስንት እንደሚከፈል አይነገርም ታይታን የሚወደው ዲ ግርማ አለባብሶነው ሪፖርት የሚያቀርበው ምክንያቱም አንድ የታክሲ ሾፌር ቂጡን አቃጥሎ የሚያገኘውን ደሞዝ እሳቸው ሰድስት ቀን አርፈው አንድቀን ሰርተው ያገኙታልና ነው አባ ሆዬ አያፍሩም በየሰው ቤት ጸበል መርጨት ለታመመ መጸለይ ለሽምግልና ወዘተ ብዙ ሥራ አለኝ ሊሉ ይችላሉ እርሱ ደግሞ ከተሳሰብን ራሱን የቻለ ደሞዝ አለው ሁሉም በደረሱበት ለጋዝ እያለ ሃምሳም መቶም እንደሚጥል እና ውወቃለን

5. አባ ገብረኪዳን የሚናገሩትን አያውቁትም አሁን ስለ አቡነ ፋኑኤል ብትጠይቋቸው አንዴ መናፍቅ ናቸው አንዴ ከመናፍቃን ጋር ይተባበራሉ አንዴ በሃይማኖት አይጠረጠሩም ችግር የለባቸውም ይላሉ ለነገሩ የእኛ ህዝብ አፈጮሌን ይወዳል በተለይ አባ በባለገር ቋንቋ ዛዲያ ተያ በኋላ እያሉ ሕዝቡ የረሳውን የገጠር ቋንቋ ስለሚናገሩ እና የአነጋገራቸው ዘይቤ ህዝቡን ስለሚያዝናናው የፈለገ ብር ቢያወጣ ደስ ይለዋል ይወዳቸዋል እሳቸውንም ለማየት በየሳምንቱ የሚመጣም አልጠፋም ሁሉም መልካም ነው ግን አባ ሕዝቡን ይዘው ወዴት እየሄዱ ነው ሕዝቡስ ዝም ብሎ አባ ያሉትን መስማት አለበት ወይ ሌሎች ካህናት ከአባና ከማህበረቅዱሳን ካህናት ውጪ የሉም ወይ መውደድ ሌላ ነው የሚወዱትን ተከትሎ ገደል መግባት ሌላ ነው ህዝቡ ስለወደዳቸው ሁለት አፍ መሆናቸውን እንኳን አያስተውልም ለእኔም የተገለጸልኝ በቅርቡ ነው

6. አባ ለገንዘብ እና ለመኖሪያ ፈቃዳቸው ሲሉ በአሜሪካ ሲኖዶስ ስር ነበሩ ራሳቸው በመድረክ የተናገሩት ነው በአሜሪካን ሲኖዶስ ስር ደግሞ በስልጣን ጥማት ልዮነት በተጨማሪ የሃይማኖት ችግር ነበር አሁንም አለ መዝሙር በኦርጋን ከመዘመሩ የአሳማ ሥጋ እንዲበላ ከነጫማ ወደቤ/ክ እንዲገባ ሥርዓተ ቅዳሴው በአጭር እንዲሆን ተአምረማርያም እንደማይነበብ ከኢትዮጵያ ተወግዘው የተለዮ በተሳሳተ ሃይማኖት ትምህርት የተከሰሱ እነ ልዑለቃል እነ መላኩ ያሉበት ነው ይህ ሁሉ በሚከናወንበት ሲኖዶስ ሥር ሆነው አንድም ቀን እገሌ መናፍቅ ነው ይህ ትክክል አይደለም ብለው ተቃውመው አያውቁም ለምን ብትሏቸው ኬዜ እንዳይበላሽ ይሏችኋል መቼም የመነኮሱት ለኬዛቸው አይመስለኝም ማን ያውቃል ሊሆንም ይችላል ታዲያ ዛሬ ጀግና ሆነው ጳጳስ የሚቃወሙት እውነት ለሃይማኖት ነው ? እውነቱ ለሃይማኖት አይደለም አሁን የተከበቡት በማህበረ ቅዱሳን አባላትና በሚወዳቸው ህዝብ መካከል ስለሆነ እንደጀግና ዘራፍ ብለዋል ነገ ደግሞ ማን ያውቃል ምን እንደሚመጣ ቆብ ይጣል ይሆናል ብቻ እግዚአብሔር ይጠብቃቸው

7. አባ ገብረኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል ነገሩ አላምር ሲላቸው ስልጣኑን ይውሰዱና እርሶ ያስተዳድሩ ሲሏቸው የለም አላደርገውም ሀገሩን ጥዬ ነው የምሄደው በጭራሽ እያሉ ሲፎክሩ በአፋቸው ተሰምተዋል አሁንግን ከሥልጣኑላይ ፊጥ ብለው ስናይ የዛንጊዜ ፉከራቸው የአፍ ነበር በልባቸው ግን አድርገውት ነው ምነው ዛሬ በሆነ የሚለቁት ስለቴን አገባ ነበር ይሉ እንደነበር በግልጽ ያስተውቃል ለነገሩ ለስም ተቀመጡበት እንጂ የሚመራው በቂርቆስ ጉሊት ድንችና ሽልጦ የሚገለብጡ የመንደር ዱርዬዎች መሪ የነበረው በሞቀበት ፈላው ዲያቆን ነው ይህ ዲያቆን መድረክ ጥማት ያለበት ከመሆኑም በላይ ባለስልጣን መሆንም ታላቅ ምኞቱ ነው በሬዲዮ እንኳን ሲቀበጣጥር ተው የሚለው የለም ጀግና ብለውታል የመንደር ጀሌዎቹ መቼም ቤተክርስቲያን ያልተሸከመችው ጉድ የለም ተመልሰው ቢሆን ጥሩ ግን እንደዛው እንደጥንቱ በጥፋት ላይ ጥፋት እየጨመሩ ቤተክርስቲያንን የአመጸኞች ጓዳ ሲያደርጓት ማየቱ ያማል የሚገርመው ነገር ሕዝቡም የሚወደው እንዲህ አይነቱን ነው ቢጤ ለቢጤ መሆኑ ነው ግን በምድርስ ይሁን በሰማይ ግን ይህ የለም ለመጽደቅ ከሆነ የምንከተለውን ለይተን እንወቅ።

8. አባ መሳለሚያ አካባቢ ምን የመሰለ ቤት እንደሰሩ ይታወቃል አሁንም አዲስ መኪና እየነዱ ነው ይሁን ይህ ሁሉ ሰርቀው ሳይሆን ከዛም ከዛም ቃርመው ያገኙት ነው የነጠርኩ መነኩሴ ነኝ ስለሚሉ እና እንደምሰማው መነኩሴ ማለት ለዚህ አለም ፈቃድና ምኞት የሞተ ነው ይባላል ሲመነኩስም እንደሞተ ሰው ሆኖ ተገንዞ ነው የሚመነኩሰው ከምንኩስናቸው ጋር ይህን ሁሉ ገንዘብ ማካበቱ ሀብት ንብረት ማፍራቱ እንደ ዝሙት አይቆጠርም ወይ ወይ ባንድ ልብ አልቻልኩም በቃኝ ተብሎ ቆቡን ማውለቁ መልካም ነው በጣም የሚርመው አባን ስለፖለቲካ ብትጠይቋቸው በደንብ አድርገው ያብራሩላችኋል የሚያመልጣቸው አንዳች ወሬ የለም ልቅም አድርገው አጣርው ነው የሚያውቋት በርግጥ የተትረፈረፈ ጊዜ አላቸው በቀለም ትምርትም አእምሯቸው አልተጨናነቀም ስለዚ ብዙ ክፍት ሚሞሪ ቦታ ስላላቸው የሚያዩትንና የሚሰሙትን ሁሉ አእምሯቸው ይመዘግባል ይህ ሁሉ ባልከፋ ሥር መሠረት ያለው እውቀት ስለሌላቸው ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ማፍረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ ስለማይገባቸውና ከተወገዙ ጳጳሳት ጋር ሥርዓት አፍርሰው ይቀድሱ ስለነበር ፣በምንኩስናውም ሥርዓት ብዙ ያፈረሱትና የናዱት ነገር ስላለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ማፍረስ ልማድ አድርገው ስለያዙት ሕዝቡም ሥርዓት አልበኛ ሆኖ ከሀገረ ስብከት ከቅዱስ ሲኖዶስ ተለይቶ በስም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ተብሎ ለማታለያ የፓትርያርክ ስም በመጥራት ሕዝብን እያታለሉ መኖር አባ ቢበቃቸው መልካም ነው እዚህ ካሉት ካህናት ትንሽ የኩራዝ እውቀት ያላቸው እሳቸው ናቸው ቢገባቸው የደረሰባቸው የመኪና አደጋ ማስጠንቀቂያ ነበር አሁንም ጊዜው ሳይመሽ አባ ያጠፉትን ቤተክርስቲያን ያስተካክሉ አንዳንዴም ለነፍሶ ያስቡ መቼም ቅዳሴውን ጸሎቱን ስብከቱን እንደ መተዳደሪያ ሥራ እንደያዙት ግልጽ ነው ሥራም ቢሆን ከልብ ሲሰራ ውጤቶ ያምራል ስለዚ አባ ገብረኪዳን ልብ ይበሉና ወደልቦ ተመለሱ ይህ ሁሉ ሁኔታ ሲታይ የሃይማኖት ነው ወይንስ የግሩፕ ቤት ያሰኛል ሰዎች በሃይማኖት መንገድ ሳይሆን በጉልበት በአድማ እነሱ ሚፈልጉበት መንገድ መሄዳቸው የሰው መንገድ ሆኖ ይቀራል ለጊዜው ግን ጥቂት ሰዎችን ይጎዳ ይሆናል።
ስለ ቀሲስ ሳሙኤል አነጋገራቸው ጠንካራና ለቆሙለት አላማ ወደኋላ የማይሉ ቀጥተኛ አማሪኛ የሚጠቀሙ ስለሆነ አነጋገራቸው ብዙም አያስደስተኝም እውነትን ለሚፈልግ አጭርና ግልጽ ነጥቧን ብቻ ነው የሚናገሩት ከሁሉም ደግሞ ኃይለቃል መናገራቸው ለእነ አባ ተመችተዋቿል አሁን የሉም ግን የማዝነው አራት አመት ብቻቸውን ደክመው ቤተሰብ ተሸክመው በነጻ ያለደሞዝ ሲያገለግሎ ቆይተው ሌላው ቢቀር እግዚአብሔር ይስጥልን ሳይባሉ መለየታቸው ነው። ይሁን እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል ድሮም ለሥጋ ጥቅም አልሰሩም
ገንዘቡን እንደልብ የሚያፍሱት የመሰላቸው አባ ሥልጣን ለመያዝ ሲሉ በአቡነ ፋኑኤል ሰበብ ከነሞቀበት ፈላና ከአፈቀላጤአቸው ጋር ሆነው ስማቸውን በሀሰት በማጥፋት ገፍተው ሲያስወጠዋቸው አንድም ሰው ለምን አለማለቱና አለመጠየቁ በጣም ይገርማል ለሳቸው ረፍት ነው ግን ሕዝቡ በእውነት የደከመለትን የማያውቅ መንጌ እንዳለው ወርቅ ቢያነጥፉለት ፋንድ ነው የሚል ህዝብ መሆኑ እጅግ ይገርማል እሳቸውም ጨክነው ከቤተክርስቲያን መጥፋታቸው ልክ አይደለም እስከ መጨረሻው መታገል ነበረባቸው ቀሲስ እርሶም ወደቤቶ ተመለሱ ህዝቡ ለጊዜው ተታሎ ነው እያደርግን እውነቱን ያውቀዋል እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ይባል የለ እንደሰማሁት ከልጅነት ያደጉት በቤተክርስቲያን ነው ታዲያ እስከመቼ ከቤተክርስቲያን ተለይተው ይኖራሎ እልኸኝነቱ ይብቃ የእርሶ ጥሎ መሄድ ለነ አባ ተመችቷል ቤተክርስቲያን እንሠራለን እያሉ እየተሯሯጡ ነው ጥሩ ነው ቤተክርስቲያን መስራት ግን ሕንጻውን ባቻ ማቆም እኮ አያጸድቅም ሰሎሞንም ቤተመቅደስ ሰርቶ ነበር ግን ተጠቃሚዎቹ በአግባቡ ስላልተጠቀሚበት ፈረሰ የድንጋይ ክምር ሆኖ ቀረ ዛሬም ፍቅር ሳይኖረን በአመጽ ውስጥ ሆነን በምንሠራው ቤተክርስቲያን ከንቱ ድካም ነው ስለዚህ ቤተክርስቲያን እየሠራን ወደሥርዓት ተመልሰን ወደአንድነት እንምጣ ወደፍቅር እንመለስ
አሁን የሐመረኖህ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ሥር አይደለችም ግን ለማስመሰል የፓትርያርክ ስም ይጠራል በመተዳደሪያ ደንቡም በግልጽ እንደተጣፈው ሀገረስብከትና ቅዱስ ሲኖዶስ በፋይናንስና በአስተዳደር አይገባብንም ብለዋል ምንም አይነት የመዋቅር ግንኙነት ከሲኖዶሱም ሆነ ከሀገረ ስብከቱ ግንኙነት የለንም የፓትርያርክን ስም ብቻ መጥራት በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር አያደርግም ሀገረ ስብከቱም ሲኖዶሱም ይህቺን ቤተክርስቲያን አያውቃትም በእየእስቴቱ ያሉ የማህበረቅዱሳን አባላት በስያትል በዲሲ ከአቡነ ፋኑኤል እግር ስር ተደፍተው ይቅርታ እየጠየቁ ጥፋታቸውን አምነው እየተመለሱ ነው እነዶክተር መስፍን ቀሲስ በላቸው ቀሲስ ያሬድ እነአቡነ ማቴዎስ በተገኙበት ይቅርታ እየጠየቁ በእሳቸው ሥር ሊተዳደሩ ደብዳቤ እስከመጻፍ ደርሰዋል ታዲያ እነ አባ ምነው ተለጎሙ ምናልባት ቀሲስ ሳሙኤል ተመልሰው ስልጣኔን ይወስዳሉ ብለው ይሆን አይዞት እሳቸው ሥልጣኑን የሚፈልጉት አይመስለኝም አስተዳዳሪነት በተራ ይሁን ተብሎ እነ አባ ባወጡት ደንብ ላይ ሺነበብ በዚህ እስማማለሁ ሲሉ በስብሰባ ሰምቻለሁ በሰላም ሊያስረክቦትም እንደነበር እናውቃለን ስለዚህ ገንዘቦም አይጎድልም እኔ ለነገሩ አነሳሁት እንጂ ለምን አባ ይከፈላቸዋል አላልኩም አይከፈላቸው የሚልም የለም ግን ቤተክርስቲያኒቱን በሕግና በሥርዓት እንድትመራ ያድርጉ ወደ እናት ቤተክርስቲያን ይመልሷት በቃለአዋዲ ተመሩ፣ ወደ ሀገረስብከቱ ተመለሱ አቡነ ፋኑኤልን ይቅርታ ጠይቁ አለቆችዎ እነ ቀሲስ በላቸው ታርቀዋል እርሶም ይታረቁና የሐመረኖህን ሰላም መልሱ ይህን ካደጉ ብሩን እንደፈለጉ ቢያፍሱትም አያስጨንቀንም ቢሆን መነኩሴ እንደመሆኖ ምግባርን ከሃይማኖት ጋር አስተባብረው ቢይዙ መልካም ነበር ካልሆነ ግን የግል ሕይወትዎ የግሎ ነው እኛን አያገባንም ቤተክርስቲያንን ግን አይንኩብን

እግዚአብሔር ልቦና ይስጦት 
ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ ይጫኑ
ተጨማሪ መረጃ እንዲሆን ይህንን ይጫኑ
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment