Tuesday, October 29, 2013

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ በ28 የመነጋገርያ አጀንዳዎች ውይይቱን ቀጥሏል

Ethiopian_Orhodox church bilden addis_Abeba_2
  • ዐሥር አህጉረ ስብከት የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንደሚደረግባቸው ተጠቁሟል፤ በፓትርያርኩ፣ ብፁዕ ዋና ጸሐፊውና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ የተያዙና በቁጥር ከ10 – 12 የሚኾኑ የታሳቢ ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት ዝርዝር ለምልአተ ጉባኤው እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡
  • በተጭበረበረ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃና የዶክትሬት መመረቂያ ጥናትን አስመስሎ መቅዳት/plagiarism/ ክሥና ወቀሳ እየቀረበባቸው የሚገኙት፣ ሓላፊነትን በተገቢው ኹኔታ ባለመወጣትና በትጋት ባለመሥራት የተገመገሙት ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ፣ በከባድ እምነት ማጉደል በተቀሰቀሰባቸው የካህናትና ምእመናን ተቃውሞ ከቅ/ላሊበላ ደብር አስተዳዳሪነት የሚነሡት አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንንና የመሰሏቸው ቆሞሳት ከታሳቢ ዕጩዎች መካከል መገኘታቸው በምርጫው አግባብነት ላይ ጥያቄ አስነሥቷል፡፡
  • ‹‹የምንሾማቸው ኤጲስ ቆጶሳት በተለምዶ የተሾሙ ሳይኾኑ የተማሩ፣ የሠለጠኑ፣ ነገሩ የገባቸውና መከራ ለመቀበል የተዘጋጁ ሊኾኑ ይገባል›› ከሚለው የፓትርያርኩ የምልአተ ጉባኤ ጋዜጣዊ መግለጫ ጋራ በቀጥታ የሚጣረስ አይደለምን? የቤተ ክርስቲያንንስ አመራር ከወቀሳ ያድናል?
  • የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር ጥናትና የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ተግዳሮቶች፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደራዊ ችግርና የሊቀ ጳጳሱ ዕጣ ፈንታ እንዲሁም በሊቃነ ጳጳሳቱ ዝርዝር እይታ ላይ የሚገኘው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ምልአተ ጉባኤውን በስፋት እንደሚያነጋግ ተጠቁሟል፡፡
  • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሕንፃን የጠቅላይ ቤተ ክህነት የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ያስተዳድራል፤ የመንፈሳዊ ኮሌጆች ልዩ ልዩ ገቢዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሒሳብ ተካተው በሚመደብላቸው በጀት ብቻ ይሠራሉ፡፡
  • በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከኦዲት ምርመራ ጋራ በተያያዘ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የቀረበውን ግለሰባዊ ትችት ምልአተ ጉባኤው በከፍተኛ ድምፅ ውድቅ በማድረግ የዘገየው የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ ተጠናቆ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
  • ሊቃነ ጳጳሳቱ በ‹‹መቻቻል›› ላይ የሰነዘሩት ትችት መንግሥትን አሳስቧል፤ የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋራ ሌላ ዙር ውይይት እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል፤ በደኅንነት ስም በየሊቃነ ጳጳሳቱ ቤት የሚዘዋወሩ ግለሰቦች ዝርዝር ለመንግሥት ይቀርባል፡፡
  • የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት ሓላፊነታቸውን ለቀው ወደ አሜሪካ ሄዱ፡፡ በአውስትራልያ በአሜሪካው ሲኖዶስ አስተዳደር ሥር የምትገኝ የአንዲት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እልቅና በውዝግብመሾማቸው ተነግሯል፡፡

የሃይማኖት እንከን የሌለባትና ተቆርቋሪ ምእመናን ያሏት ቤተ ክርስቲያናችን በአመራርና በአያያዝ ምክንያት የምትወቀስበትና ልጆቿን የምታጣበት ታሪክ ሊገታ ይገባል – ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ

His Holiness meglecha 11
ፎቶ- ማኅበረ ቅዱሳን
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመጀመሪያው ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባው ስለሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ዛሬ፣ ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጥዋት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በቅዱስነታቸው መግለጫ መሠረት ምልአተ ጉባኤው÷ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ምእመናንን ስለ መጠበቅና ማብዛት፣ የቤተ ክርስቲያንን የትምህርት ተቋሞች በጥራትና አደረጃጀት በመለወጥ ከመማርና መሠልጠን አልፎ መከራን ለመቀበል የተዘጋጁ ላእካነ ወንጌልን አብቅቶ ስለማውጣት፣ ፍጹም የዕድገት ለውጥ ለማምጣት ስለሚያስችለው የፋይናንስና የመልካም አስተዳደር ጅምር ጥናት ሂደት፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ የውሳኔ አሰጣጥ የቤተ ክህነት ልዩ ልዩ ክፍሎች ሓላፊዎች፣ ካህናት፣ ሊቃውንት፣ ወጣቶችና ምእመናን ውክልናና ተሳትፎ ስለሚረጋገጥበትና የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ሰፊ ድጋፍና ተቀባይነት ስለሚያገኝበት አሠራር ይመክራል፤ ውሳኔም ያሳልፋል፡፡

Monday, October 21, 2013

የካህናት እና ምእመናን ምዝገባ(ቆጠራ) ሊካሄድ ነው

  • ከ29 ሚልዮን ብር በላይ የበጀት ጥያቄ ለቅ/ሲኖዶስ ቀርቧል
  • የ49 አህጉረ ስብከትን 800 ወረዳዎች ይሸፍናል
  • ከ21,680 በላይ የሰው ኃይል ይሳተፍበታል
  • አጽንዖት ተሰጥቶ እንዲሠራበት አጠቃላይ ጉባኤው በጥብቅ አሳስቧል
  • የአህጉረ ስብከት የስታቲስቲካዊ መረጃዎች አያያዝ ጥራት አሳሳቢ ኾኗል
  • ‹‹የምእመናን ምዝገባ ለቤተ ክርስቲያን ያለው ጠቀሜታ ከመለካት በላይ የኾነ ወሳኝ ተግባር እንደኾነ የጉባኤው አባላት ተረድተናል፡፡ ያለንን አቅም በማቀናጀት በቀጣዩ ጊዜ በጥራት መዝግበን ለማቅረብ ቃል እንገባለን፡፡›› /የአጠቃላይ ጉባኤው የአቋም መግለጫ/

ሰበር ዜና – በምዕ. ወለጋ በቤተ ክርስቲያን ላይ በሚፈጸመው ግፍ ፓትርያርኩ መንግሥትን አሳሰቡ

  • የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጉዳዩን በጥብቅ ይነጋገርበታል
  • በመንግሥት ባለሥልጣናት ስለሚፈጸሙ በደሎች ከአህጉረ ስብከት የሚቀርቡ አቤቱታዎች የፍትሕ አካሉን አፋጣኝ ውሳኔ ያገኙ ዘንድ ቅ/ሲኖዶሱ ግፊት እንዲያደርግ አጠቃላይ ጉባኤው ዐደራ ጥሎበታል
  • አህጉረ ስብከት ያቀረቧቸውን የአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት በደሎችና ተጽዕኖዎች አጣርቶ መፍትሔ የሚሰጥ÷ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተውጣጣ ኮሚቴ እንዲዋቀር አጠቃላይ ጉባኤው በአቋም መግለጫው ጠይቋል
  • ‹‹ይህ ዐይነቱ ጊዜ የማይሰጠው ችግር ወደ ሌላ ከመዛመቱ በፊት አፋጣኝ መፍትሔ ማግኘት አለበት፡፡›› /የ፴፪ው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ/
  • ‹‹ድርጊቱ የመቻቻልን ሕግ እያፈረሰ ነው፤ በአካባቢው ያለው መንግሥታዊ አስተዳደር ሊያስብበት ይገባል፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
  • የምዕ/ወለጋ ሀ/ስብከት በሪፖርቱ የዘረዘራቸውን ችግሮች ከዘገባው በታች ይመልከቱ
His Holiness Abune Mathias0000

በቤተ ክርስቲያን ላይ የአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት የሚፈጽሟቸው በደሎችና ተጽዕኖዎች – የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ትችት፣ ጥያቄና ምስክርነት ሙሉ ቃል

ነገ በሚጠናቀቀው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ፴፪ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚለው መርሐ ግብር ‹‹የብዝኃነት አያያዝ፣ አክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎቹና መፍትሔዎቹ›› በሚል ርእስ አቶ ገዛኸኝ ጥላሁን፣ አቶ ታዴዎስ ሲሳይ እና አቶ ጣሰው ገጆ በተባሉ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሦስት ከፍተኛ አማካሪዎችና ባለሞያዎች ጽሑፍ መቅረቡና ውይይት መካሄዱ ተዘግቧል፡፡
በውይይቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከየአህጉረ ስብከታቸው ተጨባጭ ኹኔታ በመነሣትና ጽሑፉ በቀረበበት ይዘቱ በመገምገም በተለይ በመቻቻል፣ በመንግሥትና ሃይማኖት ግንኙነትና በኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ ዙሪያ ጥያቄ አንሥተዋል፤ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ቃል በተነገረበት አኳኋን ወደ ጽሑፍ ተመልሶ ቢቀርብ በተለይ በስፍራው ላልነበሩና በሌሎችም መንገዶች ለመከታተል ዕድል ላላገኙ ወገኖች ይጠቅማል በሚል በጡመራ መድረኩ ተስተናግዷል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ በጉዳዩ ላይ የሰነዘሩት ትችት፣ ያቀረቡት ጥያቄና የሰጡት ምስክርነት በሁሉም የዓመታዊ ስብሰባው ተሳታፊዎች ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን የመንግሥትን ተቋማት በሚመሩ ዓላውያንና መናፍቃን ጫናዎች መማረሯን ከመግለጽ ባሻገር በደሎችና ተጽዕኖዎች እስካልተወገዱ ድረስ መጪውን የከፋ አደጋ የጠቆመችበት፣ የመንግሥቱንም ተወካዮች በብርቱ የመከረችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ስለመኾኑ ከፍተኛ መግባባት ተደርሶበታል፡፡ 
ይልቁንም የውይይቱ ቁም ነገሮች፣ መንግሥት የፀረ አክራሪነት እንቅስቃሴዎቹን በሚያብራራባቸው ሰነዶቹ እንደሚያትተው፣በፕሮቴስታንት ሃይማኖት ሽፋን የጠባብነት አመለካከት ፖሊቲካ ከሚያራምዱ አካላት ጋራ ትስስር መፍጠሩና ሽፋን መስጠቱ፣‹‹ከማቆጥቆጥና አዝማሚያነት›› አልፎ በገሃድ መገለጹን የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ ‹‹የመልካም አስተዳደርና ሴኩላሪዝም ጥያቄን እንደ መንሥኤ ወስዶ ሕዝብን የጽንፈኝነት አመለካከት በማስያዝ›› ሰላማዊ መስተጋብሩን የማናጋት ሙከራው ለማቃናት አዳጋች ወደሚኾንበት ዳርቻ እየነጎደ መኾኑን ነው፡፡ ስለዚህም ‹‹ለመንግሥት መዋቅር የሚቀርቡ ጥያቄዎች ከአድሏዊ አሠራር በጸዳ መልኩ እንዲሰጡና ፍትሐዊ ጥያቄዎች አለምንም ማጉላላት እንዲፈጸሙ ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ›› በቃል የሰፈረው በተግባር ተተርጉሞ መታየት ይኖርበታል፡፡
 *                    *                    *
ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
የሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
His Grace Abune Qerlos
ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
ስላስተማሩን እናመሰግናለን፡፡ እንግዲህ ቤተ ክርስቲያኗ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምትነፍገው ነገር የለም፤ ያላትን ሁሉ ታበረክታለች፤ ታገለግላለች፡፡ አክራሪነት፣ ጽንፈኝነት የሚለውን ቋንቋ እናንተ ናችኹ ያስተዋወቃችኹን፤ እናንተው ናችኹ ያሰማችኹን፤ ከዚያ በፊትም አይታወቅም፤ በደርግም ይኹን በሌላ፡፡ እንደገና ደግሞ ብዙ ጊዜ ጽንፈኝነት፣ አክራሪነት እያላችኹ ዕድሜ ሰጥታችኹ ያበለጸጋችኋቸው እናንተው ናችኹ፡፡
አባቶቻችን፣ የእረኛ ሰነፍ ከቅርብ ሲሉት ከሩቅ ይላሉ፡፡ ወዲያው በአጭሩ መቅጨት ሲገባ ታሪካቸው እየተተረከ፣ እየተተረከ፣ እየተተረከ ብዙ ሕዝብ አተራመሱ፡፡ አዎ፣ ጥያቄዬ÷ ‹‹መረባቸውን በላይ ዘርግተዋል፤ መሬት ግን አልነኩም፤›› አሉ፡፡ እንዴ፣ ነክተው አይደለም ይህ ሁሉ የሚተራመሰው! መረባቸውንማ መሬት ዘርግተው ሕዝብ መካከል ገብተው፣ ሙስሊሙ ሕዝብ እንኳ ‹‹እኛ አናውቃቸውም፤ የእኛ አይደሉም›› እያለ እየጮኸ፣ እየጮኸ መረባቸውንማ መሬት አስነክተው ወጣቱን ትውልድ የመረዙት እነርሱ ናቸው፡፡ እንዴት መሬት አልነኩም፤ መረባቸው ወደ ላይ ነው ይላሉ? እንደ እናንተ መረባቸው መሬት ሲነካ እንዴት ሊያረጉን ይኾን?

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእምነታቸው ዘብ ቆመው ዋሉ!

ከጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘውና ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው ፴፪ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በነበረው ውሎ የተለየ ክሥተት አስተናግዷል፡፡ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚል ርእስ በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በተካሄደው ውይይት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ጋራ በተለይም በመቻቻልና በኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ ዙሪያ ሲከራከሩና በአንዳንድ ኹኔታዎችም ኤክስፐርቶቹን ሲገሥጹ ውለዋል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ÷ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ እንድርያስ÷ ከየአህጉረ ስብከታቸው ተጨባጭ ኹኔታና ከቀረበው ጽሑፍ እየተነሡ በመረጃ፣ በጥያቄና በትችት ስለ መቻቻል ጽሑፍ ያቀረቡ የሚኒስቴሩን ባለሥልጣናት ፈተና ላይ ጥለዋቸው አምሽተዋል፡፡ የሊቃነ ጳጳሳቱ ምስክርነት‹‹የባዕድ እምነት አራማጆች በቤተ ክርስቲያንና በካህናት ላይ ልዩ ልዩ ተጽዕኖ እንደሚያደርጉና ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ታላቅ ድፍረት እንደሚፈጽሙ›› ቀደም ሲል ለአጠቃላይ ጉባኤው የቀረቡ ሪፖርቶችን በገሃድ የሚያጠናክሩና የሚያጸኑ ናቸው፡፡
የሚኒስቴሩ አማካሪዎችና ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ ቅሬታዎቹ በተጨባጭ ማስረጃዎች ተደግፈው በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤበኩል ቢቀርቡላቸው መፍትሔ እንደሚሰጧቸው፣ በሊቃነ ጳጳሳቱ ከተገለጹት በላይ ያልተነገሩ ቅሬታዎች ስለመኖራቸው በየወረዳው ተዘዋውረው መረጃዎችን አሰባስበው ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል፡፡ በ‹‹ሕግ የተያዙት ጉዳዮች በሕግ እንደተያዙ ተጠብቀው እንዲቀጥሉ›› ለዚህም የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥንካሬ አስፈላጊ መኾኑን አሳስበዋል፡፡
የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጥያቄ፣ አስተያየትና ትችት በከፍተኛ ጥሞና የተከታተለው የአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊ የሞቀ ድጋፉን ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ የውይይት አጀንዳ አጋጣሚውን እንደ ምቹ ኹኔታ ለመጠቀም ያሰቡ የሚመስሉትና ልዩ ፍላጎት ያላቸው የሚመስሉት አቡነ ሳዊሮስ ውይይቱን ሳይጨርሱ አቋርጠው ሲወጡ ታይተዋል፡፡
*                        *                         *
His Grace Abune Qerlos

Wednesday, October 16, 2013

የመንግሥትን የአክራሪነት ፍረጃ ተከትሎ የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ ለውጥ የሚቃወሙ ጥቅመኞች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚሰነዝሩት ውንጀላ ተጠናክሯል፤ ማኅበሩ ክሥ ለመመሥረት እየተዘጋጀ ነው

Aba sawiros
  • ከጉጂ ቦረናና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከትና ሌሎች አብያተ ክርስቲያን በዘረፉት ገንዘብ ‹‹ሺበሺ›› በሚለው አስከፊ የሙስና ስያሜ የሚታወቁትና በነፍስ ግድያ ወንጀሎች የሚጠረጠሩት አቡነ ሳዊሮስ የሚያስተባብሯቸው የግብር አምሳሎቻቸው፣ መልአ ገነት አባ አፈ ወርቅ ዮሐንስ እና መልአከ ገነት አባ ዮናስ ታደሰ ዋነኛ ተጠያቂዎች ይኾናሉ ተብሏል፡፡

፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ተጀመረ

His Holiness Abune Mathias on the 32nd SGGA
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የአጠቃላይ ጉባኤው ርእሰ መንበር
  • የቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ በፍርድ ቤቶች ያለው ተቀባይነት ማነስ ያስከተለው ችግር፣ ልዩ እምነት ያላቸው አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርሱት ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ተጽዕኖ፣ ወደ ዐረብ አገሮች እየሔዱ እምነታቸውን ወደ እስልምና የሚለውጡ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር መበራከትና ከእኒህም የካህናት ሚስቶች መኖራቸው፤ የአብነት ት/ቤቶች ህልውና ቀጣይነትና በተለይም የመጻሕፍተ ሊቃውንት ጉባኤያት በብዛት መታጠፍ፤ የመንፈሳዊ ኮሌጆች አስተዳደር፣ የደቀ መዛሙርቱ ምልመላና ምደባ፤ በጠረፋማ አህጉረ ስብከት የአብያተ ክርስቲያን መራራቅ፣ በበጀትና በካህናት እጥረት ለችግራቸው ቶሎ መድረስ አለመቻልና የብዙዎቹ መዘጋት፣ በሰሜን ጎንደርና ቦረና አህጉረ ስብከትየአስተዳደር ችግራቸው ያልተፈታላቸው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የአህጉረ ስብከቱን 20 በመቶ ፈሰስ አንከፍልም ማለታቸው፣ ባልታወቁ ሰዎች የአብያተ ክርስቲያን መቃጠል፣ የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች (ዐደባባዮች፣ መካነ መቃብሮች፣ የልማት ቦታዎች) መደፈርና ወደ ግል የማዞር ችግር ጉባኤውን እያወያየ ነ፡፡

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ዐረፉ፤ የቀብር ሥነ ሥርዐቱ ነገ በኢየሩሳሌም ይፈጸማል

  • በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ከሠላሳ ዓመታት በላይ አገልግለዋል
  • ‹‹በጌቴ ሰማኔ፣ በጎልጎታ፣ በዴር አብርሃም ሁሉ ሰፊ ይዞታ እንዳለን በታሪክ ሰፍሯል፡፡ ግብር ለመገበር አቅም ስላነሰንዴር አብርሃምን ግሪኮች ወሰዱብን፤ ቤተ ልሔም ያለውን ርስታችንን አርመኖች ወስደውታል፤ በዚያ ላይ ያለንን መረጃ በሙሉ ቀደም ሲል አርመንና ግብጾች ወስደው አጥፍተውታል፡፡››
  • ‹‹ግብጾች በጣም ነው የሚከራከሩት፡፡ በዴር ሡልጣን ጉዳይ ግብጾች ያቋቋሙት ትልቅ ኮሚቴ አላቸው፡፡ ኢትዮጵያውያንም የእኛ ነው ካልን ዴር ሡልጣን ከእጃችን አይወጣም፡፡ ለዚህ ቦታ መርጃ የሚኾን አንዳንድ ፕሮጀክት መዘርጋት አስፈላጊ ኾኖ ሲገኝ ምእመናን እጃችኹን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ዴር ሡልጣን አለን ማለቱ ብቻውን በቂ አይኾንም፡፡››
  • ‹‹ሕዝቡ ከገዳሙ ጎን ቆሞ፣ ገዳሞቻችን እንደ ሌሎቹ በልጽገው ፈጣሪ እንዲያሳየኝ ጸሎቴ ነው፡፡ የዴር ሡልጣን ክርክር ፍጻሜ አግኝቶ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መብቷ እስከ ኾነ ድረስ የኢትዮጵያ ምእመናን ለዴር ሡልጣን መርጃ እንዲኾን አስቦ እንደ ግብጾች አንድ ድርጅት አቋቁሞ ለዚያ ሒሳብ ተከፍቶ እንዳየው እመኛለኹ፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. ለጋዜጠኞች የተናገሩት/
His Grace Abune Heryakos
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
(ከ1923 – 2006 ዓ.ም.)

Monday, October 7, 2013

‹‹የበደልናትን ቤተክርስቲያንን እንክሳለን ፤ ይዘን የወጣነውን ህዝብ መልሰን እናመጣለን ፤ ላጠፋነው ጥፋትም ቤተክርስቲያኒቱ ይቅርታ ታድርግልን›› ተሀድሶያውያን

ከእንቁ መጽሄት እንዳገኝነው
(አንድ አድርገን መስከረም 20 2006 ዓ.ም)፡- ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተይዞ በመታየት ላይ የሚገኝው የበጋሻው ደሳለኝ እና የያሬድ አደመን ጉዳይ በእርቅ መንገድ መፍትሄ እንዲፈለግለት በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኝው ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ መሆኗን ከቤተክህነት አካባቢ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡ መረጃው እንደሚያመለክተው በጋሻውና ያሬድ አደመ‹‹የበደልናትን ቤተክርስቲያንን እንክሳለን ፤ ይዘን የወጣነውን ህዝብ መልሰን እናመጣለን ፤ ላጠፋነው ጥፋትም ቤተክርስቲያኒቱ ይቅርታ ታድርግልን›› ማለታቸውና እርቁን መፈለጋቸው ታውቋል፡፡