Friday, February 24, 2012

ምክር

፩፦ ምክር



          የሰው ልጅ ከልጅነት እስከ እውቀት፥ ከኲተት እስከ ሽበት ምክር ያስፈልገዋል። ጳጳስም ሆነ ካህን፥ ባዕለጸጋም ሆነ ደሀ፥ ባዕለ ሥልጣንም ሆነ ተርታ ሰው፥ ምክር የማያስፈልገው የለም። ማንም ይሁን ማን፥ በጎ ኅሊና ያለው መካሪ ከሌለው ከሚያለማው የሚያጠፋው ይበዛል። አበው፦ «መካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ፤» ያሉት ለዚህ ነው። ከዚያ በላይ ቢነግሥ እንኳ በኃይል እንጂ በፍቅር ሊነግሥ አይችልም። እያሠረ፥ እየገረፈ፥ እያፈናቀለ፥ እየገደለ፥ ግፍ በግፍ ይሆናል።
በጎ ምክርን የሚሰማ እንዳለ ሁሉ፥ የማይሰማም አለ። ቅዱስ ዳዊት ከበጎ ኅሊና የሚመነጭ ምክር ለሰው ሕይወት እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ሲናገር «ለሚያደርጋት ሁሉ ምክር መልካም ናት፥ ምስጋናውም ለዘለዓለም ይኖራል።» ብሏል። መዝ ፩፻፲፥፲። ልጁ፥ ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞንም፦ «አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል። ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቆቅልሾችን ያውቃል። . . .  ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ትእዛዝ ቸል አትበል፤ ለራስህ የክብር ዘውድ ለአንገትህም የወርቅ ድሪ ይሆንልሃል።» በማለት መስክሯል። ምሳ ፩፥፭-፱።

የቦረና ጉጂና ሊበን ዞነን ሃገረ ስብከት በኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል ቀን በተነሳው ግጭት ከ40 በላይ ክርስትያኖች ታሰሩ

የቦረና ጉጂና ሊበን ዞነን ሃገረ ስብከት በኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል ቀን በተነሳው ግጭት ከ40 በላይ ክርስትያኖች ታሰሩ


  • በግጭቱ ምክንያት ንግስ አልነበረም ፤ ቅዳሴም ሳይቀደስ ቀርቷል
  • የሚጠቡ ህፃናት ቤት አስቀምጠው በእስር የሚገኙ እህቶች አሉ
  • አራት ሰዎች ያህል ከአንድ ቤት የታሰሩም ይገኛሉ
  • ምሽቱን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በእስር ላይ ከሚገኙት ምዕመናን ውስጥ የወረዳው ሊቀ ካህን መሪጌታ ልሳነወርቅ ወልዴ ፤ ቀሲስ ወርቁና  የ80 ዓመት እድሜ አዛውንት አቶ ዘውዴ አበሩ በእስር ላይ እንደሚገኙ  ለማወቅ ችለናል


(አንድ አድርገን የካቲት 16 ፤2004ዓ.ም) የቦረና ጉጂና ሊበን ዞኖች ሃገረ ስብከት የክብረመንግስት ከተማ  ህዝብ ትግል የተባረረውና ዛሬም የሃገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ነኝ የሚለው ተሾመ ሃይለማርያም አሁን መሽጎ በሚገኝበት በክብረመንግስት ከተማ ሌላ ቀውስ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ሳይጠሩ አቤት ሳይላኩ ወዴት የሚሉ ሰዎች ቤተክርስትያንን ከበዋት ይገኛሉ፡፡ የተሀድሶያውያን ርዝራዦች በየቦታው ጊዜ ጠብቀው በማድባት ቤተክርስትያናችን ላይ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ ፤ ከበላይ ያለው አመራር ንዝህላልነት በጉዳዩ ዙሪያ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል ፤ ችግሮች ሲፈጠሩ ለችግሮቹ ወቅታዊ መፍትሄ አለመስጠት ችግሮችን ሌላ ችግር እንዲፈጥሩ እድል እየሰጠ ይገኛል፡፡

Monday, February 20, 2012

በአሪዞና የተጀመረው እርቅ በመልካም ጅምር ተጠናቀቀ

በሀገር ውስጥ ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በውጪ በሚገኘው ሲኖዶስ በካከል ባለፈው ሳምንት የተጀመረው ድርድር እግዚአብሔር በፈቀደው በጥሩ ሁኔታ መጠነቀቁ ከሥፍራው በደረሰን ዜና ለመረዳት ችለናል። ከባለፉት

ድርድሮች ሁለቱም ወገኖች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ንግግር አድርገው አያውቁም ነበር፣ ሌላው ቀርቶ ሰላምታ እንኳን መለዋወጥ የቻሉበት ጊዜ እንዳልነበረ ስናስታውስ የአሁኑ ዙር በእውነቱ ትልቅ እና ብዙ ጉዞዎችን ያደረጉበት ነው ብለን እናምናለን፣ በማንኛውም ቦታ እና ዓለም የሚገኙ የሰላም ወዳድ ሀይሎች ለዚህ ለሃያ ዓመታት የዘለቀው የጠላትነት ጊዜ አብቅቶ፣ ቃለ ውግዘቱ ተነስቶ አንድ የሚሆኑበት እና እንደገና በአንድ መቅደስ የምናገለግልበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን እንገምታለን።
የተጀመረውንም የጾም ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ሰላም የናፈቀውን የተዋሕሶ ቤተሰብ እንደገና ሰለም እንዲያሳየን አብዝተን እንድንጸልይ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
የጋራ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


 የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

እንኳን ለታላቁ ጾም፣ ጾመ ሁዳዴ አደረሳችሁ




ይህ ታላቅ ጻም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሞቶ ሕይወት ሊሆነን በገዳም ገብቶ የጾመው ጾም ስለሆነ፣ እኛም መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ጾሙን የረደኤት የበረከት እንዲያደርግልን እና ለትንሳኤው በዓል በሰላም እንዲያደርሰን እንመኛለን።
ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን አብዝተን እንጸልይ፣ የድህነታችን፣ የእኛነታችን መገለጫችን፣ የኢትዮጵያ ሀገራችን የስልጣኔ ምንጭ እና ኩራት የሆነችው የተዋሕዶ እምነታችንን ከአረያም ሆኖ በቃሉ ችግሮችን አስወግዶ አጽራረ ቤተክርስቲያንን አስታግሶ፣ የረቁትን አቅርቦ ያሉትን እንዲያጸናልን የዘወትር ምኞችን ነው።
መልካም ጾም
ቸር ያቆየን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

Saturday, February 18, 2012

የአብነ ፋኑኤል ስብሰባ ለምን ይሆን?


የስብሰባው ቦታ

በዚህ በጨረስነው ሳምንት ውስጥ በአሪዞና የተጀመረው ጥቂት እንደሄደ ያለምንም ስኬት ተጠናቋል፣ በብዙ ተንታኞች ከበፊተኛው በበለጠ መቀራረብ ቢኖርም እስከ አሁን ብዙ መፈታት ያለባቸው ችግሮች ግን ሊፈቱ እንዳልቻሉ ይነገራል። እንደ ተንታኞቹ በተለይ ከአስታሪቂዎቹ ውስጥ ሌላ ስውር የሆነ መንገድ ይዘው እሚንቀሳቀሱ ሰዎች እንዳሉ ታውቋል፥ እውነታው ግን ጊዜው ሲደረስ ይታወቃል ብለን እናምናለን፥ ለሁሉም የእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ጸሎት እንደሚሆን እናምናለን፣ ሰላሙ ወርዶ ቤተክርስቲያን ወደ አንድ ሥርዓት የምትመጣበት ጊዜ እሩቅ የሚሆን አይመስለንም፣ ለዛ እንዲያበቃን እንመኛለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቡነ ፋኑኤል ለእርቅ የመጡትን አባቶች ይዘው በዋሽንግተን አካባቢ ተከታይ አለኝ፣ ሥራ እየሰራሁ ነው ለማለት ይመስላል ከእላይ ታች እየተባለ ነው። ከአካባቢው ምንጮች እንደተረዳነው በመጪው እሁድ የካቲት ፲፩ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. (Feb. 19, 2012) በፎልስ ቸርች አካባቢ በሚገኘው የሜቶዲስት ቸርች ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ እየተጣደፉ እንደሆነ ከአምንጮቻችን ተገልጾልናል። እንደምንጮቻችን ገለጻ በዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ሚካኤል ያላደረጉት ለምንድነው ብለው ሲጠየቁ፣ የተለያዩ ምክንያቶች እንዳላቸው ይነገራል ከነዚህም ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ነው፡

Thursday, February 16, 2012

ስድስት አብያተክርስትያናት በጧፍና እጣን እጦት የመዘጋት አደጋ አንዣቦባቸዋል

ስድስት አብያተክርስትያናት በጧፍና እጣን እጦት የመዘጋት አደጋ አንዣቦባቸዋል


(አንድ አድርገን የካቲት 08 ፤ 2004 ዓ.ም)፡-  የገሀነም ደጆች የማይችሏት ቀዳማዊት ንፅሂት እመቤት ቅድስተ ቤተክርስትያን ዙሪያዋን በጠላት ጦር  እየደማች ትገኛለች፡፡ አረማውያን ቤተመቅደስ እያፈረሱ መናፍቃን ቅጥሯን እየጣሱ ፤ ተሀድሶዎች የራሷ ያልሆነውን እያቀረቡ ወላጅ እንደሌለው ልጅ እያስጨነቋት ይገኛሉ ፡፡ ከጠላቶቿ በላይ እየጎዳት የሚገኝው የቤተክርስትያን አስተዳደር የተማከለ አለመሆኑ ነው፡፡

የሰሜን ሸዋ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እምነት ተከታይ ነው ፡፡ ሀገረ ስብከቱ ወደ ማዕከላዊ ቤተክህነት ፈሰስ የሚያደርገው ገንዘብ ቀዳሚ ከሆኑት ሀገረ ስብከቶች ውስጥ ይመደባል፡፡ ሆኖም ግን ሀገረ ስብከቱ ሲዳሰስ ከዝናውና ከክብሩ የማይስተካከል ገጽታ ይነበብበታል ፡፡ በሀገረ ስብከቱ የሚንቀሳቀሰው የደብረ ብርሀን ማህበረ ቅዱሳን ማዕከል ከሌሎች ማዕከሎቹ የተሻለ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ቢወራለትም በተግባር ግን የሚሰማውን ያህል ሆኖ እየሰራ አይደለም፡፡ በአሁኑ ሰአት በሀገረ ስብከቱ ስር ያሉ አብያተክርስትያናት በንዋየ ቅዱሳን እጦት የመዘጋት አደጋ አጋርጦባቸው ይገኛሉ፤  አብዛኞቹ መቀደሻ ጧፍ ፤ ማጠኛ እጣን ማግኝት አገልግሎቱን እያደናቀፈ እና እየተፈታተነ የሚገኝበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ ሀገረ ስብከቱ ያለባቸውን ችግር አጥንቶ የመፍታት አቅጣጫ ሲከተል ለማየት አልቻልንም ፤ ቤተክርስትያናቱ አካባቢው ላይ የሚኖረው ምዕመን ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ቤተክርስትያናቱ የሚያስፈልጋቸውን ንዋየ ቅዱሳት ለማሟላት የአቅም እጥረት መኖሩ አንዱ ምክንያት ነው ፤ ሀገረ ስብከቱ ዓመታዊ ፈሰስ የሚደርገው ብር እነዚህን የመሰሉ ችግሮች ፈተው መሆን ያለባቸው ይመስለናል፡፡ ቤተክርስትያናቱ እየተቸገሩ ፈሰስ ማድረግ ተገቢ ነው ብለን አናምንም፡፡ 

Tuesday, February 14, 2012

ተስፋዬ መቆያ እና ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን የአገልጋዮች ጉባኤ ተጠሪ ነን አሉ


ተስፋዬ መቆያ እና ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን

ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በአሜሪካን መዲና በሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ ላይ "የአገልጋዮች ጉባኤ" በሚል ከተቋቋመ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው ጉባኤ ጉባኤውን እንደተለመደው በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ርዕሰ አድባራት ቅድስተ ማሪያም ቤተክርስቲያን ማድረጉን ሰምተን ነበር፣ ከተለያየ ቦታ የመጡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ካሕናት፣ ዘማሪያን፣ እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ ሕገወጥ ሰባኪያን እና ዘማሪያን ብሎ በማንኛውም ዓውደ ምሕረት ላይ ቆመው እንዳይሰብኩ ወይም እንዳይዘምሩ የተለዩትም ዘማሪያን በቦታው በተጋባዥነት ተገኝተው ነበር።



በፊኒክስ አሪዞና እርቀ ሰላም ተጀመረ


እርቁ እውነት ይሆን? እርቁን የማይፈልግ ክፍል ይኖር ይሆን?

ዛሬ የካቲት ፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በፊኒክስ አሪዞና የኢትዮጵያው ቅዱስ ሲኖዶስ ተወካዮች

፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የመንበረ ፓትሪያሪክ ልዩ ጸሐፊና የድሬደዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ አትናቲዮስ የወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
፫ኛ/ ብፁዕ አብነ ቀወስጦስ የኣዲስ አበባ እና የምዕራብ ሸዋ ሊቀ ጳጳስ (በህመም ምክንያት መምጣት አልቻሉም)

፫ኛ/ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
እንዲሁም ከስደተኛው ሲኖዶስ የተወከሉ ደግሞ
፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ መልከፄዲቅ የስደተኛው ሲኖዶስ ጸሐፊ
፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስደተኛው ሲኖዶስ ተወካይ
፫ኛ/ ሌቀ ካህናት ምሣሌ
፬ኛ/ መልአገ ገነት ገዛህኝ ከስደተኛው ሲኖዶስ በኩል በተወካይነት ተወክለው በተጠቀሰው ቦታ ተገናኝተው እርቀ ድርድሩን ለማድረግ ትላንት ጀምረው ተወካዮቹ በፊኒክስ ተገኝተው ዛሬ ረፋዱ ላይ ስብሰባው እንደሚጀመር ይጠበቃል።

Monday, February 13, 2012

ስለ ጸብአቴ የማነ ብርሃን ተጨማሪ ማስረጃ

ከጥቂት ሳምንታት በፊት "ጸብአቴ የማነ ብርሃን ማናቸው" በሚል ያስነበብነው ይታወሳል የዚህ ጽሁፍ ምንጮቻችን እና አንባቢዎቻችን ተጨማሪ መረጃዎችን ልከውልናል እንደሚከተው አቅርበነዋል ተከታተሉት
ጸብአቴ የማነ ብርሃን ማናቸው? በሚል የቀረበው ጽሁፍ ላይ በጣም ብዙ የአትላንታ ነዋሪዎች እና በቅርብ የሚያቋቸውም የየግል አስተያየቶቻቸውን ጽፈውልናል አንዳንዱም የማስፈራሪያ መልዕክቶችን ልከውልናል፣ ነገር ግን አላማችን በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ የግል ጥቅማቸውን፣ የግል ክብራቸውን፣ ወይም ነውራቸውን ለመሸፈን በቤተክርስቲያናችን ሥም ተቀምጠው ያሉትን ሥራቸውን እናጋልጣለን ምዕመናን ከግል ቲፎዞተኝነት ወጥተው በእነዚህ ለግል ከርሳቸው የቆሙትን ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ወይም ጳጳሳት የኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አለመሆናቸውን ማሳየት አለብን በእነሱ ለግል ጥቅማቸው እሩጫ በሚያደርጉበት ጊዜ የሚሰናከለው ንፁሁ የተዋሕዶ መንጋ ግድ ሊለን ይገባል፥ ንጹሀን የተዋሕዶ ልጆች፣ እናቶች፣ እንዲሁም አባቶችን የመጠበቅ በተኩላ እንዳይወሰዱ የመንከባከብ የሁላችንም ሀላፊነት ስለሆነ ልንጠነቀቅ ይገባናል ባዮች ነን።
ከአትላንታ አካባቢ የተላከልን ደብዳቤ እንደሚከተለው ነው ተከታተሉት
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ይከበር የመጀመሪያው ደብዳቤ ሲሆን በመቀጠል ተጨማሪ መረጃዎችንም አያይዘው ልከውልናል
ተጨማሪ ስለ ጸብአቴ የማነ ብርሃን ማስረጃ

ቸር ይግጠመን

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

Saturday, February 11, 2012

የአቡነ ፋኑኤል ማስፈራሪያ

አባ ፋኑኤል እና የአባ ሰላማ ግንኙነት

አቡነ ፋኑኤልን እና "አባ ሰላማን" ምን አገናኛቸው???
 በወርሃ ጥቅምት በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በስተ መጨረሻ ሹመታቸውን አረጋግጠው ወደዋሽንግተን ዲሲ በድብቅ የገቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የእስከ አሁኑ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ አካሄዳቸው ብዙዎችን አስደምሟል፣ እንደ አንድ መንፈሳዊ መሪ በተቻለ መጠን ልዩነትን ወደ ጎን  ትቶ ለመሥራት እንደ መሞከር ይባስ ብለው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማስፈራሪያዎችን የአባ ፋኑኤል አፈ ቀላጤ በሆነው አባ ሰላማ በተሰኘው የመናፍቃኑ አንደበት በሆነው የብሎግ መድረክ ማስፈራሪያዎችን ጨምሮ ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስፈፃሚ ሥራ አስኪያጅ ለሆኑት ለቀሲስ ዶ/ር መስፍን ልከውላቸዋል።

በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው አቡነ ፋኑኤል ቀሲስ ዶ/ር መስፍን የጀመሩትን ሥራ ካላቆሙ እርምጃ እወስዳለው በማለት ማስፈራሪያን ጨምረው በደብዳቤው ገልጸዋል የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ያገኙታል እንደ አቡነ ፋኑኤል ከሆነ ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ቤተክርስቲያን ፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር ያሉት አጥቢያዎች፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ እንዲሁም ሕዝበ ክርስቲያኑ የጣለችባቸውን ሃላፊነት ባስቸኳይ ካላቆሙ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል። እረ ለመሆኑ የሚሰሩት መንፈሳዊ ሥራ ነው ወይስ ሌላ የፓለቲካ ሥራ ነው? አቡነ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ከመጡ ጊዜ ጀምሮ በሀገረ ስብከቱ ታቅፈው ከነበሩት አጥቢያዎች ወደ አንደኛው እንኳን በመሄድ ለማግባባት አለመሞከራቸው፣ የነበረውንም ሥራ አስፈጻሚ እንደ ቤተክርስቲን መዋቅር እኔ አላውቅህም ከማለት የፍትህ መንፈሳዊ በሚያዘው መሠረት ሰብስቦ ሥርዓት ባለው መንገድ መሥራት አለበለዚያም በሌላ መተካት ሲቻል፥ ጭራሽ መኖሩንም አላውቅም ሲሉት የነበሩትን ሥራ አስፈጻሚ ማስፈራራት ምን የሚሉት አካሄድ ነው።

የዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ለአደጋ ተጋልጧል

የዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ለአደጋ ተጋልጧል

·     በገዳሙ ክልል እና ዙሪያ (በዓዲ አርቃይ ወረዳ በኩል) የፓርክ ይዞታ ለመከለል እና የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሚል በሚካሄደው የጥርጊያ መንገድ ሥራ (ከማይ ፀብሪ እስከ ዕጣኖ ማርያም) የቅዱሳን አበው ዐፅም እየፈለሰ መሬቱ እየታረሰ ነው
· የሦስቱ ገዳማት ማኅበረ መነኮሳት ዕቅዱ የገዳሙን ክብር የሚጋፋ ህልውናውንም የሚያጠፋ በመሆኑ እንዲቆምላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል

·   መንግሥት ካቀዳቸው 10 ግዙፍ የስኳር ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክቶች አንዱ በዋልድባ ገዳም ክልል እና ዙሪያ (ወልቃይት - መዘጋ) የሚቋቋም ሲሆን በዛሬማ ወንዝ ላይ 3.8 ቢልዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ የመያዝ አቅም ያለውና 40,000 ሄ/ር የሸንኮራ ተክል የሚለማበት ግድብ ይቆምለታል፤ ግድቡ በሚሸፍነው ስፍራ (ማይ ዲማ) የሚገኙ አራት አብያተ ክርስቲያን የሚነሡ ሲሆን ለ10,000 የፕሮጀክቱ ጊዜያዊ እና ቋሚ ሠራተኞች የመኖሪያ ካምፕ ግንባታ እየተካሄደ ነው
·    በቅድስት ገዳማችን ዋልድባ ውስጥ ለሚደረገው አግባብ ያልሆነ እንቅስቃሴ አበው ቅዱሳን አባቶቻችን ልዩ ሥራ እንዳይሠራባት የውግዘት ቃል (እንበለ ፈላሲ ኢይባዕ ነጋሲ) ያሳለፉባት ቦታ በመሆኗ ማኅበረ መነኮሳቱ ባደረግነው ምልአተ ጉባኤ መሠረት ለሚሠራው ሥራ ፈጽሞ ፈቃዳችን አለመሆኑንና የአባቶቻችን ቅዱሳንን ፈለግ ሕግና ሥርዐት ተከትለን የምንሄድ መሆናችንን በጥብቅ እናሳውቃለን

Wednesday, February 8, 2012

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

 
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከመንፈሳዊ የአስተዳደር ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ ከሀገረ ስብከቱ ድረ ገጽ ላይ አግኝተናል::
 
ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

 
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል


"ታላቅ ምክር"

የብፁዕነትዎን ይቅርታ እየጠየቅሁ እንደ መንፈሳዊ ልጅነቴ በግሌ ላሳስብዎት የምሻውን ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ። እድሜ 30ዎቹ ሲሆን በውጭ ሃገር ተወልደው አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋ እምነትን በባለቤትነትና በኩራት የሚከተሉ ሁለት ልጆችን እግዚአብሔር ሰጥቶኛል። ድሜቸው በአስራ ሲሆን በእምነታቸው ግን በጣም በመብሰላቸው ለዘመኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ንትርክ ሳይወዱ ተካፋይ ሆነዋል። ለዚህም የዳረጋቸው በየአብያተ ክርቲያናቱ ዶግማና ቀኖና ርዓት ነው። ዝርዝሩን እዚህ ላይ ባላሰፍረውም የሁሉም የእምነቱ ተከታይ የሆኑት ምእመናን ቤት ጠንቅቆ ያውቀዋል።

Tuesday, February 7, 2012

ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል

  • ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አይደለችም፤ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናት” ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
 READ IN PDF
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጋዜጠኛ ከአቶ አዲሱ አበበ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሀገረ አሜሪካን ስለምትገኘው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ግንዛቤ ለሌላቸው አድማጮች እውነት የሚመስሉ፤ ነገር ግን በመሬት ላይ ካለው እውነት ጋር ፍጹም የማይገናኙ  ትንታኔዎችን ሰጥተዋል:: “የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጵጵስና በተቀበሉበት ወቅት ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዳስረከቡ መረጃዎች አሉን የሚሉ ወገኖች አሉ፤ ነገር ግን አሁንም ድረስ  ቤተ ክርስቲያኑ በእርሶ እጅ እንዳለ ይወራል” በማለት አቶ አዲሱ አበበ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አይደለችም፤ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናት” ብለው ነበር:: ይህ አነጋገር በሰሜን አሪሜካ ስላለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናን በቂ መረጃ ለሌላቸው ሰዎች እውነት ቢመስልም ሐቁ ግን ከዚህ የራቀ ነው::
 ለብፁዕ አባታችን አሁን ደግሞ እኛ አንድ ጥያቄ እናቅርብ እስኪ፤ እውነት በሰሜን አሜሪካን ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናትን? 

Monday, February 6, 2012

የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ


·         በስብሰባው ያልተገኙት አቡነ ፋኑኤል ከአካባቢው ለሰበሰቧቸው ካህናት አዲስ ሹመት ሰጥተዋል፤
(ደጀ ሰላ ጥር 28/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 6/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ አጠቃላይ ጉባዔውን በኖርዝ ካሮላይና ሻርለት በማካሄድ እና መሠረታዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ እንደተጠናቀቀ ምንጮች ለደጀ ሰላም ገልጸዋል። ጥር 25 እና 26/ 2004 ዓ.ም በሀ/ስብከቱ ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በተገኙበት በተደረገው የምክክር ጉባኤ ላይ “የሀ/ስብከቱን መኖር አላውቅም” ያሉት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አለመገኘታቸው ታውቋል።

Thursday, February 2, 2012

አቡነ ፋኑኤል ሀ/ስብከት በማፍረስ ጎዳና ላይ ይሆኑ?

አቡነ ፋኑኤል ሀ/ስብከት በማፍረስ ጎዳና ላይ ይሆኑ?


(ደጀ ሰላም፣ ጥር 24/2004 ዓ.ም፤ February 2/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ምትክ የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሀ/ስብከቱን መኖር እንደማያውቁ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በተናገሩ ማግስት ለቅ/ፓትርያርኩ የላኩት ደብዳቤ ለድረ ገጻችን በአድራሻ ተልኮልናል፡፡ ደብዳቤውን ያደረሱንን ደጀ ሰላማዊ ከልብ እናመሰግናለን።
ሊቀ ጳጳሱ አስቀድሞ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ሀ/ስብከት መኖሩን አላውቅም” ማለታቸውን ሰምተናል። ያንን አስከትለው ደግሞ የለም ያሉትን ሀ/ስብከት “በሕግ ለመጠየቅ” ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ባልሸሸጉበት ሁኔታ በሀ/ስብከቱ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በብፁዕ አቡነ አብርሃም ሰብሳቢነት ባደረጉት ዓመታዊ ጉባኤ የተቋቋመውን የሀ/ስብከቱን ሥራ አስፈጻሚ “ሕገ ወጦች” እና “የግል ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች” በሚል ጠርተዋል።